የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ? ? Girma Getachew
የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጓል።ከአንድ ቀን በፊት የነገረ ኢትዮጵያ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ወጣት በላይ ማናዬ ስለ ጠቅላላ ጉባኤው አጭር አስተያየት ሰጠ።
“1. አማራ የለም የሚል ይዘት ያለው ንግግር ከሊቀመንበሩ ላይሰማ ይችላል ብየ አስባለሁ
2. ኦሮሚያ ክልል ላይ በስፋት (በኦሮምኛ) ፕሮግራሙን ያስተዋውቃል ብየ እጠብቃለሁ
3. ማደራጀት ላይ በትኩረት ይሰራል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ
4. ከሌሎች ፓርቲዎች (ከመድረክ) ጋር የበለጠ አብሮ ይሰራል ብየም እጠብቃለሁ
እና….ብዙ ስራ ይጠብቀዋል! “
ነበር የጻፈው።
” ከሌሎች ፓርቲዎች (ከመድረክ) ጋር የበለጠ አብሮ ይሰራል ብየም እጠብቃለሁ እና….ብዙ ስራ ይጠብቀዋል!” ይሄ ከሆነ ማለፊያ ነው። ስልም እኔ ምላሽ ሰጠሁኝ
ጠቅላላ ጉባኤው ተደርገ። አቶ ይልቃል ጌትነት ብቸኛ እጩ ሆኖ ቀረበ። ሌላ እጩ የቀረበ አልነበረም። በኋላ “እጩማ መቅረብ አለበት። ዴሞክራሲያዊ አሰራር እንዳለን ማሳየት አለብን…” ተብሎ ነው መሰለኝ ጠቅላላ ጉባኤው አቶ ዮናታን ተስፋዬ እንዲወዳደር ጠየቀ። አቶ ዮናታን አስቀድሞ አቶ ይልቃልን እንደሚመርጥ በይፋ አስታዉቆ ነበር። ” You got what it takes Yilkal Getnet and you deserve more than a second term! ፡” ሲል ነበር የጦመረው።
ታዲያ ይልቃል መመረጥ አለበት ሲል የነበረ ሰው፣ ከይልቃል ጋር ተፎካካሪ ሆኖ ለመወዳደር መቅረቡ ነገሩን ድራማ አያሰኘውም፡? አቶ ዮናታን ለመወዳደር ያላሰበና ያልተዘጋጀ ሰው ነው። የርሱ “መወዳደር” አቶ ይልቃል ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ተደርጎ የተመረጠ ነው ለማስባል በሞከረ መልኩ፣ አስቂኝ ድራማ ተሰርቶ፣ አቶ ይልቃል ተመረጥኩ ብሎ ብቅ አለ። (ወያኔዎች ተመረጥን ለማለት የቁጩ ምርጫ እንዳደረጉት ማለት ነው)
አቶ ይልቃልን ከማንገስ ዉጭ ግን ከሰማያዊ ጠቅላላ ጉባኤ የተሰማ ነገር የለም። ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ በጠቅላላው ጉባኤ ስለጠበቃቸው አራት ነጥቦች ላይ የሰማነው ነገር የለም። የጠቅላላ ጉባኤውን ዉሳኔ አላነበብንም። የአመራሩ አባላቱ እንደዉም በሌሎች ከሰማያዊ ጋር በማይገናኙ ሐሳቦ ሲጦምሩ ነው የምናነባቸው። ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብሮ ስለመስራትና ስለመተባበር ጠቅላላ ጉባኤው ምን ወሰነ ? የሚታወቅ ነገር የለም። የብሄረሰብ መብት ጉዳይ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ እንደ ትልቅ ጥያቄ ነው የሚወሰደው። በዚያ ዙሪያ የሰማያዊም ፕሮግራም ለማሻሻል፣ የብሄረሰብ መብቶች እንደሚከበሩ የሚያረጋግጥ የአንቀጾች መስተካከል ይኖር ዘንድ ምን እንደተደረገ የሚታወቅ ነገር የለም።
ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰቦች አገር ናት። እርግጥ ነው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተወለዱ፣ በማንነታቸውና በኢትዮጵዩዊነታቸው ብቻ የሚያምኑ አሉ። አንዱም እኔ ነኝ። በሰሜን ጎንደር አብዛኛው ከትግሬዎች ጋር የተደባለቀ ነው። በሸዋ ኦሮሞና አማራ የተደባለቀ ነው። ነጭና ጥቁር ብሎ ነገር የለም። ህዝቡ ተዋልዷል፣ ተዛምዷል። ሆኖም ለምሳሌ 97% አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ በሚኖርበት በቀለም ወለጋ ፣ ወይንም በዉቁሮ፣ ትግራይ፣ ወይም በደጋ ሃቡር ሶማሌ ክልል ..በመሳሰሉት የሚኖሩ ፣ ብዙ ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ያልተቀላቀሉ፣ ማንነታቸውን በሄረሰባቸው የሚገልጹ ኢትዮጵያዉያን አሉ። ለነርሱ የብሄርሰብ መብቶች ትልቅ ጥያቄዎች ናቸው። እነርሱ ለምን እንደኛ አላሰቡም ብሎ፣ ግትር አቋም መያዝ ስህተት ነው። እነርሱ ከሌሎች በምን መልኩ ያልተናነሱ፣ እንደዉ ሊበልጡ የሚችሉ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። በዚህ ረገድ የሰማያዊ ጠቅላላ ጉባኤ ምን ማሻሻያዎችን አደረገ ? የሚታወቅ ነገር የለም።
የሰማያዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከመደረጉ በፊት፣ በርካታ የአንድነት ሰዎች ፣ ሰማያዊ ሴንትሪስት አቋም እንዲወስድ ሲጠይቁ እንደነበረ አውቃለሁ። ሆኖም አቶ ይልቃል በወሰደው ግትር አቋም ምክንያት ለማሻሻል ፍቃደኛ ሳይሆን እንደቀረ ነው። ሆኖም የአቶ በላይ ማናዬን አስተያየት ያነበብን፣ ምናልባት ማሻሻያዎች ሊደረጉ ይችላሉ የሚል ሐሳብ የያዝንብነት ሁኔትም ነበር። ሆኖም ምንም የተሰማ ነገር የለም። ጭራሻኑ ጋዜጠኛ በላይ፣ ማንንም ለማለት ፈልጎ እንደሆነ ባይገባንም የሚከተለውን ጦምሯል፡
“ስለ ብሄረሰቦች መብት መናገር፣ ስለ ባህልና ቁዋንቁዋ ብዝሃነት ማውራት ከኢትዮጵያዊነት መውረድ ይመስላቸዋል። የብሄረሰብ ማንነትን መካድ የበለጠ ኢትዮጵያዊ መሆን አይደለም። ኦሮሞ ማለት የማይደፍር አንደበት “ኦሮምኛ ተናጋሪ” በማለት ያድበሰብሳል! በአማራነቴ ግፍ ተፈፀመብኝ የሚል ሰው እየየ እያለ “አማራ የሚባል የለም” ይልሃል። እና ምን ለማለት ነው…ማንነትን መካድ የበለጠ ኢትዮጵያዊ መሆን ማለት አይደለም!!