እንዘጋጅ! የስራ ካላንደራችንን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ እንረባረብ! ድምጻችን ይሰማ!

የስራ ካላንደራችንን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ እንረባረብ!

1/ ማክሰኞ መስከረም 11/2008 ለዳያስፖራው ማህበረሰብ የዲፕሎማሲያዊ ጫና ጥሪ ይደረጋል!

2/ ረቡእ መስከረም 12/2008 የውድ ኮሚቴዎቻችን የመልካም ምኞት መግለጫ እና ጥቅል መልእክት ይፋ ይሆናል!

3/ አርብ መስከረም 14/2008 የወረቀት ገንዘብ ግራፊቲ ስራ እንጀምራለን! ካሁን ቀደም ትብብር መንፈግ ላይ ትኩረት ያደረጉ ስራዎችን ስንሰራ መቆየታችን ይታወቃል፡፡

ዝርዝር አፈጻጻሙን አስመልክቶ በአላህ ፈቃድ የፊታችን ጁሙዓ የምንለው ይኖረናል፡፡

የተጠቀሱት ስራዎች በዚህ ሳምንት ቢጀመሩም ተከታታይ ስራ እና ርብርብ የሚጠይቁ በመሆናቸው ሁላችንም ላልደረሳቸው በማዳረስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ እንጠባበቅ ዘንድ አደራ እንላለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ብሄራዊ ጭቆናን አንቀበልም!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምጻችን ይሰማ!

አላሁ አክበር!