ስለዲያስፖራ ስንናገር ትውልድን እናስብ !

ስለዲያስፖራ ስንናገር ትውልድን እናስብ !
#Ethiopia #AddisAdmass #DiasporaDay #MinilikSalsawi #Addisababa
………. ” አንድ ህፃን ልጅ፤ “ወደፊት ምን ለመሆን ታስባለህ?” ተባለ አሉ ዘንድሮ፡፡
ልጁም፤ “ዲያስፖራ!” አለ፡፡ “………….. ////……

በአካል የሠረቀው ሌባ ሲባንን ይኖራል፡፡ በልቡ ስርቆቱን የያዘው የባሰ ሌባ፣ ከሌባ እየተሻረከ ሳይነቃበት ይኖራል፡፡ ይህ የሚሆንበት አገር ለከፍተኛ ጥፋት የተጋለጠ ነው፡፡ ቀና የሚመስለው መንገድ ሁሉ ዕውን ቀና ነወይ? ብሎ መጠየቅ ያባት ነው፡፡ የምንገለገልባቸውን ቃላት እንመርምር።
እንደ “ነፃነት”፣ “አማራጭ” እና “ዕድሎች” ያሉ ቃላት ከሚሰጡት ዕሙናዊ ጥቅም የበለጠ ቀስቃሽ ኃይል አላቸው፡፡ በተግባር ግን ገበያ ቦታ፣ በምርጫ ጊዜ እና በሥራ ቦታ አማራጭ ያለን የሚመስሉን “ሀ” እና “ለ”፤ ሌሎቹን ሆህያት ተትተው የተሰጡን ናቸው፤” ይላል ሮበርት ግሪን፡፡
አንድ መሠረታዊ የገዢዎች መርህ አለ፡-
“የመጨረሻው ምርጥ የማጭበርበሪያ ዘዴ፤ ለባላንጣህ አማራጭ የሰጠኸው ማስመሰል ነው። ያኔ ያንተ ሰለባዎች ጉዳዩን የተቆጣጠሩ እየመሰላቸው አሻንጉሊትህ ይሆናሉ፡፡ ከሁለት እኩይ ነገሮች አንዱን እንዲመርጡ አድርጋቸው፡፡ (Choosing between two evils) ሆኖም ሁለቱም አንተን የሚጠቅሙ እንዲሆኑ ማድረግ ነው ዋናው ጥበብ፡፡” (ሮበርት ግሪን)
አማራጮችን አስፍቶ ያለማየት ድህነት፣ አንዱ የድህነታችን ምንጭ ነው፡፡ ይሄ አንድም ከዕውቀትና አቅም ማነስ፣ አንድም አርቆ የማስተዋል ባህል ከማጣት፣ አንድም ደግሞ በአፍንጫ ሥር ዕይታ ከመወጠር ሊከሰት ይችላል፡፡ ከታጠርንበት አጥር ባሻገር ማየት መልካም ነገር ነው። “ይቺን ያቀድኳትን በስኬት ከተወጣሁ” አመቱን እሰየው ብዬ ጨረስኩ፤” ማለት ሌላ እንዳናይ ሊገድበን የሚችል አካሄድ መሆኑን ልብ እንበል፡፡ በአጭር ርዕይ ታቅበን ጊዜ ያመልጣል፡፡ በጀማ ጉዞ ከጀማው ጋር ከማዝገም በላቀ ንቃተ ህሊና መፈትለክ የሚያሻበት ጊዜ ነው፡፡

ስለዲያስፖራ ስንናገር ትውልድን እናስብ! ዳያስፖራ ማለት፤ አንድ ተሰብስቦ፣ በአንድ ቦታ ተቀምጦ የነበረ ህዝብ ወይም ቋንቋ አሊያም ባህል፤ ሲበተን ወይም ወደሌላ ሲሰራጭ የሚሰጠው መጠሪያ ነው፡፡ አይሁዳውያን ከእሥራኤል ውጪ የተበተኑበትንም ሁኔታ የሚያመላክት ነውም ይላሉ፡፡ እንግዲህ ለኢትዮጵያውያንም እንደዚያው ነው፡፡
ኢትዮጵያ የውጪውን ዓለም ኢትዮጵያውያን መሰብሰቧ ደግ ነገር ነው፡፡ አያያዟ ምን ያህል ከኢኮኖሚዋ፣ ከፖለቲካዋ፣ ከዲፕሎማሲዋና ከባህሏ ጋር መስተጋብር ይኖረዋል? ዳያስፖራውያኑስ ምን ያህል ከልባቸው መጥተዋል? ተስፋቸው፣ ምኞታቸው፣ የሀገር ፍቅር ስሜታቸው ምን ያህል የጠለቀ፣ ምን ያህልስ ከጥቅም ባሻገር አገርና ህዝብን ያግዛል? የሚለው የነገ ጥያቄ ነው፡፡ እግረ መንገዳችንን፤ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን፤ “ሰው ሆኖ ካሹት (ከፈተጉት) ጥቅም የማይሰጥ የለም” ያለውን ልብ ማለት ይጠቅማል፡፡
እንግዲህ መንገዱ ረጅም ነው፡፡ ከካሬ ሜትር እስከ ልብ ሜትር የሚያለካካ ነው! ማናቸውም ነገር አልጋ በአልጋ አለመሆኑን መገንዘብ ደግ ነው፡፡ ህጋዊውን፣ ቢሮክራሲያዊውንና ሰዋዊውን መንገድ በቀቢፀ – ተስፋ ለማያይ ሰው፣ ሁነኛና ቀና ብርሃን ሊያስተውልበት የሚችል ሁኔታ አለ። በተወሰነ ደረጃ ግን ሂደቱን ሊያሰናክሉ፣ ሊያቀጭጩና ሊያሟሽሹ የሚችሉ እንከኖች ይኖራሉ? ብሎ አለመጠበቅ ቢያንስ የዋህነት ነው፡፡ “ብላ ያለው ተጋግሮ ይጠብቀዋል፤ ተሸከም ያለው ታሥሮ ይጠብቀዋል” የሚለው ተረት መሠረታዊ፣ አገራዊ ፋይዳ የሚኖረው እዚህ ላይ ነው!

Addis Admass newspaper

3 Comments on “ስለዲያስፖራ ስንናገር ትውልድን እናስብ !”

  1. የመጡት 50%ሻብያ
    25%ኦነግ ኦዴድ ነጭ ለባሽ ሢሆኑ ቀሪው የወያኔ ቅጥረኛ ሠባኪዎች በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ባክኖ በሁሉም ሀጉር የሠነጋቸው መሆኑ ይታወቃል ህዝቡን አታወናብዱ የራሡን ሀገር ማልማት ያውቅበታል አፈናውን ፈርቶ ነው እንጂ የፍየል ወጠጤን ዝምብሎ አልዘመረም።

  2. Diaspora is not the same in USA, Europe and South Africa.

    Diaspora Ethiopians who live in South Africa are good and could be trusted to be Ethiopians. That is because the Ethiopian society (i dont mean here TPLF or tribalists) and the South African society share a lot in common, like pan Africanism, anti-imperialism, anti-west, etc. Therefore the Ethiopians there can keep their political views and attitudes. In the West or ferenji lands however to have those views and attitudes is dangerous and expose diaspora Ethiopians to isolation and failure in life. Therefore in order to survive (adir bay) the diaspora Ethiopians there adopt the views and the attitudes of the ferenjis and the West. If you watch ESAT you know what i mean.

    The diaspora in Europe, well it is not as good as the diaspora in South Africa but is better than the diaspora in USA.

    The diaspora in USA (well not all) is the worst because the USA is TPLF’s biggest friend and Ethiopia’s biggest enemy.
    As a result the longer the “Ethiopians” stay in the USA the more they get influenced by the anti-Ethiopian USA society, the more they get corrupted and the bigger the chance that they turn into enemies of Ethiopia.

    USA is a dangerous society for Ethiopians since 1991, that means since the country took control of Ethiopia via TPLF. Ethiopians who voluntarily go to or stay in the USA after 1991 should be viewed adeserters. As we know deserters could be brainwashed by the enemy and used as weapons against their countries of origin. We all can observe a lot such “Ethiopians” among the diaspora in the USA. Many work for the CIA and misinform and mislead Ethiopians. They have infiltrated opposition groups to sabotage the struggle against TPLF,a USA proxy, etc.

  3. tencoulu u are demonrtrating ur selfishness in ur comment!so change or stop commenting due ur mind is contaminating by so hatred

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*