ሃብታሙ ኣያሌው ኣብረሃ ደስታ የሺዋስ ኣሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው።
በኣብራሃ ደስታ፣ ሃብታሙ ኣያሌው፣ የሺዋስ ኣሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ክስ ላይ ዛሬ 03/02/2008 ዓ/ም የተሰየመው የጠቅላይ ፍርድቤት ችሎት ለጥቅምት 17 /2/ 2008ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።
የፍርድቤቱ ውሎ ከጉንበት ሰባት የተባለ ኣሸባሪ ቡድን ግንኙነት ፈጥራቹሃል የሚል ክስ ሲሆን ሲሆን የኣብራሃ ደስታ በልዩ ሁኔታ ከዴምህት ግንኙነት ነበረህ የሚል እንደዋና ክስ ሆኖ በኣቃቢ ህግ ቀርበዋል።
ዴምህት ከኢህኣዴግ ጋር የሚሰራና እስካሁን በኣሸባሪነት ያልተፈረጀ እንደሆነ ይታወቃል። ኢህኣዴግ እኮ ኣያፍርም ሞላ ኣስገዶምና ኣብረውት የመጡት የኢህኣዴግ ምልምል ሰላዮች እንደ ምስክር ሊጠቀምባቸው ይፈልግ ይሆናል።
ጠቅላይ ፍርድቤቱ በዛሬው ውሎው ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ጨርሷል።
