ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ባወጣው መግለጫ በቡርጅ ብሄረሰብና በቦረና ህዝብ መካከል ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው መልካም ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጸረ-ሰላም ሃይሎች እየደፈረሰ እንደሚገኝ ገልጿል። ከ2 ሺ በላይ የሆኑ የቡርጅ ብሄረሰብ አባላት ከታህሳስ ወር 2006 ኣም ጀምሮ  ከአካባቢው ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእረፍት ላይ የሚገኙ ነባር የዩኒቨርስቲ  ተማሪዎችን፣ የኮሌጅና የቴክኒክ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን እንዲሁም የዘንድሮውን የሁለተኛ ደረጃ ፈተና አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎችን ስለመጪው ምርጫ እና ስለአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ለማወያየት በየክልሎች ስብሰባ መጠራቱ ታውቋል። ከነሃሴ 10 እስከ ነሃሴ 25 በሚቆየው ሰሚናር ላይ ተማሪዎች ምርጫውን ተከትሎ ስለሚፈጠሩ  ረብሻዎች፣ ስለአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳትና …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአንባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የነበረው ሳምንታዊ መጽሔት ባለቤት  እና የመጽሔቱ ሶስት አዘጋጆች ሀገር ለቀው ተሰደዋል። የመጽሔቱ ባለቤት አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ ለኢሳት እንደገለጸው፤ እርሱና ጋዜጠኞቹ  በስርአቱ ሲደርስባቸው የነበረውን ወከባና አፈና ተቋቁመው የአዲስ ጉዳይ መጽሔትን  ህልውና ለማስቀጠል ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ፤ መጽሔቱዋ  በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍ ያለ ተቀባይነት ከማግኘቷም ባሻገር በገንዘብ አቅምም …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የስኳር፣ የቡናና ዱቄት እጥረት ተፈጥሯል። በዱቄት እጥረት የተነሳ በተለይ በአማራ ክልል ሰዎች ዳቦ ለማግኘት ራጃጅም ሰልፎችን ተሰልፈው ወረፋ ለመተበቅ ተገደዋል። ቡና የመጨረሻ ደረጃ የሚባለው በኪሎ እስከ 100 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ ሁለተኛና አንደኛ ደረጃ የሚባሉትን የቡና አይነቶች ፈልጎ …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፈቃዱ ሃይሌን ጠቅሶ እንደዘገበው ከባቡር ፕሮጀክቱ ጋር የተያያዙትን መንገዶች ከመምራት ጋር የተያያዘ ችግር አለ። ዋና ስራ አስኪያጁ ያለምንም ዝግጅትና እውቀት የአስፋልት መንገድ ይቆራጣሉ፣ በቅንጅትም ለመስራት ፈቃደኞች አልሆኑም በማለት ተናግረው፣ “የባቡር ኮርፖሬሽን ቦርድ አባል ሆኜ እንዲህ የተቸገርኩኝ እዚያ ውስጥ ያልገባ ሰው …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግብጽ ከስልጣን በተወገዱት ሙሀመድ ሙርሲ ዳጋፊዎች ላይ የጸጥታ ሃይሎች  የወሰዱትን እርምጃ የሚዘረዝረውንሪፖርት ይፋ ለማድረግ ካይሮ የተገኙት የሂውማር ራይትስ ወች ዋና ስራ አስኪያጅ ኬኒስ ሮዝና ሌላዋ ከፍተኛ ባለስልጣን ሳራ ሊህ ወደ መጡበት አገር እንዲመለሱ ተደርጓል። ከ1500 በላይ የተገደሉበትን በአንዳንዶች ዘንድ እንደመፈንቅለ መንግስት የሚታየውን ድርጊት ሂውማን ራይትስ ወች በተደጋጋሚ ሲያወግዝ መቆየቱ …

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል። ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል …

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሪታንያ መንግስት የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ትኩረት ሰጥታ እንደትከታተለው የሚያሳስቡ የተቃውሞ ሰልፎች ካለፈው ወር ጀምሮ በእየሳምንቱ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ዛሬ አርብም ለአምስተኛ ጊዜ ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያኑ ስሜታቸውን በከፍተኛ ቁጣ በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከስፍራው ያነጋገርነው ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹ ገልጿል። በሌላ በኩል ደግሞ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ግብረሃይል በውጭ …

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ  የምክር ቤት አባላት ፣” የህዝብ ወኪሎች ብንሆንም ስራ አስፈጻሚው አካል የምናቀርበውን ሪፖርት አይቀበልም” ብለዋል። አንድ ኢንቨስተር ከአንድ የህዝብ ተመራጭ የተሻለ ተሰሚነት አለው ያሉት ተማራጮች መፍትሄ ለማምጣት ካልቻልን የእኛ ተመራጭነት ምንድነው ሲሉ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል የህዝብ ተወካዮቹ እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በፍድር ቤቶች …

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኒው ቪዥን እንደዘገበው አበበ መኮንንና አስፋው ወንዶሰን ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊሶች ተይዘው ተወስደዋል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹንለመያዝ ለሁለት ቀናት አሰሳ ሲያካሂድ እንደነበር ተዘግባል። ኢትዮጵያውያኑ ለኢህአዴግ የደህንነት ሃይሎች ተላልፈው ይሰጡ ወይም ጉዳያቸው በዩጋንዳ ፍርድ ቤት ይታይ በዘገባው አልተጠቀሰም። ፖሊስ እስረኞቹ የታሰሩበትን ቦታም ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም።

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት ሶስት ቀናት ጋብ ብሎ የነበረው የእስራኤልና የፍልስጤማውያን ግጭት እንደገና ማገርሸቱን እስራኤል አስታውቃለች። በግብጽ አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው የሰላም ድርድር ሃማስ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፉን ተከትሎ እስራኤል የአየር ድብደባ ጀምራለች። ሃማስ የሰላም ድርድሩ እስራኤል በጋዛ ላይ ያደረገቸውን ከበባ ማስቆም አለበት የሚል አቋም ይዟል፡፤ እስረኤል በግብጽ በመካሄድ ላይ ያለውን የሰላም ድርድር …

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰነዱ ላይ ኢህአዴግ የአመራር ችግር እንዳጋጠመው፣ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ አለመሳካቱ እንዲሁም በጋምቤላ ተማኝ መሪ መጥፋቱ ተዝርዝሯል። በሃምሌ ወር መጨረሻ የተዘጋጀው ሰነድ ግልባጭ ለጠ/ሚኒስትሩ አማካሪዎች ለአቶ በረከት ስምኦን፣ ለአቶ ደስታውና ለአቶ ኩማ ደመቅሳ ተደርጓል። የቀድሞው ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢህአዴግ የፖሊሲ ስልጠና ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ  ” የኢህአዴግን ተቃዋሚ ሃይላት …

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመቀሌ በሚጽፋው ጽሁፎችና በሚሰጣቸው አስተያየቶች የበርካታ ወጣቶችን ቀልብ የሳበው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር አብርሃ ደስታ፣ በአሸባሪነት ተከሶ መእከላዊ እስር ቤት ከገባ በሁዋላ ፖሊስ ፍድር ቤት  ያቀረበው ሲሆን፣ አብርሃ በፖሊሶች መደብደቡን፣ እርሱ ያልጻፋቸውን ጽሁፎች የራሱ ጽሁፎች እንደሆኑ አድርጎ እንዲፈርም መገደዱን፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ ብቻውን እንዲቀመጥ መደረጉን እንዲሁም ፖሊሶች ያልሆኑ ሰዎች ምርምራ …

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመላውኢትዮጵያአንድነትድርጅት (መኢአድ) እናከአንድነትለዲሞክራሲናለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በጋራ ባወጡት መግለጫ  “በህውሓት/ኢህአዴግአባላትየሚመራውየኢትዮጵያምርጫቦርድበሰላማዊትግሉላይከፍተኛ መሰናክሎችንበመፍጠርከዚህቀደምየተደረጉምርጫዎች እንዲቀሙ፣እንዲዘረፉናኮሮጆእየተገለበጠለገዢውፓርቲእንዲሰጥከፍተኛሚናሲጫወትመቆየቱ”አንሶ ፣ “ዛሬበግልጽፓርቲዎችንለመዝጋትመሞከሩ በኢትዮጵያሕዝብላይእየፈፀመውያለውከድፍረቶችሁሉድፍረትነው ” ብሎአል፡፡ ” የኢትዮጵያብሔራዊምርጫቦርድከዚህአድራጐቱተቆጥቦትክክለኛየሆነየምርጫሜዳየማያዘጋጅከሆነበሰላማዊሰልፍናማንኛውንምየሰላማዊትግልስልቶችን ሁሉበመጠቀምየምንታገልመሆኑንእናሳውቃለን፡፡” የሚለው መግለጫው፣  ይህንስናደርግሊያስሩን፣ሊያሳድዱንናሊገድሉንእንደሚሞክሩብናውቅም፣በሕዝባችን ላይእየደረሰካለውመከራናየሰቆቃኑሮስለማይብስየሚደርስብንንሁሉለ መሸከምዝግጁዎችስንሆንሕዝባችንምከጐናችንእንደሚቆምበመተማመንነው፡፡ ” ብለዋል። ወጣቱናአዛውንቱበሚደረገውማንኛውምየሰላማዊትግልእንቅስቃሴሁሉ፣በተግባርከጐናቸው እንዲቆም፣በእድሜየገፉአባቶችናእናቶችደግሞበፀሎታቸው እንዲያግዙ ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል። ምርጫ ቦርድ ውህደትለመፈፀምያጠናቀቁትንመኢአድናአንደነትንየተለያዩመሰናክሎችንእንዳይዋሃዱ ለማድረግ እየሞከረ መሆኑንም ፓርቲዎቹ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብሁኔታውንበጥሞናናበእርጋታበመከታተልየዜጎችንመብትለማስከበርበሚደረገውጥረትሁሉከታጋዩችጐንእንዲቆም ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል። ለደህንነት፣የፖሊስ  እናየመከላከያሠራዊቱአባላት ባቀረቡት ጥሪ ደግሞ …

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-”ሕገመንግሥቱንናሕገመንግሥታዊሥርዓቱንበኃይልለመናድናሕዝቡበመንግሥትላይ አመኔታእንዲያጣአድርገዋል በሚልመከሰሳቸውንበመንግሥትመገናኛብዙሃንባለፈውማክሰኞእለትየሰሙትአምስትመጽሔቶችእናአንድጋዜጣ ከእንግዲህሊታተሙእንደማይችሉከወዲሁምልክቶችበመታየትላይናቸው። በተለይአዲስጉዳይ፣ፋክትእናሎሚመጽሄቶችአሳታሚዎችእስካሁንበመንግሥትመገናኛብዙሃንከሰሙትዜናውጪ በይፋየደረሳቸውክስየሌለሲሆን ነገርግንመንግሥትባሰራጨውፕሮፖጋንዳምክንያትበተለይየህትመትድርጅቶች ፕሬሶቹንላለማተምእያንገራገሩመሆኑታውቋል፡፡በዚህምክንያት የፊታችንቅዳሜዕለትመውጣትየነበረበት አዲስጉዳይመጽሔትበዕለቱየማይወጣመሆኑከወዲሁየተረጋገጠሲሆንየፋክትእናየሎሚመጽሔቶችምየመውጣት፣ ያለመውጣታቸውነገርባይለይለትም ያለመውጣታቸውጉዳይግንያመዘነመሆኑታውቋል፡፡ የብሮድካስትባለስልጣንበሰኔወር 2006 ባወጣውመረጃመሰረትፋክትበወርበአማካይ 17 ሺ 993፣አዲስጉዳይ በወር 11 ሺ 750፣ሎሚበወር 11 ሺ 250 የኮፒብዛትወይንም  ከፍተኛስርጭትያላቸውመጽሔቶችመሆናቸውን አስታውቆአል፡፡

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አማጽያኑ በአዲስ አበባው ጉባኤ ላይ ለመገኘት ለምን እንዳልፈቀዱ ግልጽ አይደለም። ይህ አቋማቸው ያአበሳጫቸው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የአማጽያኑ መሪ ሪክ ማቻርን ተጠያቂ አድርገዋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ ሁለቱም ሃይሎች ወደ ሰላም ስምምነቱ የማይመጡ ከሆነ የምስራቅ አፍሪካ አገሮች እርምጃ ይወስዳሉ ብለዋል። በደቡብ ሱዳን አሁንም ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ እልቂት …

ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዞኑ ፖሊሶች ትናንት ከሌሊቱ 10 ሰአት ላይ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አመራሮች መኖሪያ ቤት በመሄድ ፍተሻ ካደረጉ በሁዋላ ፣ አመራሮችን ወስደው አስረዋቸዋል። የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘናል በማለት ፍተሻ ያካሄዱት ፖሊሶች በአንደኛው ቤት ውስጥ ሁለት ፍሬ ጥይቶችን ማግኘታቸውን ሲያስታወቁ፣ በሌሎች መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ቪዲዮ ካሜራዎችን፣ ፊልሞችንና የተለያዩ ወረቀቶችን ሰብስበው …

ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ በከተማው የታየው ከፍተኛ የውሃ እጥረት በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ ደርጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አንድ የከተማው ነዋሪ ውሃ በቦቴ ጭነው አንድ ጀሪካን ውሃ በ10 ብር እየሸጡ ሲሆን፣ አብዛኛው ነዋሪ ደግሞ ወንዝ ውሃ በመጠቀም ችግሩን ለማለፍ እየሞከረ ነው። ” ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው፣ ስለ ንጹህ ውሃ …

ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ40 በላይ አፍሪካ መሪዎችን በአንድ ጊዜ ጋብዘው በማነጋገር ላይ ያሉት የአሜሪካው መሪ ፕ/ት ባራክ ኦባማ አፍሪካ እያደገችና ጠንካራ አህጉር እየሆነች መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሳይሆን አፍሪካ በአለም ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ መሆን መጀመሩዋን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። የአፍሪካ ስኬት ከወጣት ህዝቦቿ ጋር የተያያዘ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አክለዋል። አሜሪካ በአፍሪካ የጸጥታ ስራ ለመስራትና …

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ከተያዙ በሁዋላ ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ያለፉት 44 ቀናትን በደብረዘይት አየር ሃይል እስር ቤት ውስጥ ካሳለፉ በሁዋላ የብሪታንያ መንግስት  የኢትዮጵያን ጉዳይ አስፈጻሚ አስጠርቶ በጽህፈት ቤቱ አነጋግሯል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሲሞንድስ አቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር አገልግሎት በአፋጣኝ እንዳያገኙ መደረጉ እንዳሳሰባቸው ለኢትዮጵያው ዲፕሎማት …

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመለስ ዜናዊን ፋውንዴሽን እንሰራለን በሚል ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችና አርሶአደሮች በነፍስ ወከፍ ከ50 ጀምሮ እንዲያዋጡ መገደዳቸው በቅርቡ ከተደረገው የደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የህዝቡን ቁጣ ሊያባብሰው ይችላል ተብሎ በመሰጋቱ ፣ የገንዘብ መሰብሰቡ ሂደት ለጊዜው እንዲቋረጥ መደረጉን የኢህአዴግ ምንጮች ገልጸዋል። ፋውንዴሽኑን ለማሰራት ከሚፈለገው ገንዘብ 10 እጥፍ እንደተሰበሰበ የሚነገርለት ፋውንዴሽን በወ/ሮ አዜብ መስፍን …

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ፖሊስኮሚሽንባለፉትወራትለተካታታይ 3 ወራትያክልለሁሉምመካከለኛናከፍተኛፖሊስመኮንኖች ለደህንነትስራእገዛበሚልስልጠናከሰጠ በሁዋላ፣  ከሃምሌ 26 ቀን 2006 ዓ.ምጀምሮደግሞበአዲስአበባምኒልክትምህርትቤትግቢአዳራሽውስጥበስሩለሚገኙትሁሉም የፖሊስአባሎችስልጠናእየሰጠእንደሚገኝ ታውቋል። ስልጠናውለሁሉምፖሊሶች በተለያየዙርእንደሚሰጥይጠበቃል፡፡የስልጠናው ዋና አላማ መጪውን ምርጫ ተከትሎ የፖሊሱን ሚና ማሳወቅ፣ የፖሊሶችን የፖለቲካ አቋም መገምገምና የደህንነት አጠባበቅ ስልጠና መስጠት ነው ። በስልጠናው ላይ አንዳንድ ፖሊሶች የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ተቃውሞ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚና የመብት ጥሰቶችን እያነሱ …

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓቃቤሕግ  «ሕገመንግሥታዊሥርዓቱንበአመጽለመናድ…» በሚልክስመሰረትኩባቸውያላቸውአምስት መጽሔቶችእና አንድጋዜጣእስካሁንየክስቻርጅእንዳልደረሳቸውናጋዜጠኞቹ መከሰሳቸውንእንደማንኛውምሰውየሰሙት በቴሌቪዥንመሆኑንእየተናገሩነው፡፡ የኢሳት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ የላከው ሪፖርት እንደሚያስረዳው ጋዜጠኞቹ እንደሚከሰሱ ያወቁት ከመገናኛ ብዙሃን መሆኑ አስገርሟቸዋል። የክስ ቻርጁን ለጋዜጠኞች ልኮ ከማሳወቅ ይልቅ ይህን አይነት አካሄድ ለመጠቀም ለምን እንደተመረጠ ግልጽ አልሆነም።

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-50 የሚጠጉ የአፍሪካ መሪዎች በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ግብዣ በዋይት ሃውስ እንዲሰበሰቡ ቢደረገም፣ አለማቀፍ እውቅና ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ብዙም  ለጉባኤም ትኩረት አለመስጠታቸውን የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። አንድ ከአፍሪካ ውጭ ያለ መሪ አሜሪካን ሲጎበኝ የሚሰጠውን የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ያክል 50 የአፍሪካ መሪዎች ተደምረው ሊያገኙ አልቻሉም። ቢቢሲ ከአንድ መለስተኛ ዘገባ በስተቀር ሌሎች …

ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-1 ሺህ 435ኛው የኢድ አልፈጥር በመላው የእስልምና ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው። በአዲስ አበባ ስታዲየም የነበረው ክብረበአል በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ድምጻችን ይሰማ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይካሄድ ባዘዘው መሰረት፣ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ተቃውሞ ሳይካሄድ ቀርቷል። የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ሰሞኑን በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ በርካታ ሙስሊሞች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል …

ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም አቶ አንዳርጋቸውን በድጋሜ በማቅረብ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከባድ ሚስጢር እንዳወጡ አድርጎ ማቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አንዳርጋቸው በረሃ በነበረበት ወቅት ለአመታት ሲተኛበት የነበረውን ሰሌን ምንጣፍና ይለብሰው የነበረውን ብርድ ልብስ ኢሳት ፎቶውን ያገኘ ሲሆን፣ በረሃ ላይ የሚገኙ የግንቦት7 ታጋዮች እንደገለጹት ብርድ ልበሱን አንዳርጋቸው ከመቀበሉ …

ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት በከተሞች የሚገኙ አውራጅና ጫኝ፤ሊስትሮ፤ሱቅ በደረቴ፤ተጽእኖ ፈጣሪ ወጣቶችን፤ በተለያዩ አደረጃጀቶች የታቀፉ ወጣቶችን እና በአደረጃጀት ያልታቀፉ ሌሎች ወጣቶችን  በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀው ሰነድ ፣  “የጥፋት ፖለቲከኞች እንቅስቃሴ በመላ የከተማችን ሰላም ወዳድ ወጣቶች የተደራጀና የነቃ ተሳትፎ እንዲከሽፍ ካልተደረገ በመላ ቀልቡ ወደ ልማቱ የገባው ህዝባችን በተለይ …

ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አካባቢውን ጎብኝተው የተመለሱት የተመድ ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን በጋዛ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ መከሰቱን ጠቅሰዋል፡፡ ሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች ጦርነቱን እንዲያቆሙ በሰብአዊነት ስም እጠይቃለሁ በማለት ዋጻ ጸሃፊው ተናግረዋል። የኢድ አል ፈጥርን በአል ምክንያት በማድረግ ሁለቱም ሃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ አለማቀፍ ማህበረሰቡ የጠየቀ ሲሆን፣ ሃማስ የተኩስ ማቆም ስምምነቱን በመጣስ በእስራኤል ላይ ተወንጫፊ …

ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰኔ 18 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ ደብረዘይት በሚገኘው የአየር ሃይል ግቢ ውስጥ በአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ኢሳት የተለያዩ ምንጮችን አነጋግሮ ባሰባሰበው መረጃ አቶ አንዳርጋቸው በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ድበደባው ቆሞ፣ …

ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የብአዴን ከፍተኛ ሹሞች ለመጪው ምርጫ ይረዳቸው ዘንድ በተለያዩ የአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች የህዝብ ተወካዮችን እየዞሩ በማነጋገር ላይ ሲሆኑ፣ የህዝቡ ተወካዮች ግን ችግሮቹን ሳይፈራ እያቀረበ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ “የኢትዮጵያ መብራት ዝናብ የሚፈራ ነው” በሚል ዝናብ በዘነበ ቁጥር መብራት እንደሚጠፋባቸው ተናግረዋል። “ቋራ …

ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት እስራኤል በሃመስ  የሚወነጨፉ ሮኬቶችን ለማውደምና መሬት ለመሬት የተሰሩ መተላለፊያዎችን ለመዝጋት በሚል ምክንያት ጦሯን ወደ ጋዛ መላኩዋን ተከትሎ፣ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየደረሰ ነው። እስካሁን ድረስ ከ800 በላይ ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን በብዙ ሺ የሚቆጠሩት ደግሞ ቆስለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለው  አብዛኛው ሟቾች ህጻናትና ሴቶች ናቸው። በእስራኤል ወገን ደግሞ …

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ እና የጋራ ብልጽግና መስሪያ ቤት ዋና ጸሃፊ የሆኑት ማርክ ሲሞንድ  የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ከእንግሊዝ መንግስት የኮንሱላር ምክር የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች የሚጠይቅ ደብዳቤ ለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጽፈዋል። ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሰጠው መልስ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ የተባለ ድርጅት …

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ ሃላፊዎች ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በሰንዳፋ እና በኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛዎች ከደህንነት ጋር በተያያዘ ስልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን፣ የሰልጠና ተሳታፊዎች የሚያነሱዋቸውን  ጥያቄዎችን አሰልጣኞች መመለስ አለመቻላቸውን በስልጠናው ላይ የሚሳተፉ ፖሊሶች ለኢሳት ገልጸዋል። ፖሊሶቹ ” መንግስትበተለይከሙስሊምሃይማኖትተከታዮችየሚነሳውንዲሞክራሲያዊየሆነጥያቄለምንአይመልስም?  ለምን በፖሊስተቋምላይየስራጫናእንዲበዛ ይደረጋል?ህዝቡበፖሊስላይያለውጥላቻ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፣እኛህብረተሰቡን በተገቢውመንገድማገልገልእንፈልጋለንና …

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት በጎንደር ዩኒቨርስቲ የምረቃ ስነስርአት ላይ የተገኙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከከተማውና ከአካባቢው ህዝብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ህዝቡ በድፍረት ያሉበትን የመልካም አስተዳደርና ልማት ችግሮች ዘርዝሮ አቅርቧል። አንድ አስተያየት ሰጪ፣ “ከጎንደር አየር ማረፊያ እስከ አዘዞ ያለው መንገድ እናንተ ትማጣላችሁ ተብሎ በአፈር ተደለደለ እንጅ መኪና አያሳልፍም ነበር” ብለዋል። “ውሃንም …

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በሙስሊም ኢትዮጵያውያውያን ላይ ያደረሱትን ኢ ሰበአዊ እርምጃ ተከትሎ በአካባቢው ስትንቀሳቀስ ተገንታለች በሚል ሰበብ የተያዘቸው የሰማያዊፓርቲብሄራዊምክርቤትናየሴቶችጉዳይአባልወይዘሪትወይንሸትሞላለሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም በድጋሜ ተቀጠራለች፡፡ ወይንሸትጭንቅላቷ አካባቢ የተመታች ሲሆንእጇም በፋሻ እንደታሰረበስፍራው የነበሩ ጓደኞቿ ለኢሳት ገልጸዋል። ችሎቱን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት ካቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል አቤልኤፍሬም በፖሊሶች …

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስራኤል ኦር ይሁዳ የሚኖሩ ጓደኛሞች በራስ ተነሳሽነት ተሰባስበው ለኢሳት ያሰባሰቡትን ከ6 ሺ ዩሮ በላይ ገንዘብ አስገብተዋል። ገንዘቡን በማሰባሰብ በኩል ከፍተኛ ሚና የተጫወተው በየነ ቀጸላ ፣  በልጁ በእዮብ አንደኛ አመት የልደት ቀን ኢሳትን የመርዳት ሃሳብ እንደመጣለትና በበአሉ ላይ የተገኙት ጓደኞቹ ከፍተኛ የገንዘብ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጿል። ኢሳት በአገራችን ስላለው ሁኔታ …

ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የደህንነት አባላት በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ፣ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሰራዊቱን አባላትና ከባድ መሳሪያዎችን በምሽት ወደ ሽሬ፣ ተከዜ፣ ወልቃይት፣ መተማ፣ አርማጭሆ በመሳሰሉት የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እያጓጓዘ ነው። ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን ጋር በተያያዘ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የታው የህዝብ ቁጣ ያስደነገጠው መንግስት፣ ማንኛውም አይነት ተቃውሞ ቢነሳ በሚል …

ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕገ-መንግስታዊ ሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መብቱ ተከብረው ሥራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እያካሄደባለውቁርጠኝነትየተሞላበትሕዝባዊዴሞክራሲያዊትግልናየኢህአዴግአምባገነናዊአገዛዝ የሕዝባችንንየመብትጥያቄዎችአፍኖለመግዛትእያካሄደ ባለው የማይሳካለት ጥረት መካከል ያለው ቅራኔ እየሰፋና እየተባባሰበ መምጣቱ ለረጅም ጊዜ በአምባገነናዊ አገዛዝ ለመቀጠል የነበረው ምኞትስጋት ውስጥ እንደወደቀ የተረዳውኢህአዴግለመብታቸውጠንክረውየሚንቀሳቀሱትንሰላማዊ ታጋዮችበሽብርተኝነትእየወነጀለበማሰርና በማሰቃየትላይይገኛልሲልመድረክአስታወቀ። የኢትዮጵያፌዴራላዊዴሞክራሲያዊአንድነትመድረክሰሞኑን ‘ሰላማዊተቃዋሚዎችንበሽብርተኝነትበመወንጀል ሕዝባዊዴሞክራሲያዊትግልንመግታትናሕገ-መንግስታዊ መብቶችንረግጦመግዛትአይቻልም!!!’ በሚልርዕስ ባወጣውመግለጫኢህአዴግበዚሁአካሄዱበየጊዜውበሚወስዳቸውየተሳሳቱእርምጃዎችዜጎችበሕገ-መንግስቱ የተረጋገጡትንመብቶችበአግባቡእንዳይጠቀሙግራየሚያጋባውዥንብርእየፈጠረይገኛል።በዚህየኢህአዴግተግባር የኢትዮጵያፌዴራላዊዴሞክራሲያዊአንድነትመድረክ የአመራርአባላትናደጋፊዎችእንደዚሁምየሌሎችተቃዋሚ ፓርቲዎችየአመራርአባላትናአባላትሰለባእየሆኑይገኛሉብሏል። የመድረክአባልየሆነውየአረናትግራይለዴሞክራሲናሉአላዊነትፓርቲየሥራአስፈፃሚኮሚቴ አባልናየመድረክጠ/ጉባዔአባልየሆኑትናየገዥውንፓርቲኢ-ሰብአዊናፀረ-ዴሞክራሲያዊ …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ምርጫ የአዲስ አበባ ከተማን ለማሸነፍ ቆርጦ የነተሳው ኢህአዴግ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ነዋሪዎች ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ በማምጣት መታወቂያዎችን እያደለ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮች ገልጸዋል። ብዛት ያላቸው በተለይም ከትግራይ ክልል የመጡ የህወሃት አባላት የ13 ቱም ክፍለ ከተሞች የመኖሪያ መታዎቂያዎች እየታደሉዋቸው ሲሆን፣ በምርጫው እለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ሰ/ሸዋ ዞን የመርሃ ቤቴ ወረዳ አለም ከተማ እና የሚዳ ወረሞ ወረዳ መራኛ ከተማን እንዲሁም አዋሳኝ የደራ ወረዳን ጨምሮ 24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት እንዲሰጥ በአለም ከተማ የሚገኘውን ዋና የመብራት ማሰረጫ ትራንስፎርመር ተነቅሎ  ወደ አቃስታ የመብራት ስቴሽን ጣቢያ ለማዛወር  የነበረው  እቅድ በህዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ መክሸፉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፊታችን አርብ በቤልጂየም ብራሰልስ በሚደረገው ተቃውሞ በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ያወግዛሉ። የተቃውሞ ሰልፉ  በብራሰልሰሹማንአደባባይ እኤአ ጁላይ 25 ቀን ከቀኑ 13 ፡30 እስከ 17 ሰአት ይካሄዳል። ነገ ረቡዕ ደግሞ በጀርመን በርሊን እንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚኖር ታውቋል። ይህ በእንዲህ …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን አማጺ መሪ የሆኑት ሬክማቻር በናስር በተባለው ከተማ እንደ አዲስ በተነሳው ጦርነት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ወታደሮችንና ንብረቶችን ማውደማቸውን ሲገልጹ የናስር ከተማን ደግሞ  በእጃቸው ማስገባታቸውን እየተናገሩ ነው። ሬክማቻር ምንጮቻቸውን ጠቅሰው እንደተናገሩት  3 የሚሆኑ የጦር ተሽከርካሪዎችን አውድመው በመቶዎች የሚቆጠሩ(100) የመንግስት ወታደሮችን መግደላቸውን ሲናገሩ የመንግስቱ የጦር አዛዝ የሆኑት ፓል ማሎንግ አዋን ማስተባበላቸውንና …

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሃ ቤቴ ወረዳ በአለም  ከተማ ከመብራት ማሰራጫ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ አንድ ሰው ከፌደራል ፖሊሶች በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ቆስሏል። መብራት ሃይል የከተማውን የመብራት ማሰራጫ በማንሳት ወደ ሌላ አካባቢ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲጀምር የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ አሰምቷል። እሁድ እለት ወደ ከተማዋ የገባው የፌደራል ፖሊስ ከህዝቡ ጋር ፊት …

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበትን ቦታ ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ትክክለኛ ቦታውን ለማወቅ አልተቻለም። ይሁን እንጅ በማእከላዊም ሆነ በቃሊ እስር ቤት አለመኖራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የገዥው ፓርቲ ሰዎች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፕሮፓጋንዳ ስራ ለመስራት የተለያዩ ሰዎችን እያነጋገሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። ኤርትራ ውስጥ ነበርን ያሉ እና በአቶ  አንዳርጋቸው ላይ …

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በታላቁአንዋርመስጂድበመንግስትየደህንነትኃይሎችናበፖሊስሀላፊዎችከቀናትበፊትታቅዶበሙስሊሙ ላይ በተወሰደእርምጃከ6 ሺ በላይየመንግስትቅጥረኛሲቪልለባሾችመሰታፋቸውን አስታውሷል። “ቅጥረኞቹየተከበረውየረመዳንወርየጁምአሰላትከመሰገዱበፊትበመስጊዱውጫዊሰሜናዊአቅጣጫግርግርበማስነሳትናከፖሊሶችጋርከሁለቱምአቅጣጫድንጋይበመወራወር የታለመውን ውጤትለማምጣትሞክረዋል” የሚለው ድምጻችን ይሰማ፣  በሁሉምአቅጣጫየነበሩናበአስርሺዎችየሚቆጠሩሙስሊሞችየጁምአሰላታቸውንእንዳይፈጽሙእክልከመሆናቸውም በላይበበርካታጾመኛሙስሊሞችላይእጅግአሰቃቂጭፍጨፋ”መፈጸሙን ገልጿል። “ሙስሊሙንከሁሉምአቅጣጫበቆረጣስልትለሰላትበተቀመጠበትበመቁረጥበነፍስወከፍበያዙዋቸውዱላዎችናየመሣሪያሰደፎችርህራሄአልባበሆነሁኔታመደብደባቸውንና መጨፍጨፋቸውን የገለጸው ደምጻችን ይሰማ፣   በእለቱየተወሰደውመንግስታዊሽብር ‹‹ጥቁርሽብር›› የሚልስያሜተሰጥቶታል ብሎአል። ” ‹‹ጥቁርሽብር›› በሰለጠነውይይትከማያምን፣ሰላማዊነትናዲሲፒሊንከማይገባውመንግስትየሚፈልቅ፣ሰዎችሳይሆኑዱላብቻየሚናገርበት፣ሐሳብየሚንሸራሸርበትሳይሆንነውጥናግፍ የሚሰፍንበትሂደትነው ” ብሎአል። ‹‹ጥቁርሽብር›› አይናቸውንየጋረደውጥቁርግርዶሽየህዝብንእውነታእንዳይረዱያደረጋቸውናብቃትየሌላቸውኃላፊዎችየሚወስኑት፣ሰብዓዊነትበጭካኔጭለማውስጥየሚሰጥምበት አስከፊክስተትመሆኑን የጠቀሰው ድምጻችን ይሰማ፣  ለሰላማዊሕዝብናጥያቄምላሹንዱላያደረገኃይል፣ባልታጠቀናበእጁድንጋይባልጨበጠጾመኛሕዝብላይየጥይትቃታየሚስብ መንግስት ከርሞምየሚነዳውበ‹‹ጥቁርሽብር›› ብቻነው ብሎአል። የሐምሌ 11/2006ንአሰቃቂየመንግስትጭፍጨፋየታሪክካስማበማድረግእለቱ ‹‹ጥቁርሽብር›› ሲባልከዚህበኋላያሉክስተቶችም ‹‹ከጥቁርሽብርበኋላ›› ወይም ‹‹ከጥቁርሽብርበፊት›› …

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስሪያ ቤቱ በመግለጫው በሰሜን ኢትዮጵያ  ከ12 ዲግሪ የትይዩ መስመሮች እስከ ኤትዮ ኤርትራ ድንበር ባለው የአየር ክልል ምንም አይነት በረራ እንዳይካሄድ መክሯል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በዚሁ ክልል የሚያልፉ የንግድም ሆነ ሌሎች አውሮፓላኖችን ሊመታ እንደሚችል አስጠንቅቋል። የአሜሪካ መንግስት ማስጠንቀቂያ ካወጣባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል ኬንያ እና ሶማሊያ ይጠቀሳሉ። የአሜሪካ አቪየሽን እገዳ …

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአረና የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታግዳለች ። ወይዘሪት ተክለ ደስታ የጤና ባለሙያ ስትሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ታገለግል ነበር። የወረዳው ባለስልጣናት “አንቺ እንደ ወንድምሽ ዓረናነሽ ፣ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ …

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-”ለከፈልነው መስዋትነት አቻ ውጤት እናመጣለን” በሚል መፈክር የተካሄደው ተቃውሞ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት አምርቷል። የፌደራል ፖሊሶች ሆን ብለው ባስነሱት ግጭት ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ቆስለዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ኢሳት እስካሁን ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ ባይችልም አንዳንድ ሙስሊሞች  ስልክ በመደወል  የተገደሉ ሙስሊሞች መኖራቸውን ተናግረዋል። …

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ፣ የኢህአዴግ መንግስት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በወሰደው ህገወጥ እርምጃ የእንግሊዝ መንግስት ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። በስፍራው የነበረውን ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹን አነጋግረነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። በምስራቅ …

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በጸገዴ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ በአማራው ክልል ስር ተካለው የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችን መውሰዳቸውን ተከትሎ ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ድርጊቱን በመቃወም ከትግራይ ክልል ታጣቂዎች ጋር ተፋጠው እንደሚገኙና በማንኛውም ሰአት ግጭት ይፈጠራል ተብሎ እንደሚፈራ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ወደ 400 የሚጠጉ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ወደ ድንበሩ የተጠጉ ሲሆን፣ …