በሙኒክ ጀርመን ፀረ-ወያኔ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ::

በሙኒክ ጀርመን ፀረ-ወያኔ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ::

በዛሬው እለት በጀርመን ሰአት ከጠዋቱ ስምንት ሰአት ጀምሮ የኦሮሞ ኮሚኒቲ በሙኒክ እና ኢትዮጵያውያን አክቲቭስቶች ያዘጋጁት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን ሙኒክ መካሄዱን በቦታው የነበሩ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ ምንጮች ገልጸዋል::

የሕወሓት ቁንጮ ባለስልጣን የሆነው ዶ/ር ቴወድሮስ አድሀኖም የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በኢትዮጵያ ከግብረአበሮቹ ጋር የሚፈጽመውን ወንጀል እና ግፍ ለመቃወም የተጠራው ይህ ሰልፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን ኢሰባዊ ድርጊት በማውገድ ድምጹን ሲያሰማ አርፍዷል::በርካታ ወገኖቻችን በሀገር ውስጥም በውጭም እንደ አመት በአል በግ ሲታረዱ ትንፍሽ የማይለው ዶ/ር ቴወድሮስ በየሀገሩ እየዞረ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚፈራረመው ቀልፍ የህወሓት ሰው በመሆኑ
ይህ ጸረ ኢትዮጵያ ሰው ለማውገዝ ኢትዮጵያውያን ከያሉበት ተሰብስበው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል::