ዮሀንስ ሰሃሌ እና ምክትሎቻቸው ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ተነሱ

image

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የብሔራዊ ቡድኑ የአሰልጣኞች እና ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ከስራቸው እንዲሰናበቱ መወሠኑን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሪሽን ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የሆኑትን ኢንስትራክተር ዮሀንስ ሣህሌ ፣ ምክትል አሰልጣኝ የነበረው ፋሲል ተካልኝን ፣ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ የነበረው አሊ ረዲ ጨምሮ የብሔራዊ ቡድኑን እንቅስቃሴ የሚገመግመው የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሜቴ አባላት የነበሩት አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ እና እና ዶክተር ሲራክ ባጠቃላይ ከሀላፊነታቸው መነሳታቸውን ኢትዮአዲስ ስፖርት ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ማረጋጋጥ ችላለች፡፡

ፌደሬሽኑ በአልጂሪያ ብሊዳ ላይ ብሔራዊ ቡድኑ ከደረሰበት የ7-1 አሸማቃቂ ሽንፈት በኃላ በሩን ዘግቶ በዝግ ሲመክር እንደነበር ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ኢንስትራክተር ዮሀንስ ሳህሌ ብሄራዊ ቡድኑን ከያዙ ከአስር ወራት በላይ ያስቆጠሩ ሲሆን ብሄራዊ ቡድኑ 23 ጨዋታዎችን በእርሳቸው እየተመራ አድርጎ 11 ሽንፈት አስተናግዶ 5 አቻ ወጥቶ በ7ቱ ደግሞ ድል አድርጓል፡፡ 34 ጎሎች ሲቆጥሩበት ማስቆጠር የቻለው ደግሞ 25 ጎሎችን ነው፡፡

8 Comments on “ዮሀንስ ሰሃሌ እና ምክትሎቻቸው ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ተነሱ”

  1. አሰልጠኛችን ማበረር ውጤት አያመጣም
    ይህ ቤት በማን እንጅ እንዳለ ይታወቀል 1- ወያኔ፣2- ሻቢያ፣3- የጎጥ አቀንቃኞች
    ኮስ ቢያድግ ብሔራዊ አንድነትን ስለሚገነባ ባንድራን ከፍ ስለሚያደረግ የሕዝብ ትብብርን ስለሚፈጥር የብሔራዊ ቡድንን ማፍረስ ተገቢ ነው የኢትዮጵያ ጠላቶች
    እንኮን ደስ አላችሁ
    ሰ.አ.

  2. ምንም አይነት ብሄራዊ ቡድን አስፈላጊ አደለም! ምክንያቱም ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ለጥቂቶች ስለሆነች ብሄራዎ የሚባል ቋንቋዉ ብቻ ነዉ ያለዉ፡፡ እግርኳስ አይበላ! ብሄራዊ ዉርደት ባለበት ሰዓት ብሄራዊ ቡድን፤ መከላከያ የሚባለዉ የአንድ ብሄር ቡድን ይጫወት!

  3. እግሩም ላይ ወድቃችሑም ቢሖን የድሮውን አሰልጣኝ መልሡልን ፡፡ አጠፋውም አለማውም እሱው ይሻለናል ፡፡

  4. ሰዎች ምን ነካቸው የኳስ መጫወቻ ሜዳ የሌለበት አገር ላይ ስለ ብሄራዊ ቡድን ታወራላችሁ ገበጣ ብንጀምር ይሻለናል

  5. This is to

    ሰ.አ

    Why are you mixing politics with sport? What if any Weyana got to to do with the team’s bad performance?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*