የሕወሓት ባለስልጣናት ከአደባባይና መድረክ ለመደበቅ የወሰኑ ሲሆን ቀጣዩ የደህንነት ተቋሙ አሰራር ላይ መከሩ

የሕወሓት ባለስልጣናት ከአደባባይና መድረክ ለመደበቅ የወሰኑ ሲሆን ቀጣዩ የደህንነት ተቋሙ አሰራር ላይ መከሩ

‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎የግንቦት_20_ፍሬዎች‬ ‪#‎25Years_of_Tyranny‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የደህንነት ተቋሙ አሰራር በአዲስ መልክ ሊቀየር መሆኑ ተሰምቷል::አዲሱ አሰራርን በተመለከተ ጥናት መጀመሩን እና በደህንነት ተቋሙ ውስጥ ከሕወሓት አባላት ውጪ ሌሎች የሚኖራቸውን ሚና የሚገድብ መሆኑ ታውቋል::እንዲሁም ወታደራዊ ደህንነቶች መበርከት ስላለባቸው አዳዲስ ሰልጣኞችን በመሰብሰብ በሰራዊቱ ውስጥ ሊነሱ የሚችሉ ችግሮችን ማውደም እንደሚቻል ታሳቢ ተደርጎ አዳዲ ወታደራዊ ደህነቶች በጦላይ ስልታና እንዲሰጣቸው እንዲሁም የወታደራዊ ደህነት መኮንኖች እስራኤል እና ሩሲያ ሄደው እንዲሰለጥኑ አስፈላጊው ስራ እንዲሰራ ተወስኗል::ወታደራዊ ጄኔራሎች በሳምንት ውስጥ ብቻ ከደህንነት ተቋሙ ባለስልጣናት ጋር ከዚህ ቀደም በተሻለ በተከታታይ እየተገናኙ በሃገሪቱ ላይ የሚነሱ ችግሮች የክልል ባለስልጣናትን በማስቀደም በእንጭጩ በፍጥነት እንዲቀጩ ተወስኗል::

የግንቦት ሃያን የወያኔ በዓል ተከትሎ የሕወሓት ባለስልጣናት ወደ አደባባይ መውጣትን ሊቀንሱ ይገባል የሚለው ሃሳብ ላይ መመከሩ ለደህንነት ቢሮ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ገልጸዋል::በዚሁ የምክክር ስብሰባ ላይ አደባባይ ላይ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ እስካልተገኘ ድረስ ከፍተኛ የሕወሓት ባለስልጣናት ሕዝብ ፊት ሳይታዩ ከጀርባ ሆነው ስራ ለመስራት ተነጋግረዋል::በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ጥላቻ እያተረፍን ነው የሚል እደምታ ያለው አጀንዳ የተነሳበት ይህ ምክክር ከሙስና እና ከግድያ እንዲሁም ከእስር ጋር በተያያዘ በስፋት እጅ የሚጠቆመው በሕወሓት ባለስልጣናት ላይ እንጂ በሌሎች የኢሕኣዴግ አባል እና አጋር ድርጅቶች ላይ ስላልሆነ እንዲሁም የግንባሩ ድርጅቶች አባላት ሳይቀሩ እጃቸውን ሕወሓት ላይ መጠቆም እንደደረሱ በምክክሩ ላይ መተማመን ላይ ተደርሷል::ከዚህ ቀደም ከክልል ባለስልጣናት ይሁን ከፌዴራል ባለስልጣናት ጀርባ የሕወሓት ባለስልታናት እንዳሉ ቢታወቅም አሁን የታሰበው ለየት የሚያደርገው ግን በረቀቀ መልኩ ለማዘዝ የክልል ባለስልጣናትን ለመወንጀል መዘጋጀታው ነው::

ማንኛውንም ጉዳዮች በማስፈጸም እና በመተግበር ስራ ላይ ሊሰማሩ ይገባል ተብለው የታጩት በሃይለማርያም የሚመራው የደቡብ ድርጅት አባላት ሲሆኑ እንደ ኦሕዴዽ እና ብአዴን እስጥ ያሉ ሰዎች በጥንቃቄ ክትትል እየተደረገባቸው የሕወሓት ባለስልጣናትን ትእዛዝ እንዲፈጽሙ እንዲሁም ማንኛውም ትእዛዝ ለአንድ በክልል ይሁን በፌዴራል ለተመደበ ባለስልጣን ከሕወሓት ሰዎች በቃል ብቻ እንዲወርድ ተደርጎ ምስጢር እንዲጠብቅ እና አፈጻጸሙን እንዲተገብር ማበረታቻ ገንዘብ በማጉረስ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ማድረግ እንደሚቻል ከስምምነት ተደርሶበታል::በሕዝብ ዘንድ ማጉረምረም ቢከሰት ወዲያው ባለስልጣኑን በማሰር አሊያም በመቀየር እንደሁኔታው ወቅታዊ ትኩሳቶችን የተከተለ እርምጃ በልጥሎች እንዲወሰድ እንደሚደረግ ተመክሮበታል::የሕወሓት ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም እንደሚያድርጉት ፊትለፊት ድንፋታ እና ፊትለፊት በመጋፈጥ ማዘናጋት ማጭበርበር የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው እና ሕዝቡ እንደነቃ በምክክራቸው ላይ ከመተማመን መድረሳቸው ራሳቸውን ቀስ በቀስ ከሕዝብ መድረኮች በማሸሽ እና ጉዳያቸውን በትእዛዛቸው መሰረት ከሚፈጽሙት ጀርባ ሆነው ከቀደድሞው በተለየ በረቀቀ መልኩ ሊተገብሩ ተስማምተዋል::ቀጣዩ የፕሮፓጋንዳ ስራ የሚሆነው የፖለቲካው ስልጣኑ ከሕወሓት ሰዎች ውጪ እንደሆነ አድርጎ ሕዝብን ማሳመን እንዲሆን ይደረጋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

14 Comments on “የሕወሓት ባለስልጣናት ከአደባባይና መድረክ ለመደበቅ የወሰኑ ሲሆን ቀጣዩ የደህንነት ተቋሙ አሰራር ላይ መከሩ”

  1. What ever they said or belive it is too late now. Unless they give power to the people vote. That is the only solution they have.

  2. What ever plot is calculated Tplf old and new ones are as a fly inside the ointmment, they all are on the death row and the non stop burning fire is awaiting them:

  3. No room for Tplf masters what await them is to join the path of SADAM HUSSIEN AND GADAFI and this will be done soon.

  4. ነቅተናል ይህንን ስልታቸው ድድድድድድድድድድሮ ነው የበላነው ማንንም አያታልሉም አር የነካውን እንጨት ማን ያጣዋል

  5. Woyane / TPLF has failed totally and completely in its mission. Woyane is set out to destroy Ethiopia will in the end self-destruct. Ethiopians will continue to watch on the sidelines with aching hearts and bellies. They gnash their teeth and wag their index fingers asking themselves when the day of reckoning will finally arrive.

    Woyane and all Tigre accomplices know that behind the deafening silence of millions of Ethiopians and apparent passivity is boiling anger just like liquefied magma before it erupts in a volcano.

    Or perhaps it is like the proverbial finger in the dam. You can’t stop the dam from collapsing by sticking a finger in the hole of the dam. What happens when the dam finally collapses?

    There is no doubt about it. The day of reckoning for the Woyane and all Tigre accomplices will come “unexpectedly, like a thief in the night.”

  6. ሰውን ገድሎ ዶክተር
    ሰውን ገድሎ ሃብታም
    ሰው ገድሎ ስልጣን
    ሃገርን አጥፍቶ አዋቂ
    ፈላስፋ፣ምሁር፣ወታደር ስንቱን ስንቱ የዚህች ሀገር በደል ማቆሚያ የሌለው!
    አንድ ትውልድ እንኳን በቃ አይልም ወይ?

    ቢዋ

  7. you are talking your day night dream this useless kid propaganda is not give any sense except the fundamentalist group that ofyou and your diaspora the reality is beyond your ability.

  8. yedehininet tekuamu be-adiss aserar mekeyeru tegebi new mikinyatum ahun yalut abalat begibitawinet ena besimietawinet and(1) bota lay bicha bemekemet chat eyekamu bezuryachew yalutin gilesebochin joro-achew eskemibetes mamat new sirachew maninetachewim bekelalu yemileyu lebotaw yemayimetinu nachew?????????

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*