ከዶልፊን ከውሻ ከፍየል ጋር ጋብቻ የፈፀሙ የዓለማችን 5 ሰዎች

1. ከዶልፊን ጋር ጋብቻ የፈፀመችው ሚሊኒየር እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 2005 ላይ ሻሮን ቴደለር የተባለችው የእንግሊዝ ሚሊኒየር ኪንዲ ከተባለው ዶልፊን ጋር ትዳር መመስረቷን ለዓለም ይፋ አደረገች። ይህች የ41 ዓመት ሚሊኒየር የእስራኤል ዝርያ ካለው ዶልፊን ጋር ጋብቻዋን የፈፀመችው ዶልፊኑ የሚኖርበትን ሪዞርት በጎበኘችበት ወቅትነበር። ቴድለር በዓመት ሁለት ሶስቴ ወደ ሪዞርቱ በተደጋጋሚ በማምራት ዶልፊኑን ከጎበኘች በኋላ ፍቅራቸውን በትዳር ቋጭተውታል። ያም ሆኖ ግን ኪንዲ በዲሴምበር 18 ቀን 2006 ህይወቱ በማለፉ በባህር ውስጥ ተቀብሯል።

2. ከውሻ ጋር ጋብቻ የፈፀመ ህንዳዊ የ18 ዓመቱ ህንዳዊ ሴልቫ ኩማር ግብረ ስጋ ግንኙነት ሲፈፅሙ ያያቸውን ሁለት ውሾች ዛፍ ላይ ሰቅሎ ህይወታቸው እንዲያልፍ አደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ኩማር የተለያዩ መከራዎች ደረሱበት። ሁለቱም እጆቹ እና እግሮቹ ፓራላይዝ ሆኑ፤ አንድ ጆሮውም መስማት አቆመ። በዚህ መልኩ ለ15 ዓመታት ሲሰቃይ ከቆየ በኋላ ከዚህ ስቃይህ የምትፈወሰው ከውሻ ጋር ጋብቻ ስትፈፅም ነው ሲሉም አዋቂዎች አማከሩት። በዚህም ምክንያት በጥቅምት 2007 የ10 ዓመት እድሜ ካላት ሲልቪ ከተባች ውሻ ጋር ጋብቻ ፈፀመ።
3. ከውሻ ጋር ጋብቻ የፈፀመች ጋናዊት ጋናዊቷ ኢሚሊ ማቡ በ2009 ካሳደገችው ውሻዋ ጋር ጋብቻ መፈፀሟን ይፋ አደረገች። የ29 ዓመቷ ማቡ ውሻዋን ለማግባት የወሰነችው ውሻዋ የአባቷን ባህሪይ ተላብሶ ስላገኘችው መሆኑንም ተናግራለች። “በህይወት ዘመኔ የአባቴን ባህሪይ ያለው የህይወት አጋር እንዲሰጠኝ ስፀልይ
ነበር። ከበርካታ ወንዶች ጋር ግንኙነት ነበረኝ። ነገር ግን ሁሉም ተመሳሳይ ባህሪይ ነው ያላቸው። ቀሚስ ተከታይ እና አታላዮች ናቸው። ውሻዬ ግን ልክ አባቴ ለእናቴ ተማኝ እና አክባሪ እንደነበረው እርሱም ለኔ ታማኝ ነው። ለኔም ትልቅ ክብር አለው” ብላለች። ጋብቻውን የማቡ ቤተሰቦች ቢቃወሙትም የከተማዋ ቄሶች እና
ሌሎች ግን ጋብቻውን አድምቀውታል።

4. ከፍየል ጋር ጋብቻ የፈፀመው ሱዳናዊ በጥር 2006 ቻርልስ ቶምቢ የተባለው ሱዳናዊ ከአንዲት ፍየል ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ሲያደርግ በመያዙ ፍየሏን እንዲያገባት ተገዷል። ቶምቢ ፍየሏን ከማግባቱ በተጨማሪም ለፍየሏ ባለቤት 75 ዶላር እንዲከፍል ተደርጓል።
5. የ75 ዓመቱ ኔፓላዊ ከውሻ ጋር ተጋብተዋል የ75 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው ኔፓላዊ በሀገሪቱ ልማዳዊ ድርጊት መሰረት ከአንዲት ውሻ ጋር በ2004 ጋብቻ ፈፅመዋል። እኚህ ኔፓላዊ ጋብቻውን የፈፀሙት ታራ በተባለው ህበረሰብ ልማድ መሰረት ጥርሶቹን ሙሉ በሙሉ የነቀለ ሽማግሌ ረጅም እድሜ ለመኖር ውሻ ማግባት አለበት
ስለሚባል ነው። ነገር ግን ጋብቻው ከተፈፀመ ሶስት ቀናት በኋላ ሽማግሌው ህይወታቸው አልፏል።

ምንጭ፡ሰንደቅ ጋዜጣ