ተረስተናል ያሉ የከምባታ ጠንባሮ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የካቲት ፫(ሦስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የከንባታ ጠንባሮ ህዝብ ባለፉት 23 አመታት  የመሰረተ ልማት አገልግሎት አላገኘም በሚል ከሺ ያላነሱ ነዋሪዎች በተገኙበት በዱራሜ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አድርጓል። የአካባቢው ተወላጆች በራሳቸው ተነሳሽነት ትምህርት ቤቶችን እየሰሩ ፣ የመብራት፣ የመንገዶችና የቴሌኮሚኒኬሽን ዝርጋታ ማካሄዳቸውን ገልጸው፣ መንግስት ምንም ድጋፍ ባለማድረጉ፣ ችግሩ የባሰባቸው ነዋሪዎች እየተሰደዱ መሆኑን ሰልፈኞቹ ገልጸዋል።

ሰልፈኞቹ የደቡብ ክልል ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርገዋል። በሰልፉ ላይ የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ሳይቀሩ መሳተፋቸው ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*