የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ …33ኛው የካንጋሮ ችሎት ቀጠሮ
Minilik Salsawi ከጻፋቸው ጽሁፎች ውጪ አንድም ምስክርም ሆነ ማስረጃ ያልቀረበባቸው ሳይፈቱ በወያኔ እስር ቤት የሚገኙት (አቤል:ናትናኤል :አጥናፍ እና በፍቃዱ )የዞን 9 ጦማሪያን «በጽሑፍ ምክንያት የታሰረ የለም» ብለው በሚናገሩት የአገዛዙ ፍርድ ቤት ዛሬ ረፋድ ላይ ቀርበው ነበር፡፡ባለፈው ለብይን ተቀጥሮ ሆኖም የኦዲዮ ቅጂዎች ወደ ጽሁፍ አልተመለሱም በማለት ሰበብ ለዛሬ የተቀጠረው ችሎት እንደለመደው በቀጠሮ መዝገቡን መልሶታል::
የካንጋሮ ፍ/ቤት ዳኞች በሉ እንደተባሉት ችሎቱ የምስክሮች ቃል ከመዝገቡ ጋር እንደተያያዘ አረጋግጧል። በመሆኑም ለነሐሴ 13 ለብይን ቀጠሮ ሰጥቷል። በተጨማሪ ክሳቸው የተነሳላቸው የ5 ተከሳሾች በኤግዚቢትነት የተያዘ ንብረት እንዲለቀቅ ለፖሊስ ትዕዛዝ ሰጥቷል።«ይህ ችሎት ሃምሌ 30 ሳይሆን እስከ ነሃሴ 15 ቀን በስራ ላይ ይቆያል። በመሆኑም የብይን ቀጠሮው ነሃሴ 13 ላይደርስ ቢችል እንኳ እስከ ነሃሴ 15 የሚታይ ይሆናል ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 30 የሚዘጋ ቢሆንም እስከ ነሀሴ 15 ስለምንሰራ እና ሙሉ ቀን ምስክሮችን የምንሰማ ስለሆነ ቀጠሮውን ከዚህ በላይ ማሳጠር አንችልም» ብለዋል የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ የፖለቲካ ጉዳይ አስፈጻሚ ዳኞች::
