መምህር ግርማ ወንድሙ በ50 ሺህ ዋስትና አስይዘው ከእስር ቤት እንዲወጡ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ!!
በማጭበርበር ወንጀል በሚል ሰበብ በእስር ቤት የነበሩት መምህር ግርማ ወንድሙ በፍርድ ቤቱ ቴዛዝ በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ተደርጓል::መምህር ግርማ ከውጪ ሃገር ሲገቡ አዲስ አበባ አየር ማረፊያ ተይዘው ውወደ ማእከላዊ ተወስደው የነበር ሲሆን ፖሊስ ሁለት ጊዜ ፍርድ ቤት አቅርቧቸው ዋስትና ተከልክለው ነበር::ፖሊስ ቤታቸውን የበረበረ ሲሆን በርካታ ዶክመንቶችን እና ንብረቶችን ወስዷል::በዛሬው እለት ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቃቸው ሲሆን የደጋፊዎቻቸው ጫና ለዋስትና በሩን ከፍቷል::መምህር ግርማ ወንድሙ ዛሬ የዋስትና መብት ያገኙት መጄመሪያ በተከሰሱበት ጉዳይ ብቻ ሲሆን ሁለታኛው በጠቅላይ ቤተክህነት በኩል ለተከሰሱበት ገና አስከ ህዳር ሶስት በእስር ይቆያሉ።ምንአልባትም ሌላ የገንዘብ ዋስትና ሊጠየቁ ይችላሉ። ለጊዜው ግን አልተፈቱም እስር ቤት ናቸው ። 
