በጎንደር የተነሳው የሕዝብ ጸረ ወያኔ እንቅስቃሴ ተከትሎ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የምክር ቤት ኣባላት ላይ ሕወሓት ዛቻ ጀምሯል። ‪

#‎Ethiopia‬ ‪#‎Amharaprotests‬ : በጎንደር የተነሳው የሕዝብ ጸረ ወያኔ እንቅስቃሴ ተከትሎ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የምክር ቤት ኣባላት ላይ ሕወሓት ዛቻ ጀምሯል። ‪#‎MinilikSalsawi‬

እሪበይ ሀገሬ's photo.

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ሳንጃ እና ኣከባቢው ከባድ ውጥረት ላይ ነው፤ ዳንሻ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሔደ ነው። መስሪያ ቤቶች ዝግ ናቸው። ስሜን ጎንደር ሰራተኞች እና ነጋዴዎች ወደየስራቸው ባለመሄዳቸው እንቅስቃሴዎች በጣም መቀዝቀዛቸው ተሰምቷል። የኣማራ ክልል ምክር ቤት ኣባላት ስለጎንደር ሕዝባዊ ቁጣ እንዳንጠይቅ በስልክ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው ሲሉ ጠቆሙ፤ከትላንትና ወዲያ ለሊቱን የኣማራ ክልል ባለስልጣናት እና የክልሉ የጸጥታና ደህንነት ክፍል በፍጹም በማያውቀው መንገድ ከትግራይ ተነስተው ወደ ጎንደር የገቡት የሕወሓት የደሕንነት ሃይል ኣባላት እና የሕወሓት ልዩ ሃይል ወታደሮች የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ኮሚቴ አመራሮችን ለማፈን ያደረጉት ሙከራ ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ቁጣ ቀስቅሶ ሕዝቡ በስልጣን ላይ ያለውን ኣገዛዝ እንደማይፈልግ ከትግራይ ልዩ ሃይል ወታደሮች ጋር በመፋለም በጎንደር ከተማ ጀግንነቱን እያሳየ ይገኛል።

የሕዝቡን ቁጣ ተከትሎ ለሆዳቸው ያደሩ የብ አዴን ኣባላትን ሕዝቡን እንዲያዘናጉ ያሰማራው ሕወሓት በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ዛቻ ጀምሯል። ሕዝቡ በሕወሓት ኣገዛዝን እንደማይፈልገው በተግባር ያሳየ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የተነሳው የሕዝብ ኣመጽን በኣማራው ክልል ደግሞታል፤ ሕወሕት በክልሉ ለሚገኙና ከክልሉ ባለስልጣናት ጀርባ ላስቀመጣቸው የራሱ ሰዎች መረጃ በመስጠት የጎንደርን ከተማ ጥሶ ሲገባ እና ሕዝብን ሲያሸብር የጉዳዩን ኣሳሳቢነት የተናገሩ የክልሉ ባለስልጣናት ኣስቸኵዋይ ስብሰባ እንዲጠራ ቢጠይቁም ሕወሓቶች ከልክለዋቸዋል።የክልሉ ምክር ቤት ኣባላት እንዳሉት ማንነታቸውን የማናውቃቸው ሰዎች እየደወሉ ነው በማለት የገለጹ ሲሆን ስለ ክልሉ ጉዳይ ኣያገባችሁም ኣርፋቹ ተቀመጡ የደወልንበትን ቁጥር ኣሳልፋቹ ብትሰጡ ማን ጋር በየትኛው ቁጥር እንደተደወለ ስለተመዘገበ እንደፋቹሃለን በማለት እየዛቱ ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

4 Comments on “በጎንደር የተነሳው የሕዝብ ጸረ ወያኔ እንቅስቃሴ ተከትሎ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የምክር ቤት ኣባላት ላይ ሕወሓት ዛቻ ጀምሯል። ‪”

  1. Death for fascist TPLF. Keep going the brave great people of Ethiopia. We are always with you. If this continues, woyanes will vanish with in 15 days from our motherland Ethiopia. So the Amhara authorities, this is the time in order to stand with the people.

  2. ሰበር ዜና በጎንደር ክፍለ ሃገር
    ነጻ ነበርን አሁን ግን ነጻነት በሀገራችን ናፈቀኝ!ናፈቀን!
    ነባር ሕዝብ ከሃገሩ ሲባረር፣ሲገደል፣ስንገደል ወያኔ ትግሬዎችን በመሬታችን ገደሉ አጠፉን
    ሌለት ከትግራይ የመጣው አጋዜ በአባይ ወልዱ የሚመራው አፋኝ ቡድን ጎንደርን ወረሩይህች ናት ሃገር
    ውድ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ሃገራችን ሰው ሰው የምትፈልግበት ወቅት ነው! ሰው የሚፈተሸበት ወቅት ወያኔና ተባባሪዎቹ ጎጠኞች ሃገርን እያደሙ ነው!
    ራያና፣አለማጣ፣ኮረምም ትግሬ አይደለንም እያለ ባለበት ቀውጢ ጊዜ ነው ሕዝብ ጥንቃቃ ማድረግ አለበት! አደራ!አደራ!

    ሙሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*