የፖለቲካ ጥላቻ እና የፖለቲካ ምቀኝነት – ለለውጥ እንቅፋት የሆኑ ደንቃራዎች ይወገዱ !!! (ምንሊክ ሳልሳዊ‬)

የፖለቲካ ጥላቻ እና የፖለቲካ ምቀኝነት – ለለውጥ እንቅፋት የሆኑ ደንቃራዎች ይወገዱ !!!
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎Unity‬ ‪#‎Freedom‬ ‪#‎StoppoliticalHate‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi – ጥርስ መንከስ አሊያም በሰዎች የፖለቲካ ብስለት መቃጠል ሲልም እንደ በሽታ እና እብደት በላይ ላይ መደራረብ በፖለቲካ ጥላቻ እና በፖለቲካ ምቀኝነት መንደድ የወያኔዎች አንዱና ከዘረኝነት ጎን ለጎን እየነጎደ የሚሄድ ባህሪያቸው ነው::ተናግሮ ማሳመን ጽፎ ማስደሰት የሕዝብን ልብ መግዛት የሕዝብን ቀልብ መሳብ የኢትዮጵያዊነትን ምርኩዝ መጨበት ይህ እና ተመሳሳይ ሂደቶችን በነወያኔዎች ቤት ከባድ ጥላቻን ይወልዳል ይህን መሰል ሰውም አንድም ለሞት ሲልም ለእስራት ሲያድግም ለዘር መጥፋት ይዳረጋል::ይህ ጉዳይ ግን አንገብጋቢ መሆኑ እየታወቀ በለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ዘንድም ዘርቆ እንዲገባ በመደረግ ላይ ነው::አንንዳንድ ቦታዎችም ላይ ዘልቆ መግባት ብቻ ሳይሆን እየተተገበረ ነው::

ድርጅቶችን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ ማሴር የአንድን ግለሰብ ወይም ቡድን የሃስብ አጀንዳ ከማዳበር/ከማሻሻል ይልቅ ማጣጣል ያልበሰሉ ካድሬዎችንን ለስድብ ማሰማራት እርስ በእርስ የጋራ አጀንዳ ላይ አለመወያየት የጋራ ጠላት መኖሩ እየታወቀ በመቻቻል እና በመመካከር አለመታገል የፖለቲካ ጥላቻዎች የፈጠሩት ደንቃራ የሰራው ትልቅ የትግል እንቅፋት ነው::የትግል ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችንን እና በተመሳሳይ ቡድኖች ውስጥ የሚከሰቱ ፍትጊያዎች በግለሰቦች የመረጃ ፍሰት ላይ የሚፈጠሩ ድንጋጠዎችን ማርገብ እና ማረጋጋት የሚቻለው በሰለጠነ የመፍትሄ መንገድ እንጂ በፖለቲካ ምቀኝነት እና ጥላቻ አይደለም::ምናልባት ለጊዜው የተወሰኑ ያልበሰሉ ስሜታዊ እና ጥቅማዊ ሮቦቶችን ተጠቅሞ የፖለቲካ ጡዘት መፍጠር ይቻል ይሆናል እንጂ ዘላቂነት የለውም::በሕዝብ ዘንድ ታማኝነት ለማግኘት የአንድነት የመመካከር የመከባበር ፖለቲካ በቀናነት በትግሉ ውውስጥ በመከተል የፖለቲካ ጥላቻን ማቆም ያስገድደናል::

ወያኔ ዘረኝነቱን ተመርኩዞ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የበተነው የጥላቻ እና የመጥፎ አስተሳሰብ የምቀኝነት እና የኢ ፍትሃዊ አመለካከት አስተሳሰብ በለውጥ ሃይሎች ትግል ውስጥ ሊወገዱ የሚገባቸው እና ልንታገላቸው የሚገቡ ደንቃራዎች ናቸው::ወያኔ በሚከተለው የጥፋት ፖለቲካ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ጥላቻዎች እና ምቀኝነቶች በሰርጎ ገቦች ተሽሞንምነው በለውጥ ሃይሎች ውስጥ ዘልቀው ገብተው ድርጅቶችን ግለሰቦችን እና የለውጥ ሃይል ቀስቃሽ ሚዲያዎችን ስሞችን በጥላቻ እየበከሉ እንዳይበርዙ እያንዳንዳችን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል::ትግሉን ፈር ለማስያዝ የለውጥ ሃይሎች ከመኮራኮም ይልቅ ለመካከሩ ሊወያዩ እና ብዙ ስጢራዊ ተግባራትን ሊከውኑ ይችላሉ ::ይህ የሚሆነው ደሞ በቀና ፖለቲካ የፖለቲካ ጥላቻ እና የፖለቲካ ምቀኝነት – ለለውጥ እንቅፋት የሆኑ ደንቃራዎችን በፍጥነት አስወግደን ስልጡን ፖለቲካኛ ለመሆን ስንነሳ ብቻ ነው::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬