ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ደቡብ አፍሪካውያን ለነፃነት አባታቸውና ለቀድሞ መሪያቸው ለኔልሰን ማንዴላ ሀዘናቸውን ለመግለጽ ወደ ጁሀንስበርግበና ሶዌቶ እየተሰበሰቡ ሲሆን፤ ታላላቅ የዓለማችን መሪዎችና ታዋቂ ሰዎችም በማንዴላ ሞት ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው። በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን በስዌቶ በሚገኘው በቀድሞው የኔልሰን ማንዴላ መኖሪያ ቤት በመሰባሰብ በባህላዊ ስርአታቸው መሰረት በልዩ ልዩ የብሔረሰቦች የሀዘን ጭፈራ  ለመሪያቸው ያላቸውን አክብሮች እየገለፁ …

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ መፍቴ አጥቶ እንደቀጠለ ባለበት ወቅት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን የአነጋግረናቸው የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል። በዛሬው እለት በርካታ የአገር ሽማግሌዎች የጸጥታ ሀይሎች እያደረሱባቸውን ያለውን ስቃይ ለማስታወቅ በጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጽህፈት ቤትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢገኙም የሚያነጋግራቸው አጥተው ተመልሰዋል። አገር ሽማግሌዎቹ …

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ የሚገኙ መምህራን ፣ መንግስት ለአባይ ግድብ በማለት ያለፈቃዳቸው የቆረጠባቸውን ደሞዝ በአስቸኳይ ካልመለሰ ሰኞ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። መምህራኑ ዛሬ ወርሀዊ ደሞዛቸውን ለመቀበል ወደ ባንክ ሲሄዱ ለአባይ ግድብ በሚል ደሞዛቸው ተቆርጦ ተሰጥቷቸዋል። በሁኔታው የተበሳጩት መምህራን ወደ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሲያመሩ መስተዳድሩ ያዘዘው በመሆኑ ምንም …

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅድመ መደበኛ ት/ቤት ገብተው መማር ከሚገባቸው እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ሀፃናት ውስጥ 23 በመቶዎቹ ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው ሰነድ ያስረዳል። ከ1ኛ አስከ 4ኛ ክፍል ድረስ የትምህርት ገበታቸው ላይ የተገኙ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የሚያሳያየው ሰነዱ፣ከ5ኛ አስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ገብተው መማር የነበረባቸው ተማሪዎች   ቁጥር አነስተኛ መሆኑንም  …

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የላችሁም በሚል ከሳዑዲዓረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ቁጥሩ መንግስት አስቀድሞ ካሰበው እጅግ አሻቅቧል፡፡ በዚህ ም ምክንያት ተመላሾቹን ለመቀበልና ለማቋቋም  መንግስት በቂ በጀት አለመያዙ እንደ አገር አሳፋሪ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ መንግስት የተመላሾቹ ቁጥር 23 ሺ ገደማ መሆኑንና እነዚህም …

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በሚል የጅጅጋ ከተማ በፌደራል ፖሊስ  አባላት መወረሯን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማውን ከተቆጣጠሩት በሁዋላ ልዩ ፖሊስ እየተባሉ የሚጠሩት ሀይሎችን ወደ ዳር የገፉዋቸው ሲሆን፣ ፖሊሶቹ በየተወሰኑ ሜትሮች ቁጥጥር እያደረጉ ነው። የጸጥታ ጥበቃው በሄሊኮፕተር ላይ በሚደረግ ቅኝት የታጀበ ሲሆን፣ በየ አቅጣጫውም በዙ 23 እና …

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመርካቶ በተለምዶ ጆንያ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትላንት ከቀትር በኃላ የደረሰውን የእሳት አደጋ በወቅቱ ከመቆጣጠር ይልቅ ጉቦ ለማግኘት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በድርድር ጊዜ በማጥፋታቸው ንብረታችንን እንድናጣ አድርጎናል ያሉ ነጋዴዎች የአዲስአበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲን ለመክሰስ መወሰናቸውን አስታወቁ፡፡ ከተጎጂ ነጋዴዎች መካከል አንዱ የሆኑት ለአዲስ አበባው ዘጋቢ …

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ተሀድሶ አልወሰዱም በሚሉና በተለያዩ ሰበቦች የጡረታ መብታቸው ላልተከበረላቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት፣ የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር መንግስት ጥሪ ማቅረቡ ታውቋል። የመንግስት ሹሞች የቀድሞ ወተዳሮቹን  ፎርም እንዲሞሉ እያደረጉዋቸው መሆኑን አንዳንድ ወታደሮች ለኢሳት ገልጸዋል። መንግስት በአሁኑ ጊዜ ይህን እርምጃ ለምን ለመውሰድ እንደፈለገ አልታወቀም። ለጉዳዩ  ቅርበት ያላቸው ሰዎች …

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአደጋው 40 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የአደጋው መንስኤም ከአቅም በላይ ጭነት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። በጭልጋ ወረዳ ደግሞ አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ መኪና ተገልብጦ ተሽከርካሪዎች ለመተላላፍ ባለማቻላቸው መቸገራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። መኪናው ነዳጅ እንደጫነ በመገልበጡ እሳት ይፈጠራል የሚል ስጋት ማሳደሩን የአካባቢው ሰዎች ግልጸዋል።

ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ወር ጀምሮ ህጋዊ ወረቀት የላቸውም በሚል የውጭ ዜጎችን ማባረር የቀጠለችው ሳውድ አረቢያ፣ ከአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ትችት ቢደርስባትም፣ ዜጎችን ማስወጣት እንደምትቀጥል አስታውቃለች። አረብ ኒውስ እስካሁን በተወሰደው እርምጃ 126 ሺ ሰዎች ከአገሪቱ መውጣታቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ 90 ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መግባታቸውን ገልጸዋል። አረብ ኒውስ አንድ ባለስልጣንን …

ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በደብረማርቆስ ከተማ ተደርጎ በነበረው የህዝብ ስብሰባ ላይ ነርካታ ነጋዴዎች በታክስ መማረራቸውን ገልጸዋል። መቶ አለቃ ስመኝ መኩሪያው እንዳሉት መንግስትን አክብረን በቫት ብንገባም በአንድ አነስተኛ የንግድ ሱቅ በየወሩ እስከ 73 ሺ ብር ተጠይቀን ፤ መንቀሳቀስ አልቻልንም የምንነግደውን ሊወርሰን የሚሽከረከረው መንግስት  ሚዛኑ የሚጥልብን ግብር አስመርሮናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “የምንሰራውን ስራ በማቋረጥ …

ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦንብ ተራና እና ጆንያ ተራ የሚባሉት አካባቢዎች ዛሬ ቀን ላይ በከፍተኛ የእሳት አደጋ የተጠቁ ሲሆን የከተማዋ የእሳት አደጋ በጊዜው ባለመድረሱም በነዋሪዎች ከፍኛ ተወቅሷል። የመስተዳድሩ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግኑኝነት ሰራተኛ አቶ ንጋቱ ማሞ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረው ጥሪው የደረሳቸው አደጋው ከደረሰ ከ45 ደቂቃ በሁዋላ መሆኑን ተናግረዋል። …

ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች በስልክ እየሰጡ ባለው አስተያየት  ግንቦት7 ከኢህአዴግ ጋር መነጋገሩን አይደግፉም። አብዛኞቹ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ “ኢህአዴግ ተዳክሟል፣ ኢህአዴግ የሚታመን ድርጅት አይደለም” የሚሉ ናቸው። በዚህ ዙሪያ ኢትዮጵያውያን የሰጡት አስተያየት የሚከተለውን ይመስላል በሌላ በኩል ደግሞ የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን የድርድሩ ዜና መልካም ወሬ መሆኑን ለኢሳት በላኩት የኢሜል መልክት አስታውቀዋል። …

ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጅጅጋ በማንኛውም ሰአት ዜጎች ቤታቸው በጸጥታ ሀይሎች ይፈታሻል። የጸጥታ ሀይሎችም ከሞባይል ስልክ ጀምሮ እስከ ላፕቶፕ እንዲሁም ገንዘብ ይወስዳሉ። የቀበሌ መታወቂያዎችን ሳይዙ ከሄዱ ደግሞ ተጠርጥረው ይያዛሉ። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጅጅጋ ለኢትዮጵያውያን ከሳውድ አረቢያ በላይ የስቃይ መሬት ሆናለች ። አንድንድ ምንጮች እንደሚሉት ችግሩን የተወሳሰበ ያደረገው አልሸባብ  በጅጅጋው ፕሬዝዳንት የግል ሞባይል …

ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በከንባታ ጠንባሮ ዞን በዱራሜ ከተማ ገበያ ላይ በተነሳው ተቃውሞ አንድ ታዳጊ ሲገደል ሁለት ፖሊሶች ደግሞ ቆስለዋል። በርካታ ገበያተኞችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። ግጭቱ የደረሰው የከተማው ግብር ሰብሳቢዎች አነስተኛ ነጋዴዎች ቡና መሸጥ እንዲያቆሙ ማስገደዳቸውን ተከትሎ ነው። አርሶአደሮች የተወሰኑ ኪሎ ቡናዎችን ወደ ገበያ በመውሰድ  የመሸጥ የዘመናት ልማድ ያላቸው ሲሆን፣ የከተማው …

ህዳር ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደገለጹት ኢህአዴግ የእንደራደር ጥያቄውን በሁሉት ወር ጊዜ ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ ማቅረቡ ነው። ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢሳት ላቀረበው ጥያቄ በሰጠው የጽሁፍ መልስ “የእንደራደር” ጥያቄ እንደቀረበለት አምኖ፣ “ይሁን እንጅ ንቅናቄው በዋናነት  ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም” ያደረገው ነው ብሎአል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውም …

ህዳር ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው መግለጫ የሳውዲ የጸጥታ ሀይሎችና የሳውዲ ዜጎች በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሀይል እርምጃ በመውስድ ጉዳት አድርሰዋል። በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የሳውድ አረቢያ መንግስት አስፈላጊውን  ምርመራ በማድረግ በአጥፊዎቹ ላይ ተገቢውን እርምጃ ሊወስድ ይገባል ያለው ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቶሎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ …

ህዳር ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚታየው ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ዜጎች። ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያን በእስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ። ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቀናቸውን ይጠባባቃሉ። የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ ሺ የሚቆጠረውን ስደተኛ ለማስተናገድ የመደበው የሰው ሀይል 40 ብቻ ነው። የሳውድ አረቢያ መንግስት ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ …

ህዳር ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባል እና የኢትዮጵያን የ1997 ምርጫ የታዘቡት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ይህን የተናገሩት አዲስ ስታንዳርድ ለተባለ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ነው። በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የአውሮፓ፣ አፍሪካና ካረቢያን አገሮች የፓርላማ ጉባኤ ላይ የተገኙት ወ/ሮ አና የአምባገነን ምንጭ የሆነው መለስ ዜናዊ ቢሞትም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ለውጥ አለመምጣቱን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ተለውጣለች …

ህዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደገለጹት ስትርሀ እየተባሉ በሚጠሩ የማጎሪያ ካምፖች ውስጥ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ። በውሀ እና በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ እርጉዝ ሴቶች፣ ህጻናትና እናቶች አሁንም የድረሱልን ጥሪያቸውን እያሰሙ ነው። በማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊን ምግብ እና ውሀ ለመግዛት ወጣ ሲሉ እንደሚገደሉ ጓደኞቻቸው የተገደሉባቸው ኢትዮጵያውያን …

ህዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግለሰቡ የተገደለው ባለፈው ሳምንት ሲሆን፣ ገዳዮችም ከመንግስት ጋር ባላቸው ቅራኔ የተነሳ ጫካ የገቡ ሰዎች ናቸው ተብሎአል። ከአካባቢው ነዋሪዎች ባገኘነው መረጃ መሰረት በጅማ ዞን ኪሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው በለጣ ጫካ ውስጥ በመደበቅ አልፎ አልፎ ጥቃት የሚሰነዝሩ የአኮረፉ ነዋሪዎች ቻይናዊውን የገደሉት ፎቶ ግራፍ ለማንሳት በሚሞክረበት ወቅት ነው። ቻይናዊው …

ህዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ጅጅጋን በማስመልከት በተላለፉ ዜናዎች ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች እንድናደርግ የከተማዋ ነዋሪዎች ጠይቀውናል። ኢሳት በብሄር ብሄረሰቦች በአል ምክንያት የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ እንደተዘጋ አድርጎ ያስተላለፈው ዜና ስህተት ያለበት ሲሆን የተዘጉት የጅጅጋ ነርሲንግ ማሰልጠኛኮሌጅ እና የጅጅጋ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም እንጅ ዩኒቨርስቲው አለመሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። የአቶ መለስ ዜናዊ ሀውልት እንደፈረሰ ተደርጎ በቀረበው …

ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ ተስፋ የቆረጡ ኢትዮጵያውያን መዲናህ ከተባለው መጠለያቸው  ግንብ እየዘለሉ  ወደ ታይባን ዩኒቨርስቲ ካምፓስ እንደገቡ የአገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል። ብርጋዴር ፋህድ ቢን አሚር አል ጋናም እንደገለጹት 15 ኢትዮጵያውያን ወደ ዩኒቨርስቲው ግቢ የገቡ ሲሆን የጸጥታ ሀይሎች ኢትዮጵያውያኑን በመያዝ ወደ ማጎሪያ ካምፓቸው ልከዋቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በሰዎች፣  በመኪኖች ወይም ህንጻዎች ላይ ጉዳት እንዳላደረሱ …

ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶማሌ ክልል 8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ታከብራለች መባሉን ተከትሎ የክልሉን ዋና መቀመጫ ጅጅጋን  አርቲስቶች እና የመንግስት ባለስልጣናት በየጊዜው እየጎበኙዋት ነው። ለበዓሉ ዝግጅት የተመደበለትን 31 ሚልዩን ብር ከዝግጅቱ በፊት ቀድሞ ያጠናቀቀው የሶማሌ ክልል መንግስትን ለበአሉ ማክበሪያ እና ማድመቂያ በማለት ተጨማሪ 14 ሚሊዮን ብር ጠይቋል። ለበዓሉ ማስተናገጃ የሚሆን ስቴዲየም …

ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአህጉሪቱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ አካል ነው የተባለው ኮሚሽን፣ ኢትዮጵያ ለስኳር ልማት በሚል በታችኛው ኦሞ አካባቢ የሚገኙ ዜጎችን በማፈናቀል እየፈጸመችው ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በፍጥነት እንድታቆም ጠይቆ፣ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚያደርግም ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚኖሩ ብሄረሰቦች ላይ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ግርፋት እና እስራት መፍጠሩን …

ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን  ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር  በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ …

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ከሪያድ ወደ አዲስ አበባ ትሄዳላችሁ ተብለው በመኪኖች የተሳፈሩ ኢትዮጵያውያን እናቶችና ህጻናት በድንገት ጉዞዓቸው መሰረዙን ተከትሎ፣ በርካታ እናቶችና ህጻናት ለከፍተኛ የውሀ ጥም በመዳረጋቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው። እናቶች እና ህጻናት ተስፋ በቆረጠ ስሜት ያለቅሳሉ፤ ማለቃችን ነው ድረሱልን ሲሉ ይማጸናሉ። ህጻናቱና እናቶች አስፋልት ላይ ተበትነው በውሀ ጥም ማለቃቸው …

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው። ኢሳት የሚኒስትሩን  ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት …

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ/ም ለ8ኛ ጊዜ  የሚከበረውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  በዓል  ጋር በተያያዘ የመንግስት ሥራ እና የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዲቋረጥ ከመደረጉም በላይ በከተማዋ በየእለቱ ቤት ለቤትና በጎዳና ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተከናወነ ነው።  በጅጅጋ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ከ3ሺ500 በላይ እንግዶችን ታስተናግዳለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እንግዶቹ ከሚያርፉባቸው ቦታዎች አንዱ የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሰሞኑን ለአንድ ወር ትምህርት …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪያድ የሚታየው ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን። እሁድ  2  ኢትዮጵያን ሴቶች መክረይመንታ ሸባቢያ በሚባል ቦታ ላይ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መገደላቸውን በአይኔ ተመልክቻለሁ ያሉ የሪያድ ነዋሪ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ሌላ ኢትዮጵያዊት ደግሞ በአካባቢው ከተሰማሩት ወታደሮች ጋር ስትነጋገር በብረት ተመትታ መሞቷን እና አንዲት ኢትዮጵያዊትም እንዲሁ የቀኝ እጇ ተቆርጦ በአካባቢያቸው …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ፓርላማ  ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በተቃውሞው ላይ የተገኘችው የኢሳት የደቡብ አፍሪካ ተባባሪ ዘጋቢ ዝናሽ ሀብታሙ እንደገለጸችው በሰልፉ ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ኢትዮጵያውያን ታሰትፈዋል። ተቃውሞውን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ምክትል ሊ/መንበር አቶ ንብረት ጌታሁንም ህዝቡ በተቃውሞው ላይ ተገኝቶ ስሜቱን በከፍተኛ ሁኔታ ገልጿል ብለዋል በተመሳሳይ …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር  እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ  በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ    10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የመንግስት 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል ብሎአል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ኅብረት በዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ የያዘውን አቋም እንዲደግፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ጥያቂያቸውን ለመቀበል አውንታዊ ምላሽ እንደገኙ በመግለጽ አፈጉባኤው ለጋዜጠኞች ቢናገሩም ጉዳዩ ተቀባነት ያገኘው ለውይይት እንጅ ለማጽደቅ አይደለም ተብሎአል። የአፍሪካ የካረቢያንና የፓስፊክ አገራት ፓርላማ 34ኛ መደበኛ ጉባዔ ትላንት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ተማሪ አንተነህ አስፋው የተገደለው በዩኒቨርስቲው የጸጥታ ሀይሎች መሆኑ ታውቋል። ይህን ለመቃወም የወጡ በሺ በሚቆጠሩ ተማሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ከ120 በላይ ተማሪዎች እንደታሰሩ ታውቋል። የተወሰኑ ተማሪዎች ከፉኛ በመደብደባቸው ሆስፒታል ገብተዋል፣ የአንድ ተማሪ ህይወትም በአሳሳቢ ሁኔታ ላኢ እንደሚገኝ ታውቋል።

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታላቁ ሩጫ በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ሥር ሆኖ እሁድ ህዳር 15 ቀን 2006 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ መነሻውን ጃንሜዳ በማድረግ ፥ በ6 ኪሎ አደባባይ ፣ በምኒሊክ ሆስፒታል፣ በቀበና ፣በ አቧሬ ፣ በእንግሊዝ ኤምባሲ ፣ በመገናኛ አደባባይ በማደረግ ተመልሶ ጃንሜዳ የተጠናቀቀው ይህ ለ 13ኛ ጊዜ የተካሄደው ውድድር ከወትሮው በተለየ ጥበቃና የፖሊስ …