የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ወደነበረበት ቦታ መመለስ የህዝቡ ትግል ውጤት መሆኑን ሰማያዊ ገለጸ
የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ወደነበረበት ቦታ መመለስ የህዝቡ ትግል ውጤት መሆኑን ሰማያዊ ገለጸ
•ፓርቲው በነገው ዕለት ሐውልቱ ሲመለስ ህዝቡ በቦታው እንዲገኝና ክብሩን እንዲገልጽ ጥሪ አቅርቧል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ግንባታ ምክንያት ሚያዝያ 24/2005 ዓ.ም ፒያሳ ማዘጋጃ ቤት አካባቢ ከነበረበት ቦታ እንዲነሳ ተደርጎ የነበረው የአርበኛ አቡነ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት ከሦስት አመት ገደማ በኋላ ነገ ጥር 29/2008 ዓ.ም ወደነበረበት ቦታ እንዲመለስ የህዝቡ ትግልና ያላቋረጠ ጥያቄ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት መጀመሪያውንም ከቦታው እንዳይነሳ ህዝቡ አሳስቦ እንደነበር በማስታወስ ሐውልቱ ወደነበረበት ቦታ እንዲመለስም በተከታታይ ጥያቄውን በማንሳት ለታሪኩና ለባለውለታዎቹ ያለውን ተቆርቋሪነት እንዳሳየ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የቀላል ባቡሩ ስራ ሲታሰብ ዲዛይኑ ቅርሶችን በማይነካ መልኩ መሆን እንደነበረበት የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ ነገሩ ከሆነም በኋላ ቅርሱ ወደነበረበት ቦታ እንዲመለስ ህዝቡ ያደረገው ትግል የሚመሰገን ነው ብለዋል፡፡
መንግስት የባቡር ስራው ተጠናቅቆ ወደስራ መግባቱን ተከትሎ ሐውልቱ እንደሚመለስ ያስታወቀው ከህዝቡ የተነሳበትን ጥያቄ ተከትሎ እንጂ ለቅርሱ ከመቆርቆር እንዳልሆነ ከመጀመሪያው በባቡር ዲዛይን ስራው ወቅት (ቅርሱን እንደሚነካው እየታወቀ) ያሳየው ግዴለሽነት አመላካች መሆኑን ኢ/ር ይልቃል ገልጸዋል፡፡ ሐውልቱ በነገው ዕለት ወደቦታው ሲመለስ ህዝቡ ከ5፡00 ጀምሮ ፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ በመገኘት ለሀገር ባለውለታው አርበኛ እና ለታሪኩ ያለውን ክብር እንዲገልጽም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አቡነ ጴጥሮስ በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ወቅት ለጣሊያን እንዲገዙና ኢትዮጵያውያንም ለጣሊያን አሜን ብለው እንዲተዳደሩ እንዲቀሰቅሱና እንዲያሳምኑ በፋሽስት ቢጠየቁም እምቢ ለሀገሬ እና ለሐይማኖቴ በማለት እንኳንስ የኢትዮጵያ ህዝብ ምድሩም ለፋሽስት እንዳይገዛ በማውገዝ መስዋዕት የሆኑ ታላቅ አርበኛ ናቸው፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ለዚህ የተጋድሎ ተግባራቸው ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓ.ም ዛሬ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ መታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ችሏል፡፡

This is a completely empty bravado.Its a useless and cheap effort to boost party ego.To start off the statue shouldn’t have been touched and tempered with lest by the hands of the children of ባንዳs whose fathers took orders from facist italians and executed the patriot pop.Children of bands removed the statue just to humiliate the Ethiopian people as always.This so called engineer yilikal is unable to lead his party which is infiltrated by evil woyane.But sorry you can not be credited for this.evil woyanes could have destroyed the statue if they wanted.Infact woyanes should take credit for returning this statue intact.
የማይካድ ሀቅ ነው።
ታሪክን ማንነትን ኢትዬጵያን እየበታተነ እያጠፋ ካለው ሥርአት ለመላቀቅ አሁንም የጋራ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥል ታሪክ በወያኔ አሻራ አይጠፋም ትፍልዱ ይህን የማስጠበቅ ውዴታም የዜግነትም ግዴታም አለበት።
ሞት ለወያኔ።
Is that for independent oromia?
Are the 5 seccessionists – which united in one of scandnivan countries – encircling ethiopia to disintegrate it?
Is that the reason the ethiopian patriotic front in eritrea is kept silenced, paralayzed?
It is shocking.
If the oromo protest is for oromia independence against ethiopian unity, then we must fight against oromia independece.
So let us check it and decide.
The ethiopian military (excluding tgrai woyanie military) must be organized and combate any seccession movement soon woyane’s collapse.
“…ሀዉልቱ እንደሚመለሰ ያስታወቀው ከሕዝቡ የቱነሳበትን ጥያቄ ተከትሎ እንጄ ለቅርሱ ተቆርቁሮ እንዳልሆነ …”ከ ሠማያዊ መግለጫ የተወሰደ
አሁን ከዚህ መግለጫ ምን ፖለቲካ ትርፍ እንደ ሚገኝ አልገባኝም ይልቅ አሁን እንደ ተረዳሁት ተቀዋሚ ማለት መንግሥት የሠራውን መልካም ሰራ ሁሉ መቃወም የሚል ስርዓት እየዘረጋ ያለ ይመስላል ምንም ይሁን ምን የ አባታችን የሠማዕቱ መታሠቢያ ሀውልት መንግስት ወደነበረበት ቦታ እንደ ሚመለስ ሲገፅ ሊመሰገን በተገባው ነበር እያወራሁ ያለሁት መፅሐፍ ቅዱስ ወይም ቅዱስ ቁርዐን አይደለም የማወራው የሆዴን በሆዴ ፖለቲካ እንጄ ዳሩ ምን ያደርጋል በመንግስትና በተቃዋሚዎች ግትር እና የፖለቲካ ቁማር የማይችሉ ተወትፈዉ ሕዝቤን የጋለ የእሳት አሎሎ እንዲሸከም በሁለቱም ወገን ፈረዱበት።በሁለታችሁም እስቲ ሰትመሰጋገኑ እንስማ።
nesiebho le egziabher sibuha zetesebha.
“…ሀዉልቱ እንደሚመለሰ ያስታወቀው ከሕዝቡ የቱነሳበትን ጥያቄ ተከትሎ እንጄ ለቅርሱ ተቆርቁሮ እንዳልሆነ …”ከ ሠማያዊ መግለጫ የተወሰደ
አሁን ከዚህ መግለጫ ምን ፖለቲካ ትርፍ እንደ ሚገኝ አልገባኝም ይልቅ አሁን እንደ ተረዳሁት ተቀዋሚ ማለት መንግሥት የሠራውን መልካም ሰራ ሁሉ መቃወም የሚል ስርዓት እየዘረጋ ያለ ይመስላል ምንም ይሁን ምን የ አባታችን የሠማዕቱ መታሠቢያ ሀውልት መንግስት ወደነበረበት ቦታ እንደ ሚመለስ ሲገፅ ሊመሰገን በተገባው ነበር እያወራሁ ያለሁት መፅሐፍ ቅዱስ ወይም ቅዱስ ቁርዐን አይደለም የማወራው የሆዴን በሆዴ ፖለቲካ እንጄ ዳሩ ምን ያደርጋል በመንግስትና በተቃዋሚዎች ግትር እና የፖለቲካ ቁማር የማይችሉ ተወትፈዉ ሕዝቤን የጋለ የእሳት አሎሎ እንዲሸከም በሁለቱም ወገን ፈረዱበት።በሁለታችሁም እስቲ ሰትመሰጋገኑ እንስማ።
በዉነቱ የጴጥሮስ ሐዉልቱ ቦታዉን መያዙ ለሁላችንም ትልቅ ፌሺታ ነዉ ከዘረኞች በስተቀር። ዛሬ ድምጻችን ይሰማ እያለ የሚያናፋዉ ከዚህ አፋኝ ስርአት ጋር እጅና ጓንት ሁኖ ሲሰራ መንግስታችን እያለ አትንኩብኝ ሲል የነበረ መሆኑን አድሜያቸዉ ከ18 በላይ የሆኑ ዜጎች ሁሉ ያዉቁታል እሱን ወደ ጎን ትተን በዚህ ክስተት ተጠልፎ የወደቀዉ ባለ ሜንጫዉ ጁዋር መሀመድ ነዉ። ጁዋር መሀመድ ለአቡነ ጴጥሮስ የኦሮሞ ስም ሰጥቶ ወደ ቦታዉ መመለሱን ደግፏል እግዜር ያሳያችሁ የአቡን ጴጥሮስን ገድል ያያዘዉ ከእሱ ደካማ አስተሳሰብ ነበር። ጁዋር በዚህ ንግግሩ ተጠልፎ የወደቀዉ የኢትዮጵያ ታሪክ በዛ ምድር ለሚኖሩ መልካም ኢትዮጵያዉያን እንጂ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ አልነበረም።ስለዚህ ጴጥሮስ ኦሮሞዉ ከእሱ በብዙ መልኩ መብለጡን የሚያሳይ ነዉ። ጁዋር በነካ እጂህ እነ ራስ ጎበናን፤አብዲሳ አጋን፤ገበየሁ ባልቻን አድናቆትህን ግለጽልን። ስላንተ ከሚገባ በላይ መረጃ ቢኖረንም በወያኔ ፔይ ሊስት እንዳለህ መሆኑን ብናዉቅም ስላንተ እየሸራረፍን እያወጣን ደካማነትህን እናሳየለን። ተስፋዬ ገ/አብን የበላዉ አይን እንዳይበላህ ትንሺ ቀዝቀዝ በል።በኦሮሞ ስበሰባ የወሰድከዉን ለ ኦቦ ሰለሞን በደረሰኝ ገቢ አድርግ በ 180፣000 ዶላር ካልታመንክ በሌላዉ እንዴት ትታመናለህ?
Abune Petiros’s original name was Magarsa Badhasa born in Salale, Fitche. He is pure oromo both in his father and mother.
Birrahun ena Ayalkebet yemimesaselut
hultum yehizbin tegel yenesu wuttet
aregew yimewsed abaze alachew .
ke Jawar garm yetetalut bezehu neaw .