ለመከላከያ ለፖሊስ ሰራዊቶች እና ለደህንነት ክፍሉ ምርጫውን በማሳበብ ስልጠና ሊሰጥ ነው::

የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደተለመደው በጸረ ሰላም እና በጸረ ሕዝብነት በጥብቅ ይፈረጃሉ::
Minilik Salsawi

የወያኔው ጁንታ ስልጣኑን እንዳያጣ እየተፈረካከሰ ባለበት በዚህ ወቅት መጪው ምርጫ ከመድረሱ በፊት አስፈላጊውን ከለላ ለማግኘት ለመከላከያ ለፖሊስ እና ለደህንነት ክፍሉ ምርጫውን ተገን በማድረግ እና በማሳበብ የስልጠና ሰነድ ይዞ በየክፍሉ ካድሬዎችን በማሰራጨት የፓርቲውን አስተሳሰብ ለመጫን ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል::

ስልጠናው ዋናው ነጥብ በመጭው ምርጫ ህዝባዊ አመጾች የነጻነት እና ይመብት ጥያቄዎች እንዳይይፈነዱ ስጋት ያለብት ወያኔ በሰራዊቱ እና ደህንነቱ ላይ ያለውን ጥርጣሬ ለመቅረፍ እና ለማሳመን ያዘጋጀው ሰነድ እንዲሁን በግሩፕ እየለየ ጠላቱን ለመልቀም ያመቸው ዘንድ ያዘጋጀው መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::

ምንጮቹ የስልጠናውን ሰነድ ጠቅሰው እንደተናገሩት በዋናነት በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ የተዘጋጀ ሲሆን እንደተለመደው በጸረ ሰላም እና በጸረ ህዝብነት ይፈረጃሉ::ድርጅቶቹ ለሃገር አደጋ እንደሆኑ እና ሰራዊቱን ሊበትኑ የተዘጋጁ እንደሆነ ታውቋል:: ምንጮቹ አክለው እንደተናገሩ በሃገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ሰራዊቱን ና የደህንነት ክፍሉን በመረጃ በዝርዝር ማስተማር አለባቸው:: ያሉ ሲሆን የሚያጉረመርሙ የሰራዊቱ እና ደህንነቱ ክፍሎች የለውጡ አካል እንዲሆኑ ከፖለቲካ ድርጅቶቹ ትልቅ ስራ ይጠበቃል ብለዋል::ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሰኝ አቀርባለሁ::