ሊባኖስ በቤይሩት የቦምብ ጥቃት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አዋልኩ አለች::

 #BeirutAttacks : ሊባኖስ በቤይሩት የቦምብ ጥቃት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አዋልኩ አለች::

የሊባኖስ የጸጥታ ሃይሎች በቤይሩት የቦምብ ጥቃት የተሳተፉትን 11 ሰዎች የያዙ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሶሪያውያን መሆናቸውን ተናግረዋል::44 ሰዎችን ለሞት የዳረገው የቤይሩቱ ፍንዳታ ኢላማ ያደረገው ሆስፒታል መሆኑ ታውቋል::የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው ሰባቱ ሶሪያውያን ሁለት ደሞ ከሊባኖስ ሲሆኑ ሌሎች ይፋ አልተደረጉም:;ጥቃቱ የደረሰው የሂዝቦላ ይዞታ በሆነው አከባቢ ሲሆን ሂዝቦላ ከሩሲያ እና ኢራን ጋር በመሆን አይሲስን በማጥቃት ላይ የሚገኝ በሊባኖስ ያለ ድርጅት ሲሆን ጥቃት ፈጻሚዎችን ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር በ48 ሰአት ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጸዋል::

በቤይሩት የደረሱት ፍንዳታዎች አይሲስ የፈጸማቸው ሂዝቦላን ለመበቀል ሲሆን በኢራን የሚደገፈው እና የሺያዎች ድርጅት የሆነው ሂዝቦላ በሶሪያ ስጥ አይሲስ ላይ የሚደረገውን ዘመቻ በመደገፍ በሊባኖስ ድንበሮች እና በሶሪያ ድንበሮች አከባቢ ጸረ አይሲስ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል::የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ጥቃቱን የፈጸሙት ሶሪያውያን በፍልስጤሞች ስደተኞች ካምፕ ተጠግተው የሚገኙ ሲሆን ጥቃቱን አቅደው እና ተዘጋጅተው የፈጸሙት መነሻቸው በቤይሩት ምስራቃዊ ግዛት አሽራፊህ ከተባለው ተነስተው እንደሆነ ገልጿል::

ሙሉ መረጃው እዚህ ላይ ይገኛል::

Lebanon arrests 11 people over Beirut Attacks,mostly Syrians.