መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“የመከላከያ ሰራዊቱ ያዛዥነት ቦታዎች በአንድ ብሄር ቁጥጥር ስር ነው” በሚል ተደጋጋሚ ትችት የሚደርስበት ኢህአዴግ፣ ሰራዊቱን ህብረብሄራዊ ማድረጉን ገለጸ። የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች  እንዲወያዩበት ተብሎ በኢህአዴግ የተዘጋጀው ሰነድ የትምክት ሃይሎች ”  በአገራችን የአንድ ብሄር የበላይነት ያለ ለማስመሰል የማያደርጉት ሙከራ የለም” ካለ በሁዋላ፣ ሰራዊታችን በህገ መንግስቱ መሰረት የተዋቀረ ህብረብሄራዊ ሰራዊት …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ መስከረም 26 ቀን 2007 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክርቤቶች መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በአዲስአበባ ባለፈው ዓመት 22ሺ ያህል የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል የሚል ሪፖርት ማቅረባቸው ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት በሰኔ ወር በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት 22ሺ ያህል ቤቶች ቀደም ሲል ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠረው ማኅበር ጽንፈኛና አሸባሪ የመሆን ዕድሉ የሰፋ ነው››ሲሉ የኢትዮፐያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ተናሩ። ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ይህን ያሉት ፡ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልፀግ›› በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መስብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረውን ጉባዔ በከፈቱበት …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጥቃቅን እና አነሰተኛ ተደራጅተው ፤በየቀኑ ላባቸውን እያፈሰሱ የሚደክሙ የድሃ ድሃ እናቶች እለቅሶ ርቆ እየተሰማ መሆኑን የክልሉ ዘጋቢያችን ነጋዴዎችን አነጋግራ የሰራቸው ዘገባ ያመለክታል 33 በእድሜ የገፉ እናቶች ” በመንግስት ሌቦች ተዘርፈናል ሲሉ ” እያለቀሱ ብሶታቸውን ገልጸዋል። በአማራ ክልል በስራ አጥ እና የድሃ ድሃ ከተደራጁ 31 ሺ 549 ማህበራት …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተቃውሞ ለማሰማት በሄዱ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰው ሰለሞን ገብረስላሴ፣  በ48 ሰአታት ውስጥ ከአሜሪካ እንዲወጣ ከተደረገ በሁዋላ የመንግስት ደጋፊዎች የአሜሪካን እርምጃ ለመቃወም የጠሩትን ተቃውሞ ለማክሸፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም ተመሳሳይ ተቃውሞ አዘጋጅተዋል። የመንግስት ደጋፊዎች አሜሪካ ለኢምባሲው በቂ ጥበቃ አላደረገችም በሚል ሲቃወሙ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው አገሪቱ ለሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለመንግስት ሰራተኞች እና ለኢህአዴግ አባላት የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና የዩኒቨርስቲ መምህራንም እንዲወስዱ በመገደዳቸው፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን በቀድሞው የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር እና በአሁኑ የጠ/ሚ የፖሊሲ አማካሪ በአቶ በረከት ስምኦን እንዲሰለጥኑ እየተደረገ ነው። ስልጠናውን የሚወስዱት በታሪክ፣ በፖለቲካል ሳይንስ፣  በሶሺኦሎጂ፣ በጆግራፊ፣ በፊዚክስ እና በመሳሰሉት የትምህርት ዘርፎች …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠ/ሩ የፖሊሲ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ስልጠና በመውሰድ ላይ ላሉ የዩኒቨርስቲ መምህራን ነው። አቶ በረከት በምእራባውያን እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ገንዘብ በሃይማኖት ስም የፖለቲካ አላማ ለማራመድ በሚል ወጪ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ በረከት በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ትርምስ እንዲፈጠር ይፈልጋሉ ያሉዋቸውን …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው እስከ 200 የሚደርሱ የመጨረሻ ዓመት የህክምና  ተማሪዎች በመመረቂያ አመታቸው ላይ እንዳሉ ሲመረቁ የሚከፈላቸውን የደመወዝ ግማሽ የሚከፈላቸው ሲሆን የውዝግቡ ዋነኛ ምክንያት የሚከፈላቸው ግማሽ ክፍያ በአዲሱ የደመወዝ ጭማሪ መሰረት አለመሆኑ ነው፡፡ የህክምና ተማሪዎቹ ለአካባቢው  አመራሮች  ቅሬታቸውን አቅርበው የፓለቲካ አመራሮቹ “ቅሬታችሁ ተገቢ ነው” የሚል መልስ ቢሰጡዋቸውም የዩኒቨርስቲው ዲን  ተማሪዎቹን …

መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመጨረሻ የስራ ዘመናቸውን ዛሬ ለጀመሩት የተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት የመክፈቻ  ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መንግስት አምና እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮም ከኤርትራ መንግስት ለሚሰነዘር ማንኛውም ትንኮሳ ተመጣጣኝ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል። የኤርትራ መንግስት አስታጥቆ የላካቸውን የ ግንቦት7 ፣ ኦብነግና ኦነግ ጥቃቶችን መከላከላቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ በዚህ አመትም …

መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአሁን ቀደም  ከትርፍ አምራች የአማራ ክልል ወረዳዎች ወደ ትግራይ ክልል የተካለሉ ቦታዎች አሁም ድረስ በሁለቱ ክልሎች መካከል የውዝግብ ምክንያት ሆኖ በቀጠለበት በዚህ ወቅት የአብደራፊ ከተማን ወደ ትግራይ ክልል ለመጠቅለል የሚደረገው ቅድመ ዝግጅት ስጋት አሳድሮብናል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ገልጸዋል። የክልሉ መሪዎች  ለአጎራባች ክልል ኢንቨስተሮችና …

መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ  ማክሰኞ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ/ም በመተማ ወረዳ  ገንዳ-ውሃ ከተማ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ  በወሰደው እርምጃ የወረዳው ፖሊስ ኢንስፔክተር ዮሃንስ ይግዛው ሲገደል፣ ኮንስታብል ሻንበል አበበ በጥይት ተመቶ ክፉኛ ቆስሏል ብሎአል። ህዝብን እየበደሉ ባሉ የስርዓቱ ታጣቂዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ ግንባሩ አስጠንቅቋል። ኢሳት የመተማ …

መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ የዕንቁላል ምርቶች እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በአስደንጋጭ ፍጥነት እያሻቀበ መሆኑን ተጠቃሚዎች ገለጸዋል፡፡አንዳንድ አምራቾች በበኩላቸው እጥረቱ ያጋጠመው ከመኖ እጥረት ጋር በተያያዘ ነው ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተዘዋወርንባቸው ሳሪስ፣ ሾላ እና ካዛንቺስ አካባቢዎች በበርካታ መደብሮች የዕንቁላል ምርቶች ሰሞኑን ጨርሶ የሌለ ሲሆን አቅርቦቱ ባለባቸው መደብሮች የአንድ አበሻ …

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለተቃውሞ ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በተጓዙት ኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰው የኢምባሲ ሰራተኛ በ48 ሰአታት ውስጥ አገር ለቆ እንዲወጣ መደረጉን ኢሳት በሰበር ዜና መዘገቡን ካስታወቀ ከአንድ ቀን በሁዋላ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግለሰቡ ከአገር መባረሩን አረጋግጧል። የኢትዮጵያ መንግስት በቅጽል ስሙ ወዲ አይኑ የተባለውን የደህንነት ሰራተኛ የዲፕሎማቲክ ከለላ እንዲያነሳ ቢጠየቅም፣ …

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ( ኦብነግ) ባወጣው መግለጫ በክልሉ የሚታየው ድርቅ እየተባባሰ በመሄዱ ነዋሪዎችና እንስሳት እየሞቱ ነው። ለተከታታይ ሁለት አመታት የቀጠለው ድርቅ በመንግስት ከተጣለው የኢኮኖሚ ማእቀብ ጋር ተያይዞ በነዋሪው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። የአለማቀፉ ማህበረሰብ ለአካባቢው ህዝብ የሚሰጠው እርዳታ በተገቢው ቦታ ላይ መድረሱን እንዲያረጋጋጥ ኦብነግ …

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ተከሰው ማዕከላዊ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን አመራሮች ዛሬ መስከረም 23/2007 ዓ.ም  ከሰዓት በኋላ አራዳ ችሎት ቀርበው 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ፡ የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ፍቃዱ አበበ እንዲሁም የዞኑ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ኢንጅነር ጌታሁን አርባምንጭ ውስጥ ለአንድ ወር ከ15 …

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ለመምህራን እየሰጠ ባለው የፖለቲካ ስልጠና ላይ የሚሳተፉት በወሊሶ ከተማ አስተማሪ የሆኑት ግለሰብ “ጠንካራ ጥያቄዎችን መጠየቃቸውን” ተከትሎ መታሰራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። መምህሩ እንዳሉት ” የመንግስት ባለስልጣናት መሬት እየከፋፈሉ መሸጣቸውን አስመልክቶ ማስረጃ አቅርበው በመጠየቃቸው” ህዝብን “ልታነሳሳ ነው” በሚል  ለአንድ ቀን ታስረው ” ሁለተኛ እንዳትናገር በሚል በማስጠንቀቂያ መፈታታቸውን ተናግረዋል። ማስጠንቀቂያው …

መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትናንት ሰኞ በኦጋዴንና በጋምቤላ በተጨፈጨፉ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮችን ለማነጋገር በኢምባሲው አካባቢ በተገኙት  ኢትዮጵያውያን ላይ አንድ የስልጣን ደረጃው ያልታወቀ ሰለሞን ወይም በበረሃ ስሙ ወዲ ወይኒ የተባለ ግለሰብ ጥይቶችን በመተኮሱ የኢትዮጵያውያንንና አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል። አለማቀፍ እውቅና ያላቸው ሮይተርስ እና  ዋሽንግተን ፖስት የመሳሰሉ የዜና አውታሮች ዜናውን …

መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ የመሰናዶ እና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ መመህራን የስራ ማቆም አድማውን ያደረጉት መንግስት ቃል በገባው መሰረት የሃምሌ እና ነሃሴ ወር ደሞዝ ጭማሪ አልከፈለንም በሚል ነው። መመህራኑ የደሞዝ ጭማሪው ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ በታየው የዋጋ ንረት እየተሰቃየን ነው በማለት የወረዳውን አስተዳዳሪ ለማነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም አስተዳዳሪው ለስብሰባ በሜዳቸው ሳይሳካለቸው …

መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ቡርጂ ወረዳ የመንግስት ስልጣን በተቆናጠጡ የወረዳ ሹሞች በተደጋጋሚ የደረሰባቸው አስተዳደራዊ በደልና የሰብኣዊ መብት ጥሰት ወንጀል እንዲጣራና በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ  አቤቱታ ያቀረቡ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን ገልጸዋል። ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በአቶ አማሬ ቦሬና በ አቶ ጅሎ ቦነያ አማካይነት ያለአንዳች ምክንያት መታሰራቸውን፣ በእስር ወቅትም በተደጋጋሚ …

መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ደልጊ ፣ሻውራ፣ ጎርጎራና ቋራን ለ70 ዓመታት በማገናኘት ያገለገለው ድልድይ በመንገድ ስራ በተፈጠረ የጥናት ችግር ቢፈርስም ተመልሶ ሊሰራ ባለመቻሉ ከፍተኛ ችግር ደርሶብናል በማለት የጯሂት ከተማ ነዋሪዎች አማረዋል፡፡ ከጎንደር ወደ ጯሂት በሚወስደው መንገድ ላይ በጣልያን መንግስት እንደተሰራ የሚነገረው የሱዳን ገደል ድልድይ ከአራት ወራት በፊት በመፍረሱ  ወላዶች፣አረጋውያንና የንግዱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ችግር …

መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት በዘጠኝ ወራት ብቻ የሥራ ፈላጊዎችን መረጃ ለማጠናቀር ታስቦ በተካሄደ ምዝገባ በመላ ሀገሪቱ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሥራ ፈላጊዎች በፈቃደኝነት መመዝገባቸውንና ከነዚህ ውስጥ ከ351ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲና የኮሌጆች ምሩቃን መሆናቸውን ከከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተገኘ ጥናት አመለከተ፡፡ ይህ ጉዳይ መጪው ምርጫ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል …

መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት መሪ የሆኑት አቶ አለማየሁ መኮንን ለኢሳት እንደገለጹት መንግስት ከጀመረው የሸንኮራ እርሻ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ እየጠፋ ያለው ሰው ህይወት መንግስት መፍትሄ ሊሰጠው ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነው። በጅንካ ነዋሪ የሆነው  ኡመር ንጋቱ  በሙርሲ ብሄረሰብ አባላት በጥይት ተደብድቦ እንደሞተ መነገሩን ተከትሎ ሃሙስ እለት ከቀብር መልስ …

መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር የተገናኙነት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በሰላም ማስጠበቅና ሽብርተኝነትን በመዋጋት በኩል እያደረገች ያለውን ሚና አወድሰዋል። አገሪቱ በደቡብ ሱዳንና በሶማሊያ ሰላም በማስጠበቅ በኩለ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ኢትዮጵያ  የሰላም አስከባሪ በመላክ ቁጥር በአለም ግንባር ቀደም ከሆኑ መንግስታት ተርታ እንደምትመደብም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት …

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በጅንካ ከተማ በአይነቱ ልዩ ነው ተባለ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን የአካባቢው ምንቾች ገልጸዋል። የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገው ከጅንካ ከተማ  ወደ ሃና በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ ሰራተኛ መገደሉን ተከትሎ ነው። ሃና አዲሱ የስኳር ፋብሪካ ግንባታ የሚካሄድበት ቦታ ሲሆን፣ ግድያውን የፈጸሙትም የስኳር ልማቱ ከቀያቸው ያፈናቀላቸው የሙርሲ ብሄረሰብ አባላት …

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-98 በመቶ የሚሆነውን  የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎችን ከተቆጣጠሩት የህወሃት ጄኔራሎች ባልተናነሰ  በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ላይ የነበሩት ብቸኛው የአማራ ተወላጁ ጄኔራል አበባው ታደሰ በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ከሃላፊነታቸው ዝቅ ብልው እንዲሰሩ ከተወሰነባቸው በሁዋላ በመጨረሻ ከመከላከያ ሰራዊት መሰናበታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ጄ/ል አበባው ከጄ/ል ሞላ ሃ/ማርያም እና ከጄ/ል ሰአረ …

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ አልተቀበሉም ባላቸው አርሶ አደሮች ላይ በይፋ የማሸማቀቅ ስራ እየሰራ መሆኑን አርሶ አደሮች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል። የገዢውን ፓርቲ ፖሊሶች ተቀብለው አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ አርሶአደሮች ” ታካች አርሶ አደር “የሚል ስያሜ እየተሰጣቸው በተለያዩ መንገዶች እየተዋከቡና በእዳ እየተጠየቁ ሲሆን፣ የስርአቱ ደጋፊ የሆኑ አርሶአደሮች ደግሞ …

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ አገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ሀሰተኛ የብር ኖቶች የተሰራጩ ሲሆን፣ ፖሊስ በየቀኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ለመሰብሰብ ቢችልም ችግሩ አሁንም በስፋት እየታየ ነው። የፌደራል ፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው በመላ አገሪቱ በተሰራጨው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሃሰት የብር ኖቶች መንግስት በየቀኑ ከባንኮችና ከገበያ ሱቆች ለመሰብሰብ ተገዷል። ፖሊስ በዚህ ስራ ላይ ተሰማርተዋል …

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የትምህርት መመሪያን ለማጥመቅ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ በአገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠናውን በግዳጅ እንዲወስዱ እየተደረጉ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎቹ የፖለቲካ ስልጠና እንዳለ አስቀድመው በመስማታቸው ፣ ከስልጠናውን የቀሩ ሲሆን፣ የገዢው ፓርቲ የወረዳ ሹሞች መምህራን ተማሪዎችን እንዲያመጡ የተለያዩ ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ እያግባቡ ነው። አንድ …

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ንብረት በሆነው ጥረት ኮርፖሬት ውስጥ የሚገኙት ጣና ሞባይል ና ዘለቀ እርሻ ልማት ድርጅቶች በያዝነው አመት ከ225 ሚልዩን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው በ2007 ዓም መግቢያ ላይ በተደረገው የድርጅቱ ግምገማ ላይ ተገልጧል። አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ መሳደባቸውን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አመራሮችን ለማሳመን የተደረጉ ስብሰባዎች ና የተሃድሶ …

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ አገሪቱ ከ40 ሚሊዮን በላይ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ወጣት እና ጎልማሶች አሉ ያሉት አቶ ሺፈራው ፤  ይህንን የትምህርት እድል ያለገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች አማራጭ ትምህርት እንዲያገኙ የተደረገው ሙከራ አፈፃጸሙ ከዜሮ በታች ነው ብለዋል። በኢህአዴግ የእቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ እንደቀረበው በጎልማሶች የትምህርት አቀራረብ  አማራ 0.9፣ ኦሮምያ ፣ 0.71 …

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዋጋ ንረትን ያረጋጋሉ ተብሎ በመንግሥት ልዩ ድጋፍ በተለይ በአዲስአበባ ከተማ የተቋቋሙት የሸማቾች የህብረት ሥራ ማህበራት በሙስናና ብልሹ አሠራር ውስጥ በመዘፈቅ አንዳንዶቹ በተቃራኒው የዋጋ ንረትን የሚያባብሱ ሥራዎች ውስጥ መሰማራታቸው መረጋገጡን ከአስተዳደሩ የተገኘ ሰነድ ጠቆመ፡፡ 250ሺ ያህል አባላት ያሉዋቸው 153 መሰረታዊ ማህበራትና 10 ዩኒየኖች እንዲሁም 1 ሺ 815 አዲስ …

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄኔቫ ሲካሄድ በሰነበተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ግምገማ ላይ አቋሙን ያስታወቀው አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ኢትዮጵያ የሰአብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንደምታከብር ቃል መግባት ብቻ ሳይሆን፣ በተጨባጭ ገለልተኛ ወገኖች እስር ቤቶችን እንዲገበኙ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች እንዲጎበኙና በደል የደረሰባቸውን ወገኖች ለማነጋገር እንዲፈቀድላቸው ጠይቋል። የሰብአዊ …

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተመራው ስብሰባ ላይ ዳኞች የስርአቲ ደጋፊ እንዲሆኑ እየተገደዱ ባለበት ሁኔታ እንዴት ነጻ ዳኝነት ሊሰጥ ይችላል በማለት ጠይቀዋል። የድርጅት አባላት ያልሆኑ ዳኞችም ስራቸውን ለመስራት እየተቸገሩ መምጣታቸውን መናገራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ይሄው በመላው አገሪቱ በሚደረገው የፖለቲካ ስልጠና የገዢው ፓርቲ ደጋፊ አባላት ሳይቀሩ በስርአቱ ላይ …

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ስራ በሚገኘው ደጀና አቬሺን ውስጥ የሚሰራ ስሙ በውል ያልታወቀ አንድ ወታደር በግቢው ውስጥ ለሚሰሩ  ሰራተኞች  በተከፈተው ሻሂ ቤት ውስጥ በአስተናጋጅነት የምትሰራዋን በደብረዘይት ነዋሪ የሆነች ወጣት በስድስት ጥይቶች ተኩሶ መግደሉን የአይን እማኞች ገለጹ። ትናንት 11 ሰአት ላይ ሰራተኞች ሰርቪስ አውቶቡስ ለመያዝ በተሰለፉበት ወቅት፣ ወታደሩ በአስራዎች …

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በእስር ቤት ውስጥ ከሌላ እስረኛ ጋር ተጋጭተዋል በሚል ሰበብ ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው በሁዋላ ጸሃይ ላይ ለረጅም ሰአት እንዲቀመጡ ተደርገዋል። አቶ ኦኬሎ ድብደባው የተፈጸመባቸው ቂልንጦ እየተባለ በሚጠራው  እስር ቤት ውስጥ ሲሆን፣ በእስር ቤት ሃላፊዎች መረጃ እንዲያቀርብ ተብሎ …

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ 130 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች ለአፍሪካ መሪዎች በእስር ቤት ጥቅም ላይ የሚሆኑ የማሰቃያ መሳሪያዎችን ይሸጣሉ። የኤልክትሪክ ንዝረት ያላቸው   ከብረት የተሰሩ ሹል ዱላዎችና ሌሎችም  የማሰቃያ መሳሪያዎች ለአፍሪካ እና ለእስያ አገራት መሸጣቸው በአህጉራቱ ውስጥ የሚታየውን ሰብአዊ መብት እረገጣ አባብሶታል። በአለም ላይ ስለት ያላቸውን የንዝረት ብረቶችን የምታመርተው …

መስከረም ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምዕራብ አርማጮሆ ወረዳ የአብርሃጅራ ነዋሪዎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በመሬት ስሪት ፣በልማት ና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ቅሬታወች ቀርበዋል፡፡በውይይቱ ላይ በመገኘት ቅሬታቸውን ያቀረቡት ነዋሪዎቹ “የወረዳው አመራሮች እርስ በርስ በመሻኮት ስልጣን ለመያዝ ሰዎችን ያስገድላሉ የበላይ አመራሮችን የኑሮ ሁኔታ በማጥናት ቤት ሰርተዋል፣ሃብት አከማችተዋል በማለት እነርሱም የበላይ አለቆቻቸውን …

መስከረም ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባወጣው መግለጫ ፍትህ ሚኒስቴር ሃምሌ 28፣ ቀን 2006 ዓም በፋክት፣ ሎሚ፣ ጃኖ፣ አዲስ ጉዳይ፣ እንቁ መጽሄቶችና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ያቀረበው ክስ በህገመንግስቱ የሰፈረውን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ፣  ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው የሰብአዊ መብቶች አለማቀፍ መግለጫ አንቀጽ 19 ፣ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች አለማቀፍ ቃልኪዳን አንቀጽ 19 …

መስከረም ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ ለመጪው ምርጫ በሚያደርገው ዝግጀቱ የመንግስት ሰራተኞችን፣ መመህራንና ተማሪዎችን በማስገደድ የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና እንደቀጠለ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ሳምንትም በርካታ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። በአዲስ አበባ በኢትዮ-ቻይና ቲቪቲ በነበረው ስልጠና ላይ ” ከ23 አመታት በሁዋላ አሁንም እራሳችሁን ከደርግ ጋር እያነጻጸራችሁ ነው? ደርግ ከሻእቢያ፣ ከእናንተ ጋርና ከሶማሊያ ጋር ጦርነት …

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ለቀናት ጋብ ብሎ የቆየው ግጭት ከትናንት ጀምሮ እንደገና አገርሽቷል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ጋትሉዋክ ቱት የገዢው ፓርቲ ልሳን ለሆነው ፋና ሬዲዮ ” ኪራይ ሰብሳቢዎችና የመሬት ደላሎች በጠነሰሱት ሴራ ለዘመናት ተቻችሎ የኖረውን ህዝብ ለመከፋፈል ጥረት በማድረጋቸው መስከረም አንድ በሚጤ ከተማ በተፈጠረው ግጭት 13 ሰዎች” መሞታቸውን፣ በገጠር …

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት መስከረም 5 ትምህርት እንዲጀምሩ ቀደም ብሎ ይዞት የነበረውን እቅድ በመሰረዝ አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመስከረም 30 በሁዋላ እንዲጀመር ትእዛዝ አስተላልፏል። በትምህርት ሚ/ር ደኤታ ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ ዲንሳ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች መስከረም 5፣ 2007 ዓም የተጻፈው ደብዳቤ   የአንደኛ አመት ወይም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ ተደርጎ …

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተመድ የሰብአዊ መብት  ኤክስፐርቶች  ኢትዮጵያ  የጸረ ሽብር ህግን  ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ለማፈን እና የማህበራት ነጻነትን ለመጋፋት እየተጠቀመችበት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ህጉን አላግባብ መጠቀሙዋን እንድታቆም መጠየቃቸውን-ከጄኔቫ የወጣ መግለጫ ያመለክታል። የተመድ የሰብ ዓዊ መብት ባለሙያዎች አያይሰውም ኢትዮጵያ  በተያሰው ዓመት መጀመሪያ በሰብአዊ መብት ካውንስል አባላት የጸደቀውንና በ 193 ቱም የመንግስታቱ ድርጅት …

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በቢቸና አውራጃ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2 የቀድሞ የቅንጅት አባሎች ተገድለዋል። ገዢው ፓርቲ እንዳደራጀ የሚነገረው ቡችሌ የተባለው ቡድን ክንዳየ አለሙና አባይነህ በተባሉ የቀድሞ የቅንጅት አባላት ላይ ስዋ ወንዝ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግድያ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሎአል። ሁለቱም ሰዎች በተመሳሳይ መንገድ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድበው መሞታቸው ታውቛል። ከ10 …

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ኒክ ኦቻላ ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ አዲስ አመት ደገኞች በፈጸሙት ጥቃት 8 የመዠንገር ተወላጆች ተገድለው ፣ ከ3 ሺ በላይ የሚሆኑት መሰደዳቸውን ገልጸዋል። 835 መዠንገሮች ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠግተው በምግብ እጥረትና በብርድ ሲሰቃዩ መቆየታቸውን አቶ ኒክ ተናግረዋል። አቶ ኒክ እንደሚሉት ለግጭቱ መንስኤ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው የመሬት ቅርምት ፖሊሲ ነው። በዚህ …

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ በላይ የት ሄደን አቤት እንደምንል ግራ ተጋብተናልም በማለት በመንግስት አሰራር ማዘናቸውንም ተናገረዋል፡፡ የቋራ ከተማ ነዋሪዎች ከወራት በፊት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተገኙበት የጠየቋቸው የመልካም አስተዳደር ፣የመንገድ ፣የመብራት እና ስልክ ችግሮች ይፈታሉ በማለት አመራሮቹ ቃል ቢገቡም በዚህ አመት በተደለደለው የበጀት ቀመር ተጨማሪ በጀት ሳይያዝ መቅረቱ እንዳሳዘናቸው …

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከክልሉ ባለስልጣናት የሚደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፕሬዚዳንቱ አቶ አብዲ ሙሃመድ ወደ አዲስ አበባ እንዲሄዱ ከጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል በክልላቸው የሚገኙ ሲሆን፣ ” በኢትዮጵያ ውስጥ ከህወሃቶች በስተቀር ማንም ከስልጣን ሊያነሳኝ የሚችል ሃይል የለም” በማለት፣ የአቶ ሃይለማርያምን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል። በምስራቅ እዝ አዛዥ ጄ/ል አብርሃም ገብረማርያም እንደሚተማመኑ የገለጹት …

መስከረም ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የህዝብ ግንኙነት ስራ አማካሪ እና የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበር በመሆን ካገለገለ በሁዋላ የተለያዩ የቪዲዮ ማስረጃዎችን በመያዝ ከአገር የወጣው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን ፣ “ኦ ኦጋዴን” በሚል ኢሳት ያስተላለፈው አጭር የዶክመንታሪ ፊልም፣ በስልጣን ላይ ያሉት ገዢዎች ለሶማሊ፣ ለኢትዮጵያና በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ያላቸውን ንቀት ያሳያል ብሎአል። ዘገባውን ከተመለከተ …

መስከረም ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህገመንግስቱ የጸደቀበትን ህዳር 29 ቀን «የብሔር ብሔረሰቦች ቀን» በሚል በየዓመቱ ሲያከብረው የቆየው ኢህአዴግ ዘንድሮ  20ኛውን ዓመት በተለየ ድምቅት በማክበር ሕዝቦች በሕገመንግስቱ የተረጋገጡላቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አተገባበር እንከን አልባ እንደነበሩ በማጉላት በመጪው ግንቦት ወር ይካሄዳል ተብሎ በሚገመተው ምርጫ ላይ ከፍተኛ ድል ለማግኘት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ለፌዴሬሽን ምክርቤት ቅርበት ያላቸው …

መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አብዲ ሙሃመድ 7 የስራ አስፈጻሚ የኮሚቴ አባላትን ማበረራቸውን ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ በአስቸኳይ እንዲመጡ ቢታዘዙም፣ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል ጅጅጋ ውስጥ እንደሚገኙ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ተናግረዋል። ለአቶ አብዲ ቅርበት ያላቸው የመከላከያ ባለስልጣኖች በተደጋጋሚ ስልኮችን በመደወል አቶ አብዲን ለማግባባት እየሞከሩ ሲሆን  አቶ አብዲ በበኩላቸው ” ኢትዮጵያ ውስጥ 30 …

መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለሁለተኛ ዙር እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ስልጠና በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በአለመግባባት ሲቀጥል፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ተማሪዎች በመሰላቸት ውይይቶችን እንደማይከታተሉ ከተሳታፊዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። የተለያዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ተማሪዎች  ውይይቱ አሰልቺ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ የግሉን ስራ እንደሚሰራና ውይይቱን እንደማይከታተል ገልጸዋል። ለመምህራን በሚሰጠው ስልጠና ደግሞ በአንዳንድ የማሰልጠኛ ቦታዎች መምህራን ሃሳብ …