<‹የእረኞች›› ችግር ነው!! (አሌክስ አብርሃም)

ሰሞኑን በአገራችን ‹አንዳንድ አካባቢዎች›በተከሰተው ድርቅ ስለሞቱ ከብቶች ክቡር አቶ ሪድዋንየሰጡት ምላሽ ብሶቴን ቀሰቀሰው ‹‹ከብቶቹ የተጎዱት እረኞቹ በወቅቱ ውሃ ወዳለበት አካባቢ ስላልወሰዷቸው ነው›› ለመሆኑ በሚሊየን የሚቆጠር ኢትዮጲያዊ ማጣፊያው ያጠረው ከላይ ለብሶ ውስጡን ርሃብ የሚሞረሙረው መሪዎቹ በወቅቱ እህል ወዳለበት ቦታ ስላልወሰዱት ነው ብንልስ …..

=====================================================

<‹የእረኞች›› ችግር ነው!! (አሌክስ አብርሃም)
ጋዜጠኛ – ‹‹15 ሚሊየን ኢትዮጲያዊያን ተርበዋል ይባላል እርሰዎ ምን ይላሉ ?››
ማን እንደሆኑ የዘነጋኋቸው መላሽ – ‹‹የተራበውማ ሰማኒያሚሊየን ህዝብ ነው.. 15 ሚሊየኑ ጭራሽ የሚላስ የሚቀመስ ያጣው ነው ››

እና ሰሞኑን በአገራችን ‹አንዳንድ አካባቢዎች›በተከሰተው ድርቅ ስለሞቱ ከብቶች ክቡር አቶ ሪድዋንየሰጡት ምላሽ ብሶቴን ቀሰቀሰው ‹‹ከብቶቹ የተጎዱት እረኞቹ በወቅቱ ውሃ ወዳለበት አካባቢ ስላልወሰዷቸው ነው›› ለመሆኑ በሚሊየን የሚቆጠር ኢትዮጲያዊ ማጣፊያው ያጠረው ከላይ ለብሶ ውስጡን ርሃብ የሚሞረሙረው መሪዎቹ በወቅቱ እህል ወዳለበት ቦታ ስላልወሰዱት ነው ብንልስ …..

ህዝቡ ጀሪካ. አሰልፎ ውሃ የሚጠባበቀው ውሃና ፍሳሽ በወቅቱ ህዝቡን ውሃ ወዳለበት ቦታ ስላልወሰደው ነው ብንልስ …. በመብራት መቆራረጥ ፍዳችንን የምንበላው …
መብራት ሃይል በወቅቱ መብራት ወዳለበት ቦታ ስላልወሰደን ነው ብንልስ ….የስልክ ኔትወርክ የራበን ቴሌ ኔትወርክ ወዳለበት ቦታ ስላልወሰዱት ነው ብንልስ …..
ፍትህ የሚጓተተው የፍትህ አካላት በወቅቱ ወደፍትህ ደጅ ስላላደረሱን ነው ብንልስ ……. ›› እንደው ይሄ ‹‹በወቅቱ ያለማድረስ ነገር›› ከተነሳ አይቀር

አቶ ሪድዋን ህዝቡን እየመሩ ተፈላጊው አገልግሎት ወዳለበት ቦታ ባለማድረሳቸው ለደረሰው ግፍ ሁሉ ‹‹መሪ እረኛ ነው ›› በሚለው መርህ መሰረት እራሳቸውን ጨምሮ
መሪዎችን ፓርቲያቸውንም ይውቀሱልን !! አሁንየተጮኸለት ጭራሽ ለይቶለት ወደሞት አፋፍ የቀረበው ነው እንጅ ብዙ ነገር የተራብነው ሁላችንም ነና !!
ለማንኛውም ዜጎቻችን በእርሃብ በተከበቡበት ሰዓት ያነሳኋቸው ነገሮች ቅንጦት ሊባሉ የሚችሉ ናቸው እንደው በነካካ አፋችን ብየ እንጅ !!

Salim Jibril's photo.