በእስራኤል የወያኔ ቴሌቭዥን የሰራው የሃስት ዘገባ የክስ መዘዝ ለውሳኔ ተቀጠረ::

በአለፈው ዓመት በ­22.11. 2013 የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ፣ በእስራኤል ለሚገኘው የወያኔ ሚዲያ ለ­“IETV” ያመጣው የክስ መዘዝ፣ቀጥሎ ለውሳኔ መቀጠሩ የክሊክ ሃበሻ ዘገባ አመልክቷል::የዛሬ ዓመት ኖቨምበር 22 ቀን 2013 ነበር፤ ቴል አቪቭ ከሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ኢትዮ­ይሁዳያንና ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ዓረቢያ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ፣ ሞተና የሴቶች መደፈር፣ ሰቃይና ሰቆቃ የወያኔ/ኅውሃት ገዥውና እምባገነኑ መንግሥት ችላ ብሎታል ብሎ በመቆርቆርና በመበሳጨት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው እንደነበር የሚታወስ ነው። http://www.clickhabesh.com/?p=105083

Image
ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል አብዛኛዎቹ በልጅነት እድሜ የመጡና ከዚህ የተወለዱ ወጣት የኢተዮጵያ ይሁዳውያን የተሳትፉበት ከመሆኑም ባሻገር፤በዚህ መልኩ በኢምባሲው ጽ/ቤት ፊት ለፊት ወጣት ኢትዮ ይሁዳውያንን አልገብግቦ እንደዚህ ዓይነት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በእሥራኤል ሲካሄድ በዓይነቱ የመጀምሪያ ነበር ቢባል ማገነን አይሆንም። ምክንያቱም ቴል አቪቭ የሚገኘው አምባሳደር ኽላዊ ዮሴፍ የወጣት ኢትዮ ይሁዳውያን በሰልፉ መሳተፋቸው አስደንግጦት፣ እዚሁ እሥራኤል በሚገኘው የአማረኛ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ቀርቦ ከተናገረው፣ በእሥራኤል መንግሥት ሙሉ በሙሉ በሚተዳደረ የአማረኛው ሬዲዮ ጣቢያ የተናገርውን አዳምጡ የሬዲዮውን ቃለ ምልልስ አዳምጡና ንባቡን ቀጥሉ፦

ልብ በሉ፦ በዲሞክራሲና በነጻው ሚዲያ ሃገረ እሥራኤል ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ “የአንድን ወገን ብቻ አቅርቦ” በተደጋጋሚ ማለትም አምባሳደሩንና ደጋፊዎቹን ቃለመጠይቅ ሲያደርግ፣ ቴሌቪዥኑም ሆን ሬዲዮው ከሙያው ህግ ውጭ በመሆን አንድም ቀን የተቃዋሚውን ወገን በጋራም ሆነ በተናጠል ቃለ መጠይቅ አካሂዶ አያውቅም። ህዝቡ በነጻውሚዲያ ሃገር የሁለቱንም ሃሳብ ሳያዳምጥ አንድ ወገን ብቻ ይዞ እንዲጓዝ መደረጉ ያበሳጫቸው ከዚህ ህዝብ አብራክ የወጡ በተናጠል ትግል የጋራ ትግል በማለት ተደራጅተው፣ “መሬት ­

ኢትዮ ­እሥራኤል የሰብዓዊና ነጻነት ድምጽ ምክር ቤት” ብለው ያቋቋሙት የመጅመሪያ ትግላቸው ማተኰር ያለበት በዲሞክራሲና በነጻ ሚዲያ ሃገር የህዝብ ድምጽ የታፈነውን መብተማስጠበቅ መሆኑን እጠቁማለሁ። ይህ የአምባሳደሩ መግለጫ አንዳንድ የዋህ አዛውንቶችን የኢትዮጵያን ህዝብ እያስራበ በሚያስመጣው “ጤፍ” በማታለል ለማሳመን መሞከሩ ነበር። ምክንያቱም የሚያስበው እሥራኤል የሚገኘው ኢትዮ ቤተ እሥራኤላውያን እኛ እንዳዘዝነው ነው ብሎ ያስብ ስለነበር ሳያስበው የደረሰበት የውርደት ካባ የተከናነበበት በመሆኑ ለማስተባበል መሞከሩ ነበር።ስለጤፍ ከአንድ ስብሰባ ላይ የተናገረውን ተመልከቱ፦ይህን ያህል ለመንደርደሪያ ካልኩ ዘንዳ፣ ወደ ዋናው ሃሳብ ልንደርደር።

ምንም እንኳ ዓርብ ቀን ድምጻውያን እንድሚሉት “….ዓርብ ዓርብ ይሸበራል እየሩሳሌም!” ያለ ምክንያት አይደለም። ዓርብ ህዝበ እሥራኤላውያን ለ 26 ስዓታት ሰንበትን የሚቀበሉበት ቀን ስለሆነ፤ ሁሉም ነገር ከመዘጋጋቱ በፊት ማልደው በመገዛዛት ሲያበስሉና ቤታቸውን ሁሉ ሲያጸዱ ከዋሉ በኋላ ሁሉም ቤተሰብ ሰውነቱን ታጥቦ ጽዓዳ በመልበስ ወደ ጸሎት ቤት ሄደው ሲመለሱ፣ ሰንበት ከመግባቱ በፊት ያበሳስሥሰሉትን፣ መላው ቤተሰብ በአንድ የጠረጴ ዙሪያ በመቀመጥ እየበሉና ወይናቸውን እየተጡ አምላካቸውን የሚያመሰግኑብት ቀን ሲሆን፤ የህዝብ ማመላለሻዎች፤ ሱቆች፤ መ/ቤቶች፤ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ማንኛውም በሙሉ ዓርብ ከስዓት በኋላ ከቀኑ 14፡00 ማለት 02፡00ስዓት (በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር ከቀኑ 08፡00 መሆኑ ነው) ይዘጋል።

ሆኖም ግን በዚህ ቀን የቤተሰብ ኃላፊነት ያላቸው ሌሎች በእድሜ ትንሽ ከፍ ያሉ ቢኖሩም፤ አንዲት ወጣት ቤተ እሥራኤል ከገጠሪቱ ኢትዮጵያወደ እሥራኤል በ­8 ዓመት ዕድሜዋ፤ ኅውሃት አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ ከሁለት ቀን በፊት “ዘመቻ ሰሎሞን” (Operation Solomon) በተባለውየመጣች፤ አሁን የ 31 ዓመት ወጣት፤ በፌስ ቡክ ያተላለፈውን በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን መከራና ሥቃይ ችግርና ስቆቃ ተመልክታ “ለወገን ደራሽ ወገን ነው!” ብላ፤ ልጆቿን ዛሬ የ­7 እና የ­የ­5 ዓመት ዕድሜ፡(ባለፈው ዓመት የ­6 እና የ­4 ዓመት) ከወላጆቿ አስጠግታ፤ ከምትኖርበት ከተማከተወሰኑ ጓደኞቿ ጋር በባቡር ተሳፍራ በስዓቱ ከተባለው ቦታ ቴል አቪቭ በመድረስ ከሌሎች ከሰላማዊ ሰልፈኛው ጋር በመሆን፤ በሳዑዲ ዓረብያ ጭካኔ የተጐዱትንና የሞቱትን ኢትዮጵያኖች ፎቶ በማንገብ፤ የኢትዮጵያው መንግሥት ለዜጐቹ ግድ ሳይሰጠው ዝም ማለቱ በጣም ስለአንገበገባት፣ የዲሞክራሲ መብቷን በመጠቀም በጉዳት ላይ ላሉት ወገኖቿ ስትጮህላቸውና ድምጿን ስታሰማ ዋለች፡፡

ታዲያ ከሰላማዊ ሰልፉ አንድ ሳምንት በኋላ (በሳምንቱ ዓርብ) “IETV” በተባለው ቴሌቪዥን ይህችን ወጣት ያልተናገረችወን በኤዲቲንግ የተቀነባበረ ፕሮግራም ቀረበ። (የኢዲቲንግ ዕውቀቱ ወይም ሙያው ያለው አቆራረጡንና አቀጣጠሉን ይረዳል)ይህን ፓርት/ክፍል ተመልከቱ፤ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ “ሰባት” (7 ጊዜ)ይህ ቃል በፕሮግራሙ ተደጋግሟል። ለምን? ተደጋገመ የሚለውን የፍርዱ ሁኔታ ሲያበቃ ከህግ ጠበቃዋና ከወጣቷ ጋር ፈቃደኛ ከሆኑ በቃለ መጠየቅ ከአንደበታቸው እንሰማለን የሚል እምነት አለኝ። እንደ ባለመያ እስኪ የራሴን አስተያየት ጠቆም አድርጌ ልለፍ፤

1ኛ) እንደዚህ ዓይነት ነገር ልጅቱ ከተናገረች፣ መሆን ያለበት ሙሉ ንግግሯን ከነመልኳ ማቅረብግዴታ ነው፤ ከዚያ በኋላ ቋንቋ ልማይረዱ ትክክለኛ ትርጉሙን ማቅረብ የሙያ ግዴታ ነው፣

2ኛ) በጋዜጠኛ ህግናደንብ መሰረት “Sling” ወይም “የመንገድ ቋንቋ” ብሎ ነገር የለም። ለህዝብ መቅረብ ያለበት “እውነተኛና ሃቅ ብቻ እና ሃቁ ብቻ ነው”፤ ምክንያቱምሚዲያ የአንድ ሃገር ህዝብ ጠበቃ ማለት ነው፣ወደ ታሪኩ ልመልሳቸሁ፣ ይህን የተላለፈ ፕሮግራም ያዩ ዘመድ አዝማድና ቤተሰቦቿ ”እንዴት ፋሲል ይገደል ትያለሽ?” “ለምን ልጆችሽን ዝም ብለሽ አታሳድጊም?” እያሉ
ሲያዋክቧት በመደናገጥ በጣም ተረብሻ ወዲያውኑ የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊ የነበሩትን ስታማክር፤ በመጀመሪያ እንድትረጋጋ ከመከሯት በኋላ፡
ፕሮግራሙን በኢንተርኔት በማየት በፍጹም ቃላት የተለቃቀመበት የተቀጣጠለ ስለሆነ፤ ቴሌቪዥኑንና አቅራቢውን “በስም ማጥፋት” የሚያስወነጅል እንደሆነ ገለጹላት። ይህች የ­31 ዓመት ወጣት የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባትና ልጆችዋን ብቻዋን እንደምታሳድግ ስታማክር፤ የተወሰኑ ከተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ የተሳተፉ በመመካከር ወደ­5 የሚሆኑ ገንዘብ በማዋጣት ከፍለውላት“ፒኒ ጌልዓድ” የተባለ የሀግ ጠበቃ እንድትይዝ ሆነ።

በተላለፈው ፕሮግራም ላይ እንዳያችሁት፦የሀግ ጠበቃዋ በህጉ መሰረት ክሱን ጀመረ፣ “IETV” ወዲያውኑ ከኢንተርኔትና ከፌስ ቡክ ላይ ሙሉ ፕሮግራሙን አወረደው፤ ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ፕሮግራሞችን እያወረደ የሚያስቀምጥ የተጠናከረ የወጣቶች ቡድን ቀድሞ ቀድቶ አስቀምጦታል።ክሱ ተጀመረ ብያለሁ፤ እናስ ማለታችሁ አይቀርም፤ እናማ የቴል አቪቭ ወረዳ ፍ/ቤት ዳኛ የከሳሽና ተከሳሽን የህግ ጠበቆችን ቃል ከሰማ በኋላ፤ እንደ እሥራኤል ህግና ደንብ መሰረት የሚቻል ከሆነ ሁለቱ የከሳሽ የህግ ጠበቃና የተከሳሽ የሀግ ጠበቃ በጋራ ተስማምተው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ ለሆነ የሀግ ጠበቃ ሁኔታውን በመካከላቸው ሁና ከህግ አንጻር እንድታሸማግል “Court Mediators” ዘንድ ተላኩ። እዚያ መስማማት ባለመቻላቸውም በአለፈው ኦጐስት/ነሃሴ 2014 ወረዳው ፍ/ቤት ቀርብው ነበር።

ታዲያማ የተከሳሽ ጠበቃ ለዳኛው በ”ይፋ” ከሳሾችና ተከሳሾች በተገኙበት(በ”ይፋ” የሚለው ይሰመርበት) በመከራከሪያነት የተጠቀመው (የ“IETV” የህግ ጠበቃ በሂብሪው የተናገረውን ቃል በሂብሪውና በእንግሊዝኛ ላስቀምጠው) በሂብሩ የተጠቀመው ቃል “להבהיר” (Apologize) ከማለቱም በተጨማሪ፤ ከሳሿ ፈቃደኛ ከሆነች በዚያው ቃለ መጠይቅ ልናደርግላት እንችላለን ሲል የመከላከያ መልሱን አቅርቧል። የወጣቷ የህግ ጠበቃ ግን በወጣቷ ማህበራዊ ህይዎትም ሆነ የሥነ ልቦና ላይ ከፍተኛ መረበሽና አለመረጋጋትን ስላስከተለባት፤ ሆን ተብሎ በወጣቷ ላይ የተክናወነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ስለተካሄደ፤ ለድርጊቱ “IETV” ይቅርታ ከመጠየቅም ባሻገር የሥነ ልቦና ጉዳት ካሳና የህግ ጠበቃዋን ወጭ ሊከፍል ይገባዋል ሲል መልስ ሰጥቷል።

ዳኛውም ወጣቷን ተከሳሾቹ በሚሉት ትስማማ አትስማማ እንደሆን ተጠይቃ፤ በ­“IETV” ምን ዓይነት ቃለ ምልልስ እንደማትሰጥና፣ ይህ ቴሌዥን በህይወቴ ላይ ከፍተኛ የሆነ መጥፎ አሻራ ያጣለባት መሆኑንና፤ የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ከተለያዩ ክፍሎች የደረሳት መሆኑንም ለፍ/ቤቱ አስረድታለች። ፍ/ቤቱም ለ­19.01.2015 ቀጥሯል። ችሎቱ ክፍት ስለሆነ ማንም ሰው የዲሞክራሲ መብቱን ተጠቅሞ መገኘት ይችላል። ቦታው ቴል አቪቭ ወረዳ ፍ/ቤት ነው፤ “ቫይጽማን ጎዳና 1 ­ ቴል አቪቭ“ ትክክለኛውን ስዓትና ቀን ቀኑ ሲቃረብ እናሳውቃለን። ለወገን ደራሽ ወገን ነው ብላ ድምጿን ለማሰማት ወጥታ ሥነ ልቦናዊ ድቀት ለደረሰባት ወጣት እህታችን፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ያለበት ሃገር ያለሽ በመሆንሽ ሁላችንም መልካሙን ሁሉ እንመኝልሻለን!!
ሐና መከተ – ጋዜጠኛ እሥራኤል