በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተነሳው አለመግባባት ቅራኔ ፈጥሯል።
በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተነሳው አለመግባባት ቅራኔ ፈጥሯል። #Ethiopia #Oromoprotests #Amharaprotests #TPLFArmy #EthiopianArmy #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi – mereja.com ከኬንያ የድንበር ኣከባቢና ደቡብ ሱዳን ቅጥረኛ ወታደሮችን ገዝተን ማሰራት እንችላለን ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ያደረግነውን በመከላከያ ውስጥ እንደግመዋለን የሚሉ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በሰሜን እዝ እና ምእራብ እዝ ከሚገኙ ወታደሮቻቸው ጋር በተነሳው ኣለመግባባት ቅራኔ መፈጠሩን የወታደራዊ ደህንነት ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል፥ ጉዳዩ የከረረ መሆኑ ለሕዝቡ ትግል ኣንድ እመርታ ያሉት ምንጮቹ የሃገር ውስጥ የተቃዋሚ ሃይሎች ስልታቸውን እንድፈትሹና እንዲቀይሩ ኣስፈላጊ ወቅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
የወታደራዊ ደህንነት ሱፐርቫይዘሮች የሆኑ ምንጮች በኣማራ ክልል የተነሳውን የሕዝብ የለውጥ እና የመብት ጥያቄ ተከትሎ በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ለመገምገም በተሰማሩበት የምእራብ እዝ እና የሰሜን እዝ ውስጥ ያለው ሁኔታ ኣደገኛና ሰራዊቱ ማብራሪያ በተከታታይ እየጠየቀ የሕወሓት መኮንኖችን መረበሹን ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል። በማስፈራሪያና በዛቻ ተከበን ማገልገል ኣንፈልግም ወደቀያችን መልሱን የሚሉ ወታደሮች እየበረከቱ የመጡ ሲሆን ከኦሮሚያ ክልል የተቀጠሩ ወታደሮች በይበልጥ ሰራዊቱን መልቀቅ እንፈልጋለን በማለት በሕወሓት መኮንኖች ላይ ጫና እየፈጠሩ በመገኘታቸው ኣለመግባባቱ በርትቶ ቅራኔዎች እየሰፉ መምጣታቸው ታውቋል። #ምንሊክሳልሳዊ

What do you mean by this =======> ” የሃገር ውስጥ የተቃዋሚ ሃይሎች ስልታቸውን እንድፈትሹና እንዲቀይሩ ኣስፈላጊ ወቅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። ”
An ideal situation would be if the soldiers side with the people and fight TPLF.
Of course we should not forget that the country needs a military now, during a transition period and later.
Imagine, without a military Egypt would bombard the big dam, Eritrea would invade etc.
Please we donot NEed aty disturb us
@ US decline:
First, let’s destroy TPLF.
It is the biggest enemy of Ethiopians.
Let’s build our unity.
እኔ በበኩሌ አይደረግም እንጅ ቢደረግ እንኲን ግብጽ ኣባይን ብትደበድብ ይሻላል ወያኔ አንድ ንጹህ ሰውን ከሚገድል
የኛ አገር መከላከያ ሠራዊት፤ፌደራል ፖሊስ፤አጋዚ፤አድማ በታኝ እና የመሳሰሉት የወያኔ አጋሰሶች የነሱ የውጊያ ችሎታ መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁአን ዜጎችን መግደል እንጂ ከውጪ ጠላት ጋር ውጊያ ቢጀመር የመጀመሪያ ፈርጣጮች ናቸው።ጀግና ቢሆኑ ኖሮ ወገኖቻቸውን አይገሉም ነበር።የፈሪ አመሉ ይህ ነው።