ብአዴን የህወሃት የአማርኛ ዲፓርትመንት እንጅ የአማራ ውክልና የለውም!!
የብአዴን በደም የጎፈየ በዓል Gashaw Mersha
በሽግግር መንግሥቱ ውሥጥ አማራ ለምን ተወካይ እንዳይኖረው ሆነ?? የሚል ጥያቄ የቀረበለት መለሥ ዜናዊ “አማራው በውሥጡ አልፈን ሥለመጣን ችግሩን ሁሉ ሥለተረዳንለት ተወካይ እያሥፈልገውም” የሚል ቀልድ ነበር የመለሠው!! በእርግጥ ያለ አማራው ውክልና የተመሠረተው የሽግግር መንግሥት ለአማራ ህዝብ የቄጠማ ምርኩዝ ነበር የሆነው። ይህ ጉዳይ ያሣሠባቸው የቀዶ ህክምናው ሊቀ ጠበብት አሥራት ወልደየሥ ከመሠሎቻቸው ጋር በመሆን ነፍሥ አድኑን መአህድን አቋቋሙ። ውክልና አልባው አማራም በፍጥነት በመአህድ ጥላ ሥር ተሠባሠበ። ይህ የአማራ መሠባሠብ ደግሞ ለጸረ አማራ አራማጁ ህወሃት የሞት ድግሥ ሆኖ ተሠማው፣ ሥለዚህ በፍጥነት መአህድን የሚውጥለት ዘንዶ ማበጀት ነበረበት። በዚህ ቀመር የተፈጠረው ብአዴን (በነገራችን ላይ ኢህዴን በመለሥ ዜናዊ ቀጭን ትዕዛዝ ወደ ብአዴን ሲለወጥ የፓርቲው አባላትና የተወሠኑት አመራሮች እንደ ማንኛውም ሠው በራድዮ ነበር የሠሙት) ያልኖረበትን በኣሉን አክብሩልኝ እያለ ነው።
.
አማራው በተቆረጠበት የሞት ፍርድ ከአርባጉጉ እሥከ ሀረር፣ ከጉራፈርዳ እሥከ ጋምቤላ፣ ከጎንደር እሥከ ቤንሻንጉል ድረሥ በደም አዙሪት ሲታመሥ፣ ዘመነኞች ሲያሣድዱት አንድም ቃል ትንፍሽ ብሎ የማያውቀው ይልቁንሥ አመራሮቹ ዘሩ እንዳይበቅል አድርገው ሲሠድቡት እና ሲያሸማቅቁት አበጀህ ሲል የከረመው ብአዴን 35 አመት ሆኖኛልና እልልልል… በቅምጤ በሉልኝ እያለን ይገኛል። መቸም በዚህ 25 አመት ውሥጥ በአማራ ህዝብ ላይ ያልተቀለደ ነገር የለም። ብአዴንም የዚህን የከረመ ቀልድ ተከታይ ክፍል ነው ሊጫዎት የሚፈልገው።
.
እሥቲ አሁን አማራውን በምን መመዘኛ ነው የብአዴንን 35 አመት የሚያከብረው?? ታምራት ላይኔ ይሄን ነፍጠኛ በለው ብሎ ሶማሌዎችን ለሠበከው፣ እነ እንድሪያሥ እሽቴ በሚሊዮን አማራዎች ሥም የኤርትራን ህዝብ ይቅርታ ለጠየቁበት፣ እነ ደመቀ መኮንን በፊርማቸው ቆርሠው ለባዕድ ለሠጡት ያባቶቹ ርሥት፣ እነ አለምነው መኮንን ልጋጋም በባዶ እግር የሚሄድ ብለው ለሠደቡት፤ ለየትኛው ውለታው ነው ብአዴን ከበሮ የሚደለቅለት?? ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ደብረ ብርሃን ለፈሠሠውና ፍትህ ላጣው ደሙ??.
.
ብአዴን ሆይ ስትፈጠር ጀምሮ አማራን ለማዳከም እንጅ የአማራ ውክልና እንደሌለህ ታውቃለህና በድህነት የደቀቀውን ህዝቤን ልቀቅ!! ስለ አንተ የአሽከርነት ዘመንም አማራው ጉዳዩ አይደለምና ለድግሥህ ንሴብህ የሚልበት ሞራል የለውም። በመጨረሻም በደም የጎፈየውን ታሪካችሁን የምታሥተካክሉበት የንሥሃ ዘመን ላይ መሆናችሁን እንድታሥቡ እሻለሁ። ይህ ካልሆነ ግን የአማራ ህዝብ እናንተን የሚሸከምበት ትክሻው መዛሉን ልትረዱ ይገባል።
.
.
ብአዴን የህወሃት የአማርኛ ዲፓርትመንት እንጅ የአማራ ውክልና የለውም!!