በህዳር 23 በኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ የተከፈተው የሽብር ድርጊት ፈፃሚነት ክስ ብይን ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል::

ይህ ቀን በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት በመንግስት አቃቤ ህግ በኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ የተከፈተውን የሽብር ድርጊት ፈፃሚነት ክስ የመጨረሻ ብይን የሚሠጥበት ቀን ነው፡፡
በዚህ ቀን ፍርድ ቤቱ ሲመለከት የቆየውን አቃቤ ህጉ ያቀረበውን መረጃ በማየት ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች በቀረበባቸው የሽብር ድርጊት ፈፃሚነት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው አግኝቻቸዋለው በመሆኑም እራሳቸውን ይከላከሉ አልያም ደግሞ ጥፋተኛ ሆነው አላገኘዋቸውም በማለት በነፃ እንዲሰናበቱ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች የሽብር ክስ ተምስርቶብን ከ አንድ አመት በላይ በእስር ቤት ስቃይ ላይ እያሳለፍን ብንገኝም ለቆምንለት አላማ ግን ፍፁም በፅናት ላይ እንገኛለን፡፡
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የህዝብ ወኪሎች ናቸው፡፡ ኮሚቴው ማለት ኢትዬጰያውያን ሙስሊሞች ማለት ነው፡፡ ህጋዊ የሆነ ውክልና ያላቸው በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ የሚገኙ የኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች አንድ አካል ናቸው፡፤
ህዳር 23 የሚበየነወ የጥፋተኝነት ብይን በኮሚቴው ላይ ሳይሆን በኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ ነው፡ ለዚህም ነው ህዳር 23 በኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ በሽብር ድርጊት ፈፃሚነት የቀረበው ክስ ብይን የሰጥበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምንገልጸው፡፡
ኮሚቴውን እና ህዝብን ፈፅሞ መለየት አይቻልም፡፡ ለቀሩት 10 ቀናቶች የኮሚቴዎቻችን የፍርድ ሂደት ሳይሆን መባል ያለበት የኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች የፍርድ ሂደት መባል እንደሚኖርበት እሙን ነው፡፡
በመሆኑም ኮሚቴው ማለት የኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ማለት በመሆኑ በዚህ ክስ አንተም፣እኔም፣ አንቺም፣እነሱም መወንጀላችን በመገንዘብ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት የሚሰጠው ብይን በሁሉም ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ፍትህ ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!!
BY:- ABU DAWD OSMAN