ዛሬም እንደትላንቱ እንዳይሆን…?! ( አለማየሁ ገላጋይ )

ዛሬም እንደትላንቱ እንዳይሆን...?!

ዛሬም … ?
… ድርቅ ተንጠርብቧል፣ ደግሞ ረሃብ ሊዘንብ? እልቂት ከመሬት ሊፈላ? መፈናቀል ሊያንሰራራ? እዬዬ ሊያስተዳድረን? ዋዬ ሊውጠን?…
ያኔ …
… “አዬ ሰባ – ሰባት ባልተወለድኩኝ፣
እናቴ ከእጄ ላይ ጥሬ ስትቀማኝ” ያልነውን፤
ዛሬም …
… “ሁለት ሺህ ሰባት ባልተወለድኩኝ፣
እናቴ ከእጄ ላይ ጥሬ ስትቀማኝ”ን ልንደግም?
ተፈጥሮ እናትን ከቀማች፤ ከእናት ውስጥ ባላንጣ ከፈጠረች ከዚያ ወዲያ ምን አለ? ለሰውልጅ ምን ተረፈው? ለመኖር ምን አጓጓው? … ልንል?
ዛሬም …?
… በችጋር መጠራሞት፣ መቃተት የትውልድ ፅዋ ሆኖ “ማነህ ባለሳምንት” ልንባል? በባዶ እንቅብ መናቸፍ፣ በወና አቅማዳ መንሳፈፍ … ሊደገም? ስጋችን እንደ እፍየ ገላ ሊያመልጥ፣ አይናችን አጥንታችንን ሰርስሮ ሊሰምጥ? … በእንባ አቀባባይነት፣ በሰቀቀን አደራ አስቀማጭነት ሁለት ትውልድ ልናማክል?…
… ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ “ረሃብና ተስቦ በኢትዮጵያ” በተሰኘ ጥናታቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፡-
“ከታሪካችን ታላላቅ ምዕራፎች አንዱ የሚመሰክረው የኢትዮጵያን የልጆች ደም ጠጥቶ፣ በልጆቿ ሥጋ ዳብሮ፣ የልጆቿ አጥንት የሚረመረምበት መሆኑን ነው፡፡ ገበሬዎቹ ሰለስቱ አጋእዝት ወይም ሰልስቱ አጋንንት፣ ርኀብ፣ በሽታ ገዢዎቻችን ናቸው፡፡”
ዛሬም …
… የገባሪ ልጅ ጭሰኛ ሆነን እኛም ደማችን ለጥማቱ፣ ሥጋችን ለመዳበሩ፣ አጥንታችን ለመረማመጃው ሊውል? ምን ይሉት ዕጣ፣ እንዴት ያለው የዘር በሽታ ይሆን?…
… ከሰባ ሰባቱ ረሃብ በኋላ ስንት ረሃቦች ተግተለተሉ? ሰማኒያ ሁለት፣ ሰማኒያ ሶስት፣ ዘጠና ሁለት፣ ዘጠና ሰባት … አራት የረሃብ ቶርፒዶዎች፤ አገር የነቀነቁ… እንደሽፍታ ተደብቆ አካባቢ የሚያሸብረው ትናንሽ ረሀብ ሳይቆጠር ማለት ነው፡፡ ቶም ፍራክሊን የተሰኘ አሜሪካዊ ስለነዚህ ድብቅ የሽፍታ ባህርይ ያላቸው ርሃቦች እንዲህ ሲል አትቶ ነበር፡- “During the 20 – year period, between 1958 and 1977 about 20% of the country was under famine condition each year.” (በ1958 እና 1977 ዓ.ም መካከል ለሃያ ዓመታት ያህል የአገሪቱ ሃያ ከመቶ አካባቢ በየዓመቱ በረሃብ ይጠቃ ነበር፣) ይልና ከእነዚህ ሃያ ረሃቦች መካከል አንዱ ብቻ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ እንደዳሰሰው ይጠቁማል፡፡ እሱም በ1965 ዓ.ም የተከሰተው ረሃብ ነው። ፍራንክሊን አስራ ዘጠኙ ረሃቦች ከስልሳ አምስቱ ረሃብ በእልቂት አይተናነሱም ነበር ይላቸዋል፡፡
ታዲያ፤ አንዱን ብቻ ምን አገኘው? “ፖለቲካ” ይላል – ፍራንክሊን፡፡ ከአፄ ኃይለሥላሴ ሰማኒያኛ የልደት በዓል ጋር ረሃቡ በመግጠሙ የብሶት ማግለብለቢያ ተደረገ፡፡ ለአንድ ንጉስ ኬክ ትልቅ ነገር ሆኖ ሲቆርሱ የተነሱት ፎቶ አላማውን ስቶ ለአልጋ ነጣቂዎች ፍጆታ ዋለ፡፡
“ረሃብ” እንዲያ ነው ለእኛ፡፡ የፖለቲካ ማርሽ መቀየሪያ፡፡ አፄ መንግሥቱ ኃይለማሪያም  ለጠላቶቻቸው የፕሮፓጋንዳ ግልጋሎት እንደተጠቀሙበት ማለት ነው። አስረኛው የአብዮት በዓል ከሰባሰባቱ ረሃብ ጋር ገጥሞ ሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር ለዊስኪና ለአብረቅራቂ መብራት ተመደበ። ለዚህም ሁለት ሚሊዮን ህዝብ በልዋጭ ለሞት ተዳረገ፡፡
ረሀብ ከነኩት፣ ካንጎዳጎዱት ብዙ ነው። ከዚያ ወጥተን ወደ ሌላ አቅጣጫ እንማትር፡፡ በተንጠረበበው ድርቅ፣ በሚዘንበው የረሃብ ዶፍ መካከል “ብልጭ” የምትል የጥበብ ፀሐይ አለች፡፡ አልፎ አልፎ ቢሆንም ቅሉ፡፡ አንዱ ከቁጭት ሌላው ከህይወት እየጨለፈ የገመምተኛ ሣቅ ያስፈግጋታል፡፡ ፀጋዬ ገብረመድህን ረሃብን የቁጭት ቁጨት አድርጎ በግጥም አፍተልትሎታል፡፡ “ረሀብ ስንት ቀን ይፈጃል?” በሚል።
ረሃብ ቀጠሮ ይሰጣል?
ወይስ ቀን ቆጥሮ ይፈጃል?
“የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል”
ይባላል፣ ድሮም ይባላል
ይዘለዝላል ይከትፋል
ብቻ እስከሚጨርስ ድረስ ሆድ ለሆድ ጊዜ ይሰጣል?
ወተት አንጀት ነጥፎ ሲላብ
ሆድ ዕቃ ደርቆ ሆድ ሲራብ
ተሟጦ አንጀት በአንጀት ሲሳብ …
የጣር ቀጠሮው ስንት ነው
ለሰው ልጅ ሰው ለምንለው
ላይችል ሰጥቶ ለሚያስችለው
ስንት ቀን ነው? ስንት ሌት ነው?
ፀጋዬ የግጥም ሱባኤ ገብቶ ረሃብተኛንና ረሃብን የሆነበት ሥራው ነው፡፡ ድቅድቁ ረሃብ እንደ ድንኳን ሸራ  ተሸንትሮ ለእዝን ጥላ ተካስሟል፡፡ ማዘኛ ዳስ ሆኗል፡፡
የማዕዱ ወዝ ሳታጥጥ
አድባሩ አብዳ ሳትፈረጥጥ
ጥንብ ላይተርፋት ሜዳ  – አይጥ
የቤት ድመት ሳታማምጥ
በእመቤቷ አስከሬን ብካይ
እሷም ዋይ አንጀቷም ዋይ – ዋይ
ውሻም በጌታው ሥጋ ላይ
ቸነፈር በጣለው ሲሳይ
አይ! ….
ረሃብ ሰው ሲዘነጥፍ፣ ከእርሱ ጥበብ ማትረፍ አይበልጥም፡፡ ግን ደግሞ ሲያመልጥም ትርፍ የለውም። እንደውም የአንዳንድ ባለቅኔ ልብ ከሰርግ ቤት ይልቅ ሀዘን ቤት ማሰስ ይቀናዋል፡፡
ዛሬም … ?

3 Comments on “ዛሬም እንደትላንቱ እንዳይሆን…?! ( አለማየሁ ገላጋይ )”

  1. Is the author a CIA agent ?
    Why does he quote ferenjis ?
    Does he know that 50% of Americans would starve to death if not for government aid ?

    The author is one example why diaspora Ethiopians in USA can not be trusted.

    Diaspora is not the same in USA, Europe and South Africa.

    Diaspora Ethiopians who live in South Africa are good and could be trusted to be Ethiopians. That is because the Ethiopian society (i dont mean here TPLF or tribalists) and the South African society share a lot in common, like pan Africanism, anti-imperialism, anti-west, etc. Therefore the Ethiopians there can keep their political views and attitudes. In the West or ferenji lands however to have those views and attitudes is dangerous and expose diaspora Ethiopians to isolation and failure in life. Therefore in order to survive (adir bay) the diaspora Ethiopians there adopt the views and the attitudes of the ferenjis and the West. If you watch ESAT you know what i mean.

    The diaspora in Europe, well it is not as good as the diaspora in South Africa but is better than the diaspora in USA.

    The diaspora in USA (well not all) is the worst because the USA is TPLF’s biggest friend and Ethiopia’s biggest enemy.
    As a result the longer the “Ethiopians” stay in the USA the more they get influenced by the anti-Ethiopian USA society, the more they get corrupted and the bigger the chance that they turn into enemies of Ethiopia.

    USA is a dangerous society for Ethiopians since 1991, that means since the country took control of Ethiopia via TPLF. Ethiopians who voluntarily go to or stay in the USA after 1991 should be viewed as deserters. As we know deserters could be brainwashed by the enemy and used as weapons against their countries of origin. We all can observe a lot such “Ethiopians” among the diaspora in the USA. Many work for the CIA and misinform and mislead Ethiopians. They have infiltrated opposition groups to sabotage the struggle against TPLF,a USA proxy, etc.

  2. ከበላተኛ,ከከዳተኛ,ከዘረኛ,ከሴሰኛ,ከጉረኛ,ከቀማኛ,ከሸረኛ,ከብሄርተኛ,…አምላክ ይጠብቀን!!!

  3. tencoulu ስራ ያጣ መነኩሴ…ስራ ስለሌለህ ዝም ብለህ ትቀደዳለህ:ፈረንጅ አፍቅረህ የከዳችህ ይመስለኛል ሁሌ ፈረንጅን ከመአርዮስ ታደርጋቸዋለህ:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*