የወያኔን ሰውበላ ስርዓት በማገልገል ላይ ላሉ የሠራዊት አባላት በሙሉ! Adjama Dejene
የወያኔ ደንቆሮ ጀነራሎች የኢትዮጵያን ሠራዊት በሰላም አስከባሪነት ወደ ሶማሌ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳና ሌላም አፍሪካ አገር የሚሄዱት ወታደሮች ከ 1ሺ እስከ 1400 የአሜሪካ ዶላር በወር ከልዩ ጥቅማ ጥቅሞች በተጨማሪ እንደሚከፍል እየታወቀ ነገር ግን የወያኔ ቱባ ጀነራሎች ለወታደሩ የሚከፍሉት እስከ 200 ዶላር እንደሆነና ከዚያ የተረፈው የወያኔ ጀነራሎች ኪስ እንደገባ ነው እናም ወንድሞቻችን እባካችሁ ከእንቅልፋችሁ ንቁ ሌላው ቀርቶ ለምሳሌ በሶማሌና በሌላም ቦታ ወታደሮቻችን ሲሰው አይተናል የተባበሩት መንግስታት ቢያንስ 100ሺ ዶላር የህይወት ካሳ እንደሚከፍል ከነርሱ ጋር አብሮ በአስተርጓሚነት ሄዶ የነበረው የአሁኑ የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኰንን አብሮ መሄዱና ምን እንደተሰሩ ከእርሱ ሰኞ 24/08/2015 በተላለፈው ኢሳት ሬዲዮ ላይ ከ34ኛው ደቂቃ ጀምሮ በአንክሮ ተከታተሉት ይህን ጉድ በምንችለው መንገድ አገር ቤት ይህን ስርዓት በማገልገል ላይ ላሉ የሠራዊቱ አባላት ቤተሰቦቻችን የምናደርስበትን መንገድ ፈልጉ አያችሁ ወገኖች እኔ እድሜየ 57 ነው የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ጊዜ 16 ዓመት ተማሪ ሆኘ ነው ለውጥ የመጣው ያደኩበት የወታደር አካባቢ ስለነበር ብዙ ጀነራሎችን አውቃለሁ እንኩዋን ቪላና ህንፃ ሊገነቡ የመንግስት ቤት ነበር የሚኖሩት፣ በደርግም ትምህርቴን ጨርሸ በቀድሞው ባህር ኃይል ሠራዊት ተቀጥሬ 10 ዓመት ከ10 ወር ከሀዲው ወያኔ በግፍ አገር እስከተቆጣጠረበት ድረስ አገልግያለሁ እናም እኔም የነበርኩበት ክፍልም ሆነ በምድር ጦርና አየር ኃይል የነበሩ ጀነራሎች እንዲህ የተጋነነ ቤት ያላቸው አላውቅም ዘመዴም ጀነራል ነበር እስራኤል፣ አሜሪካ ሄዶ የተማረ ነው ከእብሪተኛው የሲያድ ባሬ የሶማሌ ጦርነት ጀምሮ ለአገሩ ደሙን ያፈሰሰ፣ አጥንቱን የከሰከሰ የኢትዮጵያ የጀግና ኒሻን ተሸላሚ ነው ፖፕላሬ በሚባለው አካባቢ (ሽመልስ ሀብቴ ት/ቤት) አካባቢ በሚገኘው የመንግስት ትንሽ ቤት ውስጥ ነበር የሚኖረው እናም የአሁኖቹ ተደጋግሞ የተገለፀ ነው ከየት አምጥተው ነው ይኸ ሁሉ እናም ከላይ እንደተገለፀው በሰራዊቱ ህይወትና ደም ነግደው ነው፣ በህገ ወጥ ኮንትሮባንድ ንግድ ነው እነዚህ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ሰውንም የሚበሉ ጅቦች ናቸው ታዲያ ወገኔ የአገሬ ሰራዊት ሆይ ለማን ነው የምትሰቃየው? ለነርሱ ስልጣን ማራዘም አንተን ግደል እያሉ አባትህን፣ እናትህን፣ ወንድምህን፣ ልጅህን ሲያስገድሉህ ኖረዋል እናም አይበቃምን??? እነርሱ እየዘረፉ ህንፃ በህንፃ፣ ቪላ በቪላ ሆነዋል ዛሬ 90 ሚሊዮን ወገኖቻችን በከፋ የኑሮ ውድነት የሰቆቃ ኑሮ እየኖሩ ነው የአገሬ ሰራዊት አንተ መሳሪያ ተሸክመህ አገር ሳይሆን እነዚህን ጨካኞች በአንተ ሲነግዱ ወገንህ በረሃብ እየተሰቃየ ከቆሻሻ ምግብ ፍለጋ ሲጋፋ ለህሊናህስ አይሰማህም??? አሁን ደግሞ በቡሃ ላይ ቆረቆር እንደሚባለው ይባስ ብሎ ድርቅ በአገራችን ገብቶ 24 ሚሊዮን ወገናችን በአስከፊ ሁኔታ ላይ ናቸው ስለ ድርቅ ሲነሳ እነ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ካሊፎርኒያና አውስትራሊያ በከባድ ድርቅ እየተሰቃየች ነው እያሉ ያሾፋሉ እናም የኢትዮጵያ ሰራዊት ሆይ ንቃ እስከ መቼ ይነገድብሃል? ሞትህን እንኳን ለቤተሰብህ የማያረዳ የጨካኞች ስብስብ የ21ኛው ክፍለ ዘመኑ አዶልፍ ወያኔን ተሸክመህ እስከመቼ!!!
http://ethsat.com/?p=34116
