የስደትና ሞት ፍርደኛው..! Amdom Gebreslasie
በህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት የትግራይን ህዝብ ለማስተዳደር የሚመጥን ህዝባዊነት፣ ብቃትና ፍላጎት እንደሚያንሰው ባለፉት 24 ዓመታት ታይተዋል።
በተለይ ወጣቱ በኣገሩ ሰርቶ የሚኖርበት ምቹ ሁኔታ ማበጀት እንዳልቻለ ከህዝቡም ተደጋግሞ እየተሰማ ያለው ሓቅ ነው።
ይህ ብሙስና የበሰበሰ ኣቅመቢስ መንግ

ስት ወጣቱ ሃይል በኣገሩ ሰርቶ እንዳይኖር ቆፍድዶው በመያዝ ለስደት እየዳረገው ይገኛል።
የህወሓት መንግስት የወጣቱ ፍልሰት ምክንያት ብሎ ያስቀመጠው “…በኣቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት…” ብሎ ቢሆንም ወጣቱ ግን በኣገሩ ሰርቶ ለመኖር ባለመቻሉና በኣገሩ ቁጭ ብሎ ከመሞት እግሩ ወደ መራው በመሰደድ በሞትና በሂዎት መሃል ሁኖ የሚመርጠው የመጨረሻ እርምጃው ነው።
በፎቶው የምትመለከቱት በራያ እንዳመኾኒ ወረዳ እምባ ሓስቲ ቀበሌ የሚኖሩ 20 ወጣቶች ያደራጁት ማህበር ነው።
ይህ ማህበር መንግስት ለገጠር ወጣቶች የገቢ ምንጭ እንዲሆ
ናቸው ተራራ(ጎቦ መቐሎ) ኣልምተው ሸጠው እንዲጠቀሙበት ተብሎ ከዓመታት በፊት የተሰጣቸው ነው።
እነዚህ 20 ወጣቶች ለዓመታት ያለሙት የባህር ዛፍ ተክል ኣድጎ ሸጠው ሊጠቀሙበት ሲጀምሩ የቀበሌውና የወረዳው ኣስተዳዳሪዎች “…ቦታው የተሰጣቹ በስህተት ነበር ስለዚህ ከነተክሉ ለባለቤቱ መልሱት…” በማለት ከወጣቶቹ በመቀማት ከነሱ በጥቅም ለተያያዘው ሰው “..ሰጥተነዋል..” ተብለው ተቀምተዋል።
ወጣቶቹ ከዓመት በላይ ከቀበሌ እስከ ዞን ኣብየቱታቸው ቢያቀርቡም ሰሚ ሊያገኙ ኣልቻሉም። እነዚህ ወጣቶች ያቋቋሙት ማህበር ዑና ሰፈር የሚል መጠርያ ያለው ሲሆን 4 ወንዶችና 16 ሴት ወጣቶች ያቋቋሙት ነው።
ይህ ግፍ ከደረሰባቸው በሗላ ሁለት ሴቶችና ሁለት ወንዶች ኣማራጭ ኣጥተው እግራቸው ወደ መራቸው ተሰደዋል።
፩) ኣሸናፊ ንጉስና ገብረ ጥጋቡ የዑና ሰፈር ማህበር ኣባላት ሲሆኑ ያለሙት ባህር ዛፍ ለሌላ ግለ ሰው በመሰጠቱ ተቃውመው፣ እስከ ዞን ድ
ረስ ኣቤቱታ ኣቅርበው ሰሚ ባለማግኘታቸው በእምባ ሓስቲ ቀበሌ ህዝብ በተሰበሰበበት ቀርበው “…እኛ በኣገራችን ኣልምተን ለመኖር መንግስት ባወጣው እድል ተጠቅመን ተራራ ኣልምተን ነበር። እናንተ ከቀበሌ እስከ ዞን ያላቹ የመንግስት ኣካላት ተመሳጥራቹ ለዓመታት ያለማነው ሃብታችን ቀምታቹናል። ደስ ይበላቹ ኣገራችን ለቀን እግራችን ወደ መራን ልን

ሰደድ ተገደናል…” ብለው በመናገር ከሁለት ወር በፊት በሱዳን ኣቅጣጫ ተሰደዋል።
ከወራቶች በፊት በኣሸባሪው ኣይኤስ ኣይኤስ 29 ወገኖቻቸው በሊብያ እንደታረዱ እያወቁ፣ በረሃና የኩላሊት ሌቦች መኖራቸው እያወቁ ከሞት ፊትለፊት ገጥመው ተሰድ ደዋል። ኣሁን የደረሱበት ኣልታወቀም።
፪) ሕልፍቲ ሃይለና ኮማዒስ ቅብኣቱ ደግሞ የዑናሰፈር የባህርዛፍ ማሕበር ሴት ኣባላት ነበሩ።
እነዚህ ሴት እህቶቻችን ደግሞ ህወሓት መንግስት ኣብየቱታቸው ሊሰማቸውና ከዘራፊዎች ሊያስጥላቸው ባለመቻሉ ወንድሞቻቸው ለሱዳን ከተሰደዱ ከኣንድ ወር በሗላ በጁቡቲ ወደ የመን በህገወጥ መንገድ ተጉዘው በየመን ተይዘው ወደ ጁቡቲ እንዲመለሱ ከተደረገ በሗላ ምንም ወደ ሌላት ኣገራቸው ላለመመለስ ሌላ እድል ለመጠቀም ከወላጆቻቸው ተጨማሪ ብር እንዲላክላቸው መልእክት ልከዋል።
ወጣቱ የስደትና የሞት ፍ
ርደኛ ያደረገው የህወሓት ስርዓት መያዣና መጨበጫ ያጣ፣ የወገን የዜጎቹ ሞት፣ ውርደት፣ ስደት፣ ስቃይና ሰቆቃ ከመጤፍ የማይቆጥር ጨካኝ ሆነዋል።
ሰሞኑን ከሶማሊ ላንድ እየወጡ ያሉ ዘገባዎ
ች እንደሚያመላክቱት በሺዎች የሚቆጠሩ ተጋሩና ሌሎች ኢትዮዽያውያን በእስር ቤት ታጉረው እየተሰቃዩ እንዳሉ ነው።
እስቲ ወገኖች እነዚህ ወጣቶች ስደትንና ሞትን ኣይናቸው ጨፍነው እየተጋፈጡት ያሉበት ምክንያት ኢህኣዴግ እንደሚለው “..በኣቋራጭ ለመበልፀግ ካላቸው ጉጉት” ነው…?

ሰሞኑ ኣቶ ዳዊት ገብረእግዚኣብሄር የተባሉ
ኢትዮዽያዊ የተናገሩት ተጨባጭ ሃቅ ለመቃወም የሚዳዳቹ የህወሓት ደጋፊዎች ሆይ…!
የህዝባቹ እንባ፣ ሰቆቃ፣ መከራ፣ ስቃይ፣ ስደትና ሞት እንዳታዩ የሸፈናቹ ሰይጣን ምንድ ነው..?
የሃገራችን ወጣቶች፣ ሙሁራና ፖለቲከኞች ከግል ጥቅማቹ ይልቅ የህዝባቹ ችግር ተመልሳቹ ኣስተውሉ። እስቲ ሃሳባቹ ለግሱ።
ነፃነታችን በእጃችን ነው…!
IT IS SO…!