የአዲስ አበባን መስፋፋት በተመለከተ የተሰጠ አስተያየት – ተፈራ ድንበሩ
ሰሞኑን የኦሮሞ ፈዴራሊስት ኮንግሬስ ባለሥልጣን የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ በፖርቲው ስም ያወጡትን መግለጫ ይመለከታል።
በመሠረቱ ፖርቲያቸው ሕዝባዊ ዓላማዎችን አንግቦ ሕዝባዊ ጥያቄዎችን ቢያነሣ መብቱ ስለሆነ እንደሕዝብ ፖርቲ የመንቀሳቅስ መብቱን ሊከበርለት ይገባል። ሆኖም በመግለጫው ላይ የሠፈሩት ሐሳቦች ኦሮምንና ኦሮሚያ የሚባለውን አዲስ አገር ከሌላው ሕዝብና አገር ለይተው አስቀምጠዋል፤ እንዲዚሁም አዲስ አበባን ከፈዴራላዊ አመለካከት ጋር በሚቃረን ሁኔታ የከልሉ መብት ተጥሷል ብለው አቅርበውታል። ሆኖም መሠረታዊ ችግሩ ላይ ባለማተኮራቸው ኢሕአዴግ የሚፈልገውን ጨዋታ እየተጫወቱለት ነው።
ይኸውም መንግሥት የአዲስ አበባን መስፋፋት ሰበብ አድርጎ ተጨማሪ ባለሥልጣናትን የሥርዓቱ ተገዥ ለማድረግ እና ተጨማሪ የሀብት መዝረፊያ መንገድ ለመክፈት፣ እንዲሁም የኦሮሞን ሕዝብ ማንነት፣ ቋንቋ፣ ባህል የማጥፋት ዘመቻ ነው ብለዋል። በዚህ አባባላቸው ባለሥልጣናትን የሥርዓቱ ተገዥ ማድረግም ሆነ ተጨማሪ የሀብት መዝረፊያ መንገድ የተባሉት የመቃወሚያ ነጥቦች በመሠረቱ የአዲስ አበባን መስፋፋት የሚቃወሙ አይደሉም። በመስፋፋቱ ሰበብ ይከተላሉ የተባሉት ችግሮች የሚያመለክቱት ውሳኔ ሰጭው መንግሥት ራሱ ሊታመን አለመቻሉን ነው እንጂ፤ ይህ መንግሥት ካልታመነ ደግሞ የሚወስደውን ትክክለኛ ይዘት ያላቸውንም ሆነ ትክክለኛ ይዘት የሌላቸውን አንድ ላይ ጭፍልቆ ሁሉንም መቃወም ነወይ የሚበጀው ወይስ ሌላ አማራጭ መውሰድ?
ስለአሜሪካ ያነሡት ጠቅላይ ግዛቶች /states/ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ሥልጣን እንዳላቸው መጥቀሳቸው እንዳለ ሆኖ፤ በዘር /ethnicity/ የተመሠረተውን የኦሮሚያ ክልል ከዚያ ጋር ለማነፃፀር መሞከራቸው ወርቅንና ብረትን የማወዳደር ያህል ነው፤ ምክንያቱም ያ ሥርዓት ያለበትን አጠቃላይ ይዘት አብረው መውሰድ ስላለባቸው ነው። አሜሪካ በዘር፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖት… ወዘተ ላይ የተመሠረተ ፈዴራሊዝም የላትም፤ አንድ አሜሪካዊ ከየትም ይምጣ የትም ይወለድ በየትኛውም ጠቅላይ ግዛት ተዘዋውሮ መኖር፣ መሥራት፤ ልጆቹን ማስተማር ይችላል፤ አሜሪካኖች በሁሉም ጠቅላይ ግዛትች የሚናገሩት ከቅኝ ግዛታቸው የወሰዱትን እንግሊዝኛን ሲሆን ያንን ቋንቋ በመጠቀማችው አደጉ እንጂ አልተጎዱበትም፤ ምክንያቱም ማንኛውም ቋንቋ (እንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ጊዶልኛ፣ አገውኛ፣ ትግርኛ፣ ወዘተ..) ለተገልጋዮቹ የመገናኛ መንገድ /medium of communication/ እንጂ ሐጢአት የለበትም፤ የአሜሪካ ጠቅላይ ግዛቶች (United States) የተፈጠሩት በታሪካዊ/ፖሊቲካዊ/ ጅኦግራፊ እንጂ በዘር ወይም በቋንቋ አይደለም። ኦሮሚያ ግን በቋንቋና ዘር አገርን እና ሕዝብን በመከፋፈል ሕዝብን ለያይቶ ለሚገዛው ኢሕአዴግ መንግሥት በመሣሪያነት እያገለገለ ነው። መቀላቀልንና ማንነትን የማጣት ጥያቄም ከጠባብ ብሔርተኝነት የሚመነጭ አመለካከት ነው፣ ምክንያቱም መነጣጠልን /isolationism/ የሚከተል ጎታች አስተሳሰብ ነው፤ ባለፉት 40 ዓመታት እንኳ እንዲህ ያሉ የውስጥ ችግሮች ባይኖሩብን ኖሮ የት መድረስ እንችል እንደነበር በአንፃሩ የበለፀጉ አገሮችን ታሪክ አነፃፅሮ በማየት መቀላቀልን /integration/ ለሕዝቦች መቀራረብና ማኅበራዊ ፍቅር ተጠቅመውበት እነሆ በእድገት ላይ አተኩረውና ከኛ ልቀው የሚገኙትን ምእራባውያን አገሮች አንጋጠን ልናያቸው ችለናል።
ወረድ ብሎ ደግሞ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ውስጥ ላሉ ከተሞች ዕቅድ የማውጣት አቅሙም ሥልጣኑም የለውም ሲሉ፤ በሌላ በኩል ግን ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ የቀረጥ ገቢ እንድታገኝ ተጠይቆ ለረዥም ጊዜ ሳይፈጸም መቆየቱን ጠቅሰዋል፤ ይህ የሚያመለክተው ደግሞ አዲስ አባባም ሆነ በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች በኦሮሚያ ሥር መሆናቸውን እንደሚቀበል ነው፤ ይህ ከሆነ የማካለል ተግባር የተፈጸመው በዚያው በኦሮሚያ ሥር ስለሆነ መሬት ተወሰደብን የሚለው ጥያቄ ትርጉም ያጣል።
በአገራችን ድልድይ አይሠራብን፤ መንገድ አይገነባብን፤ የአስኳላ ትምህርት ቤት አይከፈትብን፤… ያሉ ኢትዮጵያውያን በአንድ ዘመን የነበሩ ሲሆን፤ በአንፃሩ መንገድ በመሬታችን ካላለፈልን፤ ድልድይ ካልተሠራልን፤ ትምህርት ቤት ካልተከፈተልን በማለት ትግል የተደረገበትም ዘመን ነበር። እድገት አይደረግ ብሎ መሟገት ተገቢ አይደለም፤ ሆኖም ግንባታ ሲፈጸም የሕዝብ መብት እንዲከበር፤ በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሕዝብ በተወካዩ አማካይነት በተገቢው ሁኔታ እንዲሳተፍ፤ እንዲሁም ግንባታው የሚያፈናቅለው ወገን ካለ ተገቢው ካሣ እንዲከፈለው ማድረግ የወግ እና ፍትሐዊ ነው።
ቀጥሎ የተመለከተው ደግሞ “አንዱን አካባቢ ከሌላው ጋር የመቀላቀል ተግባር የምእራባውያን እንጂ የኛ አይደለም” ብለዋል። ይህ አባባል እኛ እርሻ የምናርሰው በሞፈርና ቀንበር ስለሆነ ትራክተርና ኮምባይን ሀርቨስተር አያስፈልገንም፤ ዲሞክራሲ የሚባል ነገርም በግሪክ ተፈጥሮ ምእራባውያን የሚጠቀሙበት ሥርዓት እንጂ የኛ አይደለም፤ አያስፈልገንም… የሚያሰኙ መሠረታዊ ስህተቶች ውስጥ ይጥለናል።
ወደእውነተኛው ፊዴራሊዝም መመለስ ይገባናል በማለት ያስቀመጡት መደምደሚያ ራሱ አጠያያቂ ነው፤ ምክንያቱም በአገራችን የነበረው ፊውዳሊዝም ከዚያም የኮሚኒስት አቅጣጫን ይዞ የነበረው ፍጹም ማእከላውነትን የተከተለ አሪስቶክራቲክ አመራር የነበረ ሲሆን፤ ኢሕአዴግም በስም ፀረ-ኮሙኒዝም ቢመስልም ከደርግ የቀዳውን ኮሚኒስታዊ የአወቃቀር ሥርዓት የተከተለ አምባገነናዊ ሥርዓት ስለሆነ እንመለስበት የሚሉት ፊዴራሊዝም ሁሉቱንም አይመለከትም። ከዚያ በፊት የነበሩት የኦሮሞ አፍ ሲነገርባቸው የነበሩት ግዛቶች ጅማ፤ ሊሙ-እናርያ፤ ጎማ፣ ጉማና ጌራ በሁለት ትውልድ ውስጥ በሚለካ ጊዜ ውስጥ የነበሩ ታዳጊ ፊውዳላዊ አመራር ይከተሉ የነበሩ ትናንሽ የጊቤ አካባቢ መንግሥታት ነበሩ እንጂ አሁን አሮሚያ ከተባለው ክልል ጋር የማይመጣጠኑ ስለሆነ ፊዴራላዊ ይዘትም ፅንሰ-ሐሳብም አልነበራቸውም፤ እነሱም ቢሆኑ በግዛት ስፋት ለማደግ እርስበርሳቸው ሲዋጉ የነበሩ እንጂ ፊዴራሊዝምን አያውቁትም። ሆኖም እንመለስበት የሚሉት መቼ ሥራ ላይ የዋለ ፈዴራሊዝም ማለታቸው እንደሆነ ግልጽ አይደለም።
ለሆነም አዲስ አበባ ኦሮሚያ የሚባል መንግሥት ከመፈጠሩ በፊት የነበረችና የሁሉም ኢትዮጵያውያን መገልገያ ዋና ከተማ /metropolitan city/ መሆኗ መታወቅ አለበት። የፖርቲው አመለካከት ችግር ሊንፀባረቅ የቻለው ከርዕዮተ ዓለማቸው ጋር ከሞቱ 60 ዓመታት ካለፋቸው ጆሲፍ ስታሊን እና ብላድሚር ኤሊኽ ሌኒን ለብሔረሰቦች ችግር መፍቻ ተጠቅመውበት የነበረውን ያውም ፖላንድ ላይ ተሞክሮ ጆርጅያ ላይ የከሸፈውን ፅንሰ-ሐሳብ /defunct theory/ መመሪያቸው በማድረጋቸው ነው፤ የኢሕአዴግም አመሠራረት ይህንኑ ጽንሰ-ሐሳብ የተከተለ ነው። ብሔርተኝነት አልፎ አልፎ በታዳጊ አገሮች የሚገኙ ጠባብ ብሔርተኞች የተወሰኑ ሕዝቦችን በቋንቋና ዘር ለይተው እንደፈረስ በመጋለብ የሥልጣን ጥማቸውን የሚያረኩበት ያረጀ ፅንሰ-ሐሳብ ሲሆን ኢምፔሪያሊስቶችም ትናንሽ አሻንጉሊት መንግሥታትን በመፍጠር አገሮችን አያዳከመው በእጅ አዙር የሚቆጣጠሩበት ዘዴ ሆኖ አግኝተውታል፡፡
ዜጎቻችን እንደወትሮው የትውልድ ቦታችውን ወለጋ፥ ጎጃም፣ ሸዋ፣ ባሌ፤ ከፋ፣ ትግሬ ወይም በምሥራቅ፣ ሰሜን፣… ወዘተ እና የጋራ አገራቸውን ኢትዮጵያ ብቻ በማለት ቢታወቁበት እና የፈለጉትን ቋንቋ ቢናገሩ ከልዩነታችን ይልቅ አንድነታችን ጎልቶና ጠቃሚ ሆኖ ኅብረታችንን ስለሚያጠናከር፤ ሰው-ሠራሽና ተፈሯዊ የጋራ ጠላቶቻችንን በቀላሉ ለማሸነፍ ከመቻላችንም በላይ ዲሞክራሲንና ፍትሕን ለማስፈን በልማትም ከዓለም ወደኃላ የሚያስቀሩንና ወገኖቻችንን ለስደት የሚዳርጉ ሁኔታዎችን ለማስወገድ የተሻለ አማራጭ ስለመሆኑ ትክክለኛ ፈዴራሊዝምን በሥራ ላይ ካዋሉ አግሮች እድገት መረዳት ይቻላል። ስለሆነም፣ ለሕዝቦች የጋራ እና የእኩልነት፣ እድገት፣ ብልፅግናና ማኅበራዊ ግንኙነት እውነተኛ ወደሚሉት ፊዴራሊዝም ለመምጣት የሚታሰብ ከሆነ አገርን በመልክ-አምድር /ጂኦግራፊያ/ አቀማመጥ ላይ ባማከለ ሥልት ማዋቀር እንጂ ተስማምተው ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦችን በዘርና ቋንቋ ከፋፍሎ በማለያየት አይደለም፤ ሕዝቦች ሁሉ ተባብረው ዲሞክራሲያዊና ፍትሐዊ መንግሥት እንዲፈጠር በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፖርቲዎች በጋራ የአገር ጉዳይ ላይ መተባበር ነው የሚያስፈልጋቸው፤ በትግል ወቅት በጋራ የአገር ጉዳዮች ላይ መተባበር ያልቻሉ ፖርቲዎች የፌዴራላዊ ፅንሰ-ሐሳብን ተከትለናል ለማለት አይችሉም፤ ምክንያቱም ሊያስተባብራቸው በሚገባ የጋራ ትግል ላይ ያልተባበሩ ፖርቲዎች የዕድል ጉዳይ ሆኖ በእውነተኛ ፊዴራሊዝም የሚሳተፉበት ሁኔታ ቢያጋጥማቸው እንኳ ተግባራዊ የማድረግ ልምዱም ብቃቱም ስለማይኖራቸው ነው። በትግሉ ወቅት ሕዝቦችን በእኩልነት የማያይ ፖርቲ ሥልጣን ላይ ሲወጣ ቀድሞ ያላሳየውን ባህርይ ከየት ሊያመጣ እንደሚችል አሳማኝ አይደለም።
ከላይ የተጠቁሱት ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆኖ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በአንድነት የሚያይ ወገን የአዲስ አበባን መስፋፋት አንደችግር እይመለከትም፡፡ ስለዚህ ጥያቂያችሁ ወደትክክለኛ ፊዴራሊዝም እንዲያመራ ፖርቲያችሁ በዘር ሳይሆን በጂኦግራፊ፤ ወይም ዘርና፤ ሃይማኖትና ቋንቋን በማይለያይ አገር-አቀፋዊ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ቢሆን ሕዝቦች ሳይለያዩ የተሻለ ልማት፤ ፍትሐዊ አመራር እና ኅብረት ሊያመጡ የሚችሉ መሪዎችን በመምረጥ ላይ ብቻ ያተኩራሉ። ብሔርተኛነት ሕዝቦችን ያራርቃል፤ እርስበርስ መተማመንን ያጠፋል፡፡ ነገር ግን ሕዝቦች ሲተባበሩ የጋራ ችግራቸውን በጋራ ማስወገድ ስለሚችሉ ዲሞክራሲ እውን ለማድረግ የተመቻቸ ይሆናል፤ ሰላም ይፈጠራል፤ አገርም ትበለጽጋለች።
በትሐት የሚመራውና የአሻንጉሊቶች ጥምረት የሆነው ኢሕአዴግ እንደሆነ እንኳን መሬት ማካለል፣ የማከራየትም፤ የመሽጥም፤ የመስጠትም ተግባር ፈጽሟል፤ እንኳን መሬት ዛፍ አስቆርጦ ሽጧል፤ የአገር ሀብት የሆነን የወርቅ ማዕድን ሽጧል፤ የሚጠቅመው ሆኖ ካገኘው በ24 ሰዓት ውስጥ የፈለገውን ሕግ ያወጣል፤ ለሕግ ተገዥ አይደለም፤ ከሕግ በላይ እንጂ። ሕዝቦቻችንና የሕዝብ ድርጅቶች እስካልተባበሩ ድረስ እየተከሠተ ያለው ጥፋት ይቀጥላል። ለየብቻችን ስንሮጥም የምናገለግለው ያው ጨቅኙን ሥርዓት ነው። ፈዴራል የሚባሉ ክልሎች ስማዊ /symbolical /እንጂ እውነተኛ ፈዴራል ስለአይደሉ ጥያቄ የቀረበበት ጉዳይ የበሽታው ምልክት ላይ እንጂ በበሽታው በራሱ ላይ ስላልሆነ ችግሩ ትክክለኛ መንግሥት የማምጣቱ ጉዳይ ነው። በአንድ በኩል በዘር ላይ የተመሠረተን አከላለል ተቀብሎ የከፋፋዩን እና ጨዋታ እየተጫወቱ በሌላ በኩል ፍትሕ ተጥሷል ማለት ለአንበሳ ጊደር ሰጥቶ ከአንበሳው ቁራጭ ሥጋ እንደመቀላወጥ ነው። ስለዚህ ድካማችሁ ውጤታማ እንዲሆን ትግላችሁ ሕዝቦችን ያማከለ ከብሔርተኛነት ነፃ የሆነ ፕሮግራም ቢቀይስ እና ዋናው ችግር ላይ ቢያተኩር ይመረጣል። በስሜት ተነሣስቶ የእሳት እራት እየሆነ ያለው ወጣት እና ሕዝብ በዓላማም በስልትም ሕዝባችንን ሁሉ ከአስከፊው የጭቆና ሥርዓት ለማስወገድ የዚህ ወይም የዚያ ክልል ሳይል ኢትዮጵያን ከዳር እስከዳር ነፃ ለማውጣት ለጋራ ዓላማ ከማናቸውም ፍትሕ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ጎን መሰለፍ ይገባዋል።
I think people from any corner can raise their demands. However, it is up to peoples’ parties to work together and coordinate people’s causes and make alliance. Otherwise, opposing forces can fight each other, which scenario can be favored by the dictator Weyane; because, that is why they used divide and rule policy on racial orientation in the first place. That is why they used ethnic bound states in the country. Yes, we need to wake up!
Ejoolee Oromoo tookumaanan jabaanu. Wayaaneen albaatee. Icci goolati awaaltu malee inrafiini. Sabni hukaamee Ethiopia hunduu siiwajiin jiiraa. Repuliqii Ethiopia tookuumaadhanan indhabnaa.
aw Bekele Gerba aterf bay , aguday honu eko
Bekele Gerba yefeta!! belo Amara endalchohe
Amara egrachin lay wedko yeqerta yeteyeq belew arefut
Agonbiso behed Mogn yemesla begu!! ale yagere sew !!
eyetestewale !!!!
your time is up, banda.
please all Ethiopians should have united
Mr. Tefera,
it is not a good time now to criticize oppositions, unless you are woyane. If you think for the future of Ethiopia please support these struggle to get rid of Woyane.I am sure Ethiopia will be better off when woyane is gone. Oromo’s are not anti Ethiopia as you may think. They have sacrificed their lives for this country; Abdisa Aga, Jagama Kello, Demisse Bulto, Teferi Banti, Balcha Safo (Aba Nefso),…..Oromos need justice, fairness, freedom in Ethiopia. So, if you are struggling justice, democracy, freedom, please support the struggle. Woyane should go away first. Don’t block the struggle by any means.
beamharana be oromo mekakel slalew neger balebitochu kuch belew meweyayet mechal alebachew begls mknyatum yeoromo Nesa awchi Onegna onegawiyanm honu ke hwehat tekorkumew betekawaminet yekomu beglS yenegerun sle amharaw erasu bchaka kuch blew sidoltu ena lezerochachew yemechnal yemilutn karta awttew begara amharaw telatachn mililik krstiyan eyale oromon chefchfal bemalet teketayochachewn 25 amet oromiya yeoromo merit nech hlmachn oromiya yemtbal ager nech eyalu sisebku norewal endewm ende Dr.merara gudina , bekele gerba, bekele nega yalu ethiopiya yemtbal ager ketefelegech eyalu bekrbu hwehat yametalachewn ena amharawn yeasiwoch sreat nafaki eyalu agerun yenetekutn behayl endikebel ena ewnet lemadreg oromowoch ende asefaferachn bzu nen yerasachn tewekay yasfelgenal silu neber tyakiw zari yeoromo temariwoch benezih hayloch dgaf yemetaw sreat ewneteNa menged yzo saymeta zer bemegdel zer bematfat ager kakefafele mengst mn ytebekal ? amharam hone lilaw gabilaw sumaliw betera betera tekefaflo techefchfal agerun tenetkal zari zoro beterachew oromo oromo slehone mechefchef tejemere yh ende enssa eyagadelu lemegzat mannetn matfat kemalem ahunm yhn sreat degefn snayew yemnfelgewn alaregem blachu yanu lemedgem sayhon yeseratu meseret beatekalay tkit hayloch legara tkmachew silu yametut bemehonu telati yeaSiwoch sreat endimeta yfelgal yemtlutn amharam manager alebachu yeasiwoch sereat yeferesew beshabiya,behwehat, beOneg, alneberem sreat ferese malet hzb agerun masrekeb alebet malet new amharaw mannetun ena ageru ende oromo weym tgri ayawkm malet new? ethiopiya le ethiopiyanoch kalhonech tbetates dl le ethiopiya hzboch
@ ato Tefera Dinberu,
I read your article. I disagree with your divisive approach to the Addis Abeba master plan progect regected by the oromo people. Your criticism of Bekele Gerba’s opinion is biased and baseless. Bekele is an honest and true ethiopian nationalst who demonstrated practically in defending the right of all ethiopians.Your accuzation ONLY shows how you are maneuvering to create division between oromos and amharas. Bekele is more ethiopian than the ethiopians. But his short coming is he was born Oromo. Few people like you who have a mission from wuyane will never accept him. Is it Bekele who stabilshed ethinic based federalism in ethiopia? No, it is wuyane that Dinberu is serving. Can wuyane be trusted? So why you accused the oposition of the master plan is “not the expanssion of Addis but not trusting the fed. Gov’t” you said in your first paragraph. The fed. Gov’t = wuyane.
In your oposition to the Oromo language you mentioned America as an example. Why you forgot Canada, or swuzerland who are using more than one language officially.
Your main problem is not the oromo political agenda. Your problem is the name oromo itself. You will die with this illness. There is no cure for hatred. But oromos will continue for freedom and democracy in ethiopia. We did not start with your advice and we will not stop with the order from you.
Freedom and democracy prevails !!
One thing that should be known is that we follow principles. We are not supposed to support an idea simply because we know the personality that produced the idea. I support the human rights of Bekele Gerba; however, I must criticize when his party makes a mistake. That is what democracy is all about. Tefera is saying that we should not fight in the battle field that the racist Weyane regime has devised it against us 25 years ago. If you guys did not realize that Weyane exists at the expense of our division (ethnic based parties be it Amara, Oromo, Sidama, Wolaiyta, etc. and the satellites of EPRDF like OPDO and others), then you are 25 years back in the history of Weyane and need to learn more. No educated and rational minded politician that claims to support democracy and equal rights of the people of a country should want to repeat Bantustanism, Balkanization, or apartheid rule and see an Ethiopian Slobodan Milosevic or Radovan Karadzic. You need to know what narrow nationalism is. Narrow nationalism is an obstacle to democracy and human rights of the peoples of the country; because we need to integrate rather than disintegrate to be strong and prosperous like many developed nations in the World. Can you imagine of a United States of Ethiopia? If I say of East Africa, it might be an illusion for narrow nationalists that cannot think beyond their nose. Why do you want to limit yourself on Oromyia while the whole Ethiopia is yours? If you are not a narrow nationalist, I think you did not develop the confidence in the power the people and still inherently believe that Haileselassie will rise from his grave and rule Ethiopia !?!
If you want to know what band means, try to study the history of Meles (Legesse) and his father, Zena. Spitting words is simply hatred and not politics. Do you need to graduate from college in order to know that equality means respecting all peoples irrespective of their racial origin? Do you know that there is nothing wrong in being an Oromo, Amara, Tigre, Wolyita, Sidama, etc.? If you say yes, then you accept that we do not need any of these people to be oppressed by anybody including by a dictator from their own race. This is the principle human rights.
a banda is a traitor that sells one’s country to an enemy. Who saved Ethiopia for us and who made deals with Italians, Sudanese, Egyptians, and others? Think like a 21st century person, not like a primitive tribal person.
To Nigussie Getachew
Thank you my friend; we are together. I support that Weyane should go and Ethiopians from all walks of life should struggle hand in hand to eradicate it. You are right; Abidisa Aga, Demisie Bulto, Teferi Benti, Jagama Kello, Balcha Abba Nefso, Taitu Bitul, and many other Oromo brothers and sisters have sacrificed themselves in saving our common country from colonizers along with other Ethiopian patriots. We respect these forefathers and mothers. When we struggled for the downfall of Haileselassie and Mengistu, we did not see our own advantages. We had a vision of seeing a future Ethiopia where all its peoples eradicate all types of oppression, where no more discrimination on the basis of race, language, religion, and other creeds could exist. We had a dream that individual rights would be respected and justice to prevail as people would be the authority over the country. We believed that faith should be an individual affair and Ethiopia our common country. We believe that all languages are equal in serving their speakers, but among 80 of them, there must be one or two official languages.
However, today we found out that our struggle was hijacked by Weyane. What saddens us is to see that grandsons and granddaughters of those patriots mentioned above serve Weyane. The simple formula that Weyane created for itself can be seen as follows:
TPLF = OPDO X ANDM X TPLF XDRPFM
AMARA X OROMO X Nationalities in S. Ethiopia = TPLF (Weyane)
If you can analytically see the equation, Oromo eliminates Oromo, Amara eliminates Amara, and Southern Nations & Nationalities eliminate their own forces. The 8 or 9 states created in Ethiopia are designed on racial/ethnic/ basis to serve the purpose of Weyane as many nationalities are designed to race against neighboring nationalities and Ethiopia to be eliminated, leaving an expanded grater Tigray.
Politics based on racial hatred and vengeance will not take us anywhere. Nobody should be accused of the sins of one’s grandparents. We should leave things for history and look forward in order to build our country in all aspects of life. We should see the past in order to improvements or corrections. Gragn Mohammed tried to create a united Ethiopia in his own way. Emperor Yohannes tried his own way to create a united Ethiopia. Abba Jiffar tried his own way. But jealousy prevailed seeing that Menelik succeeded. If Abba Jiffar was successful, Ethiopia would have been the same. If other leaders were successful, Ethiopia would have been still Ethiopia, because no past leader liked to tear the country but to build. What happened to this generation? A generation that is cheated by filling its tummy? Why does a politician limit oneself within the boundary of a river instead of the whole country?
One should understand that nobody can benefit alone from being a citizen of a great country, but all citizens. Why do we see ourselves down and look up developed nations? Because we cannot forecast. We cannot see beyond our nose. How come that we hesitate to build the country of our forefathers?
You can read my past articles that are professionally prepared and criticize me or any other personality base on facts and rational thoughts.
Lastly, we should learn from our African father, Nelson Mandela who was successful to mediate between the past and the present by calculating the future. I hope you understand that.
God bless you my brother !
For those of us who believe in God, the bible says that humanity decided to build a gigantic tower as a symbol of their power, to make a name for themselves, the Tower of Babel, believing that they can reach the heavens; so, God was angry due to their arrogance and separated their languages. (Genesis 11:4). He created Adam and Eve and all of us are their children’s children’s…children. However, as Cain killed Abel, we still sin forgetting to be brothers and sisters and kill each other on the basis of language differences.