ማስጠንቀቂያውን እንስማ፤ ኢትዮጵያ በአደጋ ላይ ናት! ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ
ማስጠንቀቂያውን እንስማ፤ ኢትዮጵያ በአደጋ ላይ ናት!
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ
ታኅሣሥ 1፤2008ዓም
አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ስለ ልጇ እንዲህ አለች፡ “ልጄን በጥቅምት ወር ለትምህርት ላኩት በኅዳር ሬሣውን ለቀብር ተቀበልኩ!” ይህች እናት የሁላችንንም ወላጅ እናት የምትወክል ናት፤ ኢትዮጵያን እና በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ላይ ያለውን ሁኔታም በግልጽ የምታሳይም ናት፡፡ ሟች ልጇ የሷ ልጅ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ወላጆች ልጅ፤ ወንድም የሚወክል ነው፡፡ ይህ ልጅ የእናንተን በህወሃት ውስጥ ያላችሁትን የሥርዓቱ መሪዎች፣ ተላላኪዎችና አጎብዳጆችን ልጅ የሚወክልም ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ግፍ እና ሰቆቃ በአንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ላይ ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዱ እናት ላይ እየደረሰ ነው፡፡
እናንተም እንደ ሰው ከእናት በመፈጠራችሁ ይህ ስቃይና መከራ አይደርስብንም፤ አይነካንም ማለት አትችሉም፡፡ ከሕዝብ ለመሰወር ብትሞክሩ እንኳን ሁሉን ከሚችል ፈጣሪ በጭራሽ መሰወር አትችሉም፡፡ ስለዚህ ይህ ሰቆቃ እና ስቃይ በአስቸኳይ መቆም አለበት!!
ሰሞኑን በአገራችን እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በገሃድ እየተመለከትን ነው፡፡ በተለይ ከሁለት ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተወሰደው አቋም እጅግ የሚያስደንቅና የሁላችንንም ዕይታ የሳበ ነው፡፡ ተማሪዎቹ እንደተለመደው ወደ መመገቢያ ቦታቸው ሲደርሱ ምግባቸውን ወስደው በሥፍራቸው ተቀመጡ፡፡ ወደ ፈጣሪያቸው እየሞቱ፣ እየተሰቃዩና እየተራቡ ለሚገኙት ወገኖቻቸው ጸሎት አደረሱ፡፡
ከምግቡ አንዲት ቁራሽ ሳይቀምሱ ከተቀመጡበት በመነሳት ምግቡ ጠረጴዛው ላይ በመተው የመመገቢያ አዳራሹን ለቅቀው ወጡ፡፡ 15 ሚሊዮን ወገናቸው እየተራበ፣ ሌላው ደግሞ እየተፈናቀለ፣ እየተገደለ፣ የመኖር ኅልውናውን እያጣ በሰላም እየበሉ ለመኖር እንደማይፈቅዱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሳዩ፡፡
ተማሪዎቹ ስለወሰዱት እርምጃ ብዙ መባል ቢችልም ይህ ዓይነቱ የሰላማዊ ተቃውሞ ደም በማፍሰስ ከፍተኛ ብቃት ላካበተው የህወሃት ጠብመንጃ አንጋች የሚመቸው አካሄድ አይደለም፡፡ ሰላማዊ ትግል ማለትም ምን ማለት እንደሆነ ተማሪዎቹ በገሃድ አሳዩ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በሌሎች ከፍተኛ ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችም ተመሳሳይ ዕርምጃዎች በመውሰድ ለወገናቸው ያላቸውን ተቆርቋሪነት በግልጽ አሳይተዋል፡፡ የዝቅተኛ ትምህርት ተማሪዎች፣ የሆስፒታል ሠራተኞች፣ የተለያዩ መ/ቤት ሠራተኞችና ነዋሪዎችም ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ በማድረግ በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላማዊ መሆኑን በሌላ ደግሞ የሰላማዊ ትግል ብቃትና ፍሬያማነት አሁንም በኢትዮጵያ መሥራት እንደሚችል እያስመሰከሩ ነው፡፡
ኢትዮጵያን እንደ እህል በዘር መደብ ከፋፍሎ እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) የትግራይ ሕዝብን በፍጹም የማይወክል ቢሆንም አሁንም “በነጻ አውጪ” ስም አንድን ክልል ለማስገንጠል በቆመ ዓላማ ኢትዮጵያን በግፍ እየገዛ ነው፡፡ ከአነሳሱ ጀምሮ በራሱ ውስጥ የነበሩና አሠራሩንና ዓላማውን የተቃወሙትን ሁሉ በመግደል፣ በማሰር፣ በማሰቃየት የጀመረው በሟቹ መለስ ዜናዊ የተመራው ህወሃት ጨካኝነቱን ነጻ አወጣዋለሁ ባለው ሕዝብ ላይ አለገደብ ሲያሳይ ከቆየ በኋላ ወደ ሥልጣን መንበር ሲመጣ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ዘመቻውን አድርጓል፡፡ ሲጀምር አማራ ብሎ የሰየመውን ሕዝብ ማጥቃት ተያያዘ፤ ቀጥሎም ከአርባ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያ በውድ ያስተማረቻቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የከፈሉትን ዋጋ እንኳን ከቁም ነገር ሳይቆጥር በሁለት መስመር ደብዳቤ ከማስተማር ሙያቸው አባረረ፡፡ ግፉ ቀጠሎ ሲዳማዎችን፣ አኙዋኮችን፣ ለቅንጅት ድጋፍ የወጡ ሰልፈኞችን፣ በዖጋዴን ሶማሊዎችን፣ አፋሮችን፣ ማጃንጂሮችን፣ ቤንሻንጉልና ጉምዞችን፣ የኦሞ ሸለቆ ነዋሪዎችን፣ በደቡብ በርታዎችን፣ በሱዳን ጠረፍ የሚገኙ ገበሬዎችን፣ ሙስሊሞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የዴሞክራሲ አራማጆችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮችን፣ የከተማ ነዋሪዎችን፣ ሲገድል፣ ሲያስር፣ ሲያሰቃይ ቆይቶ አሁን ደግሞ ከዚህ በፊት ያደረሰው መከራ ሳያንሰው በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የበቀል በትሩን እየዘረጋ ነው፡፡
ይህ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ብቻ የተቃጣ ሳይሆን ሁላችንም በእያንዳንዳችን ላይ እንደተቃጣ ግፍ አድርገን ልንወስደው ይገባናል፡፡ የሚፈሰው የኦሮሞ ደም አይደለም፤ የሰብዓዊ ፍጡር እንጂ፡፡ ዘር፣ ጎሣ፣ ወገን፣ … የተለያየ ደም የለውም – ሁሉም ሰው በፈጣሪ በእኩልነት የተፈጠረ የአምላክ ድንቅ ሥራ ውጤት ነው፡፡ ስለዚህ ትግሉም፣ ተቃውሞውም የአንድ ቡድን ወይም የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን የትግራይ ሰዎችንም ጨምሮ የመላው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡
አለበለዚያ የወገንና የጎሣ አድርገን የምንወስደው ከሆነ ከዚህ በፊት እንደተካሄዱት በአንድ ወቅት ተነስቶ የሚጠፋ ወደሌላው ቦታ ለመቀጣጠል የማይችል፤ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ውክልና የሌለው፤ ከጥቅሙ ጉዳቱ እጅግ የሚበልጥ፤ ጭፍን፣ ጠባብና ለህወሃት ዕድሜ ማራዘሚያነት የሚያገለግል ቶሎ የሚዳፈን ግብታዊና ወቅታዊ ዓመጽ ሆኖ ነው የሚቀረው፡፡ ስለዚህ ይህንን የሕዝብ እንቅስቃሴ በሰብዓዊነት መነጽር ለማየት የማይፈልጉ ሁሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊወስዱ ይገባል፡፡ ጎሣቸውን ወይም ሕዝባቸውን ነጻ እናወጣለን ብለው ህወሃት ካደረሰው ጉዳት እጅግ የከፋ ውድመት ሊያደርሱ እንደሚችሉ በጥብቅ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ሌሎችም ኢትዮጵያዊያን “እኔን አይመለከተኝም” በሚል አስተሳሰብ ከዳር ለመሆን የሚፈልጉ ሁሉ ትግሉን ጎሣዊ ለማድረግ ከሚመኙት ያልተናነሰ ጉዳት እንደሚያደርሱ እነርሱም በጥንቃቄ ሊያዩት ይገባል፡፡ የአንድ ሰብዓዊ ፍጡር ደም መፍሰስ የራሳቸው እንደሆነ አድርገው ካልወሰዱት ጉዳቱ የራሳቸውን በር ሲንኳኳ የሚደርስላቸው ያጣሉ፡፡ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንዳትኖር ወደማድረግ የሚያደርስ የጥፋት ቁልቁለት ነው፡፡ ለዚህም ነው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) “ከጎሣ ይልቅ ሰብዓዊነትን እናስቀድም” በሚል መሪ መፈክር አንቅስቃሴውን የሚያካሂደው፡፡ከሰብዓዊነት በፊት ጎሣን፣ ወገንን፣ ዘርን፣…ማስቀደም ህወሃትን መልሶ በሥልጣን ማስቀመጥ ነው፡፡
በሕይወት በነበሩ ጊዜ ኢትዮጵያን በጎሣ ከፋፍለው ሲያበቁ በሕዝብ ለመወደድ ብለው “ሕዝብ ከሸፈተ ሠራዊት አያቆመውም” የሚል ንግግር መለስ ዜናዊ ስለማድረጋቸው ይነገራል፡፡ በወቅቱ ሕዝብ ያሉት ለተገንጣይ ቡድናቸው ድጋፍ ይሰጣል ያሉትን ሊሆን ቢችልም አነጋገራቸው ግን አሁን በአገራችን ከሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ እውነትነት አለው፡፡ ህወሃት ሁሉንም ሲያደማ ስለኖረ አሁን ሕዝብ ሸፍቶበታል፡፡ ይህንን ሐቅ ማመን ስላልፈለገ ግን ሠራዊት አሰማርቶ የሕዝብን ቁጣ ለማፈን የሚቻለውን ሙከራ እያደረገ ነው፡፡ ሌጋሲያቸውን እንጠብቃለን እያለ በሙት መንፈስ የሚመራው ህወሃት መሪው ያሉትን ቃል ቢሰማ ጥሩ ነው፡፡ እስካሁን ያሠማራውም ሆነ ወደፊት ሊያሰማራ ያሰበውን ሠራዊት ሁሉ ቢጠቀም ሕዝብ እስከሸፈተበት ድረስ በየትኛውም ዓይነት ሠራዊት ሊያስቆመው አይችልም፡፡
ህወሃት “ትጥቅ ትግል” ባለው የበረሃ ጉዞው ላይ በጠብመንጃ አፈሙዝ ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ ሲያገኝ እንደነበረው ሳይሆን አሁን አገር እየገዛ ነው፤ ህንጻም፣ መንገድም፣ … ሠርቷል፤ የጦር ሠራዊት ጡንቻውንም አዳብሯል፤ ገንዘቡን ተቆጣጥሯል፤ ብዙ ዘመናትም ለመግዛት ቋምጧል፤ ሕዝብ ከሸፈተበት በኋላ ግን ዲስኩር የነፋባቸው ህንጻዎችና መንገዶች ማንንም አይሸሽጉም፤ ሠራዊት ብሎ ለራሱ ያደለበውም ኃይል ማንንም መከላከል አይችልም፤ የሸፈተን ሕዝብ ምንም አይገድበውም፤ ማዕበል ነው፤ ጎርፍ ነው፤ ሱናሚ ነው፡፡ ስለዚህ እናንት የህወሃት ሹሞች በእጅጉ ተጠንቀቁ! በንጹሃን ተማሪዎች ላይ የጠብመንጃ ቃታ እንዲሳብባቸው የምታዙትን ሠራዊት አቁም በሉት፣ ካልተባለ ነገ ቃታውን ወደ እናንተ ለማዞሩ ምንም ዋስትና የላችሁም፤ በችጋር የሚያልቀውን የኢትዮጵያ ሕዝብና ህጻናት እንደ ራሳችሁ ሕዝብና ልጅ ተመልከቱት፤ የሙት ሌጋሲ ለመጠበቅና ለልማት በሚል ከንቱ “ውዳሴና ህዳሴ” የምታፈናቅሉት ምስኪን ገበሬ ስቃይ ይሰማችሁ፣ የፈጣሪ በትር የተመዘዘ ዕለት የእናንተም ጽዋ ከዚህ እንደማያልፍ በቀረው ጥቂት የማሰብ ኅሊናችሁ ለማስተዋል ሞክሩ፡፡
አገራችን በአደገኛ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡ ማስጠንቀቂያው ለሁሉም ነው፡፡ በአንድ በኩል ደም ከማፍሰስና ከመግደል በቀል የአእምሮው ክፍል ምንም ማሰብ የማይችል ጨካኝ ሠራዊት በመግደል ፈንጠዝያ ላይ ነው፤ ከጌቶቹ በተሰጠው ትዕዛዝ ብዙ ለመግደልና ደም ለማፍሰስ ጠብመንጃውን ወልውሏል፤ በሌላ በኩል ደግሞ አገራችንን በጎሣ፣ በዘር፣ በወገን፣ በሃይማኖት ለመከፋፈል ያሰፈሰፉ የውስጥና የውጭ ኃይላት ሕዝባዊ ዓመጹን የራሣቸው ለማድረግ ቋምጠዋል፡፡ ሕወሃት ለ24 ዓመታት ያመቻቸላቸው ዘረኝነትና ጥላቻ ለዚህ እኩይ ተግባራቸው መንገዱን ወለል አድርጎ ከፍቶላቸዋል፡፡ ሁሉም ማቆም አለባቸው!!
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” በሚለው ቀዳሚ ዓላማው መሠረት “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን በስተቀር ማንም ብቻውን ነጻ መውጣት አይችልም” የሚለው መርህ አሁንም በተግባር ላይ መዋል አለበት ብሎ ያምናል፡፡ ስለዚህ ማንኛውንም የሕዝብ እንቅስቃሴ ለራሳችሁ የግል፣ የጎሣ፣ የወገንና የሥልጣን ጥማት ማርኪያ ለማዋል ያሰባችሁ ከህወሃት ተማሩና ትግሉን ለመቀልበስ የምታደርጉትን ሙከራ አቁሙ፤ ይህ የሕዝብ ትዕይንት ነው፤ እናንተ በዘር በሽታ የተለከፋችሁ እና መፍትሔ በጠብመንጃ አፈሙዝ እናገኛለን ብላችሁ የምታምኑ የህወሃት ሰዎች ወደ ኅሊናችሁ ተመለሱ፤ ቀን ሳለ አሁን ልባችሁን ክፈቱና ዋይ በሉ፤ የሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ የአምላክ በትር በእናንተ ላይ ሳይወርድ በማጭበርበርና በማታለል ወይም በውሸት ሽምግልናና ዕርቅ ሳይሆን ከልብ በመነጨ ቅንነት የሕዝብን ጥያቄ መልሱ፡፡
የገነባችሁት ሁሉ አልሰራ ብሎ በራሱ መፍረስ ከጀመረ ቆይቷል፤ ይህ ደግሞ በጥገና እና ቀዳዳ በመድፈን አይስተካከልም፡፡ የድርብ አኻዝ የኢኮኖሚ ዕድገት እያላችሁ ለዘመናት ስትዋሹ የኖራችሁበት ዲሰኩር በችጋር ዓይኑን አፍጥጦ በገሃድ ታይቷል፡፡ ሁሉም ነገር አብቅቶለታል፡፡ አሁን ካለበት የከፋ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት አቁሙ! የኢትዮጵያውያን ደም የፈጣሪ ደጅ ከደረሰ ቆይቷል፡፡ የእርሱን ዝምታ እንደ ስንፍና ከቆጠራችሁት የበቀል በትሩን ሲዘረጋ የገተራችሁት ፎቅና ያደለባችሁት ጦር በጭራሽ አይመክተውም፡፡
የአምላክ ፍርድ በሕዝብ ምሬትና ቁጣ ይገለጻል፡፡ ያንን ለማብረድ ጊዜው አሁን ነው፤ የጋራ ንቅናቄው በዚህ ጉዳይ ላይ ከማንኛውም ይመለከተኛል ከሚል ጋር ለመሥራት አሁንም ፍላጎቱን ያለው መሆኑን ያስታውቃል፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ ባላችሁበት ኅብረተሰብ ዘንድ ተደማጭነት ያላችሁ ሁሉ በሁሉም መስክ ባገራችን ላይ የተነጣጠረውን መቅሰፍት ለማርገብ የሕዝብ ድምጽ መሆን የምትችሉበት ወሳኝ ጊዜ አሁን ነውና ድምጻችሁን አሰሙ፤ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ከጎናችሁ ነው፡፡
አምላክ የፈሰሰውን ደማችንን ያብስልን፤ ቁስላችንን ይፈውስልን፤ ለለውጥ በግል ወይም በጥቂት ቡድን ወይም በጎሣ ወይም በዘር ሳይሆን በአንድነት ለአንድ ዓላማ ለመነሳት እንድንችል ራዕይ ይስጠን፡፡
ዓይናችን እውነትን ለማየት ብርሃን ይስጠን፤ ጆሮዎቻችንም እውነትን ለመስማት የተከፈቱ ይሁኑልን፤ ኅሊናችንም እውነትን ለመረዳትና በተግባር ለማዋል የወሰነ ያድርግልን፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ
የበለጠ መረጃ ለማግኘት የጋራ ንቅናቄውን ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶን በዚህ አድራሻ ማግኘት ይቻላል፤ [email protected]

True ethiopian!
Dear Ato Obang, I have the utmost appreciation for your insightful advice to the Ethiopian people. I think, TPLF managed to destroy Ethiopia not because of its strength but our own weakness to think as a human being created in the image of God. It is because our inherent greed for our own exceptional benefit at the expense of others. It is because we follow the segregation of our selves into ethnic enclaves as prescribed by the TPLF regime. It is because we failed to understand the trap TPLF was laying for us. It is because our militant ethnic leaders brainwashed us that we are not incompatible with the rest of humanity out of our fence called ethnicity. It is because we failed to learn from Sudan, Libya, Iraq, Ruwanda, Nazi’s Germany tragedy or racism. And it is because we are at each others throat while our common enemy is ruining our nation. I think it is time to revisit and admit our own weakness and project a new paradigm that the rest of the world successfully utilized to grow together.
Again, my hats off for you my beloved brother – Obang Metho.
God bless you and God bless Ethiopia.
Correction:
Dear Ato Obang, I have the utmost appreciation for your insightful advice to the Ethiopian people. I think, TPLF managed to destroy Ethiopia not because of its strength but our own weakness to think as a human being created in the image of God. It is because our inherent greed for our own exceptional benefit at the expense of others. It is because we follow the segregation of our selves into ethnic enclaves as prescribed by the TPLF regime. It is because we failed to understand the trap TPLF was laying for us. It is because our militant ethnic leaders brainwashed us that we are not compatible with the rest of humanity out of our fences called ethnicity. It is because we failed to learn from Sudan, Libya, Iraq, Rwanda, Nazi’s Germany tragedies of racism. And it is because we are at each others throat while our common enemy is ruining our nation. I think it is time to revisit and admit our own weakness and project a new paradigm that the rest of the world successfully utilized to grow together.
Again, my hats off for you my beloved brother – Obang Metho.
God bless you and God bless Ethiopia.
ከወሬ ያለፈ ነገር የላችሁም እናንትፕ የኢህኣዴግና በተለይ የትግራይ ህዝብ ጥላቻ እንጂ ያገር ፍቅር ፈፅሞ የላችሁም
mereb
Qenachihu dersowan !!
wagahin tagegnaleh !!!
ye weyane rucha,, kaf eske afincha new !!!!
igzer awakinew
በጋራ ሆነን ወያኔን እንደምሥሥ
Hhhhhh no more ethiopia is ortodox.bye bye viva oromia.no more ortodox yeseytan zer.
የኦሮሞ ምሁራን ነገ ሳትሉ ዛሬውኑ ወጣቶቻችሁን ከዘር አጥር ብታወጡ አዲሱን የኢትዮጵያ ታሪክ ምዕራፍ በወርቅ ቀለም ለመፃፍ አጋጣሚው ተፈጥሮላችሁዋል።አሁን ምርጫው ወይ ተባብሮ ወደዘላለም ነፃነት ወይ በዘር ተክፋፍሎ ወደዘላለም ባርነት ነው።
Lemegbabiya red=qey, priest=qies
to get=magñet, amharic=amareña
television=televixn, buyer=gex, sand=TeTer, ape=ToTa, salt=cew
fatty meat=coma sga
The uprising is gaining momentum increasingly. There are honest and true LIBRAL majority in ethiopia today who can understand the reallity on the ground. Our Enemy number ONE is TPLF. Oromos, Amharas & Tigres have shown their solidarity in practice by joining the oromo rallies against TPLF in the Cpital and cities around the world. This is a good step in the right direction.
But I would like to express my disapointment with some comments who are emphasizing demagoguery inorder to high jack the revolution to their old system. That is not going to hapen. The tactic is not going to work.
Let us agree on ceasefire among oromos, amharas and tigres minus wuyane !
Woyane wodeseltan simeta Dergen bechawn altefalemewum- Behuala kedachew enje.Egna gen be andenet bemetemamen yegara telatachenen lezeleketaw enasewoged. Zeregnenet-tebabenet ye ewket manes meleket new.Zeregnenet endemayetekmen ke woyane tefat enemar. Andenet hayel new! Del lesefiw hezb! We need change!!!
Can you explain more by what you mean “hijacking to the old system” ? Which is the old system you are referring to, the derg,haile selssie or tplf ? I do not see any one group strongly organized to hijack at this point except tplf. I am waiting for an honest answer.
Ato Isubalehu,when you say old system,which old system which one ? ? In every step we have gone from bad to worse and i am finding it hard to which old system.
TEBALE ! TEBALE INDE !
ANTE ARAM ! YEMETAWKEW
FESS MEFSAT NEAW .
YEWONDOCHUN YET
Tawkewaleh Fesam .
እንኩዋን ተነጣጥለን ተባብረንም ወያኔን ለመጣል ቀላል project አድርጎ ማየት ትልቅ ሞኝነት ነው።ወያኔ እኛን ለማጋጨትና ለመነጣጠል ብዙ መድከም አያስፈልገውም። ጠብን በሁለት ሰወች መካከል ለመዝራት እጅግ በጣም ቀላል ነው።አሁን አንድ ሰው “ሚስትህን እኮ ክእከሌ ጋር ሬቶራንት በልተው ሲወጡ አየሁዋቸው” ቢላችሁ ምንም ብትዋደዱ በውስጣችሁ ጥያቄ ማሳደሩ የማይቀር ነው። ወያኔ 25 ዓመት ያራብን በእንደዚህ ዓይነት ቀላልና ብዙ ድካም በማይጠይቅ እርካሽ ዘዴ ነው። በቅዱስ ቁራን ገፅ ማንም ክርስቲያን ሽንት ቤት ገብቶ ሊጠቀም በፍፁም አያረገውም። እነሱ ግን እስላምና ክርስቲያኑን ያጋጭልናል በሚል እሳቤ አድርገውታል።አሁን ደግሞ አንዋር መስጊድ ቦምብ አፈነዱ።ቀስ ብለው ደግሞ ከዌስተርን መዝናኛ ወይንም ኤምባሲ ሊያፈነዱ ይችላሉ።በስልጣን ለመቆየት ይጠቅመናል ብለው እስካሰቡ ድረስ ምንም ነገር ከማድረግ ወደሁዋላ አይሉም።አሁን አማራ እና ኦሮሞን አገርቤት ውስጥ ለማጋጨት አዲስ እቅድ ነድፈው በስራ ላይ ለማዋል እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው እየተሰማ ነው። Let us not undremine our enemy! ! ! ! They have the easiest role to play and we have the hardest role.
My brothers all the vedio
and the pictures you viewing
are FAKE. It shows the
recent uprising in
BURKINAFASO. WHAT A LIE !
DRAMA ! DRAMA !
SEAW LE SEAW .ARAM .
Anti Civilization!
Shame on you ! How a
Human being hate development.
they are backwards.
It’s funny! How do you
imagine to make an uprising
in social media where there is literally no Internet in
the entire nation.
IT’S LIKE THE CART BEFORE
THE HOUSE !
I’m confused by the Oromo protesters when I look to their banner signs and slogans. Their banner sign is their party’s OLF flag and their slogan is free Oromia as the terrorist Jawar Mohammed’s slogan dedicated in the past time protest held in Minnesota. I’m very worrying when I can’t see my Country’s(Ethiopia) pride flag(Arenguade, Bicha, Red) in this protest. What can I say now is if they are true Ethiopians let show and carry the flag other wise their effort will remain fruitless. Unity is strengthen. God bless Ethiopia!
In general I don’t believe
In any form of uprising
where Political parties are
not reliable.
@ temelkach,
Yes, it is the king’s, the dergue’s and the wuyane’s regimes I was refering to. I hope you agree with m
እውነት እግዚዓብሄር ማለት ነው ኢትዮጵያን
ለማፍረስ የተነሱ የባቢሎን ግንብ እንደተናደ
ሁሉ ይፈርሳሉ በተንኮላቸው ይወላከፋሉ
ተኢትዮጵያ ዓምላክ ይፈርዳል!!!
Ato Isubalehu,going back to the derg,may be.But going back to the nigus where a few who belived that god sent them from heaven to rule over incorrigible is not possible.Now having said that if you think we can achieve our freedom from woyane without creating a strong unity good luck.I understand you are an ethnic scholar.
I don’t understand
What some Muslim people
are saying about the recent
incident that happened in the
Mosque , The cause for the explosion is under investigation why are always
middling before the final
Conclusion of the investigation ? One thing I
observing is they always have
a tendency of denial.
What kind of thought it is ?
They never accept or regret
for wrong doing rather they
rush to defined what ever the
outcome. It’s a disgraceful.
What an observant !!
Its absolutely right.
Obang metho the great man.God bless you.Its time to stop the tigre mercenaries once and for all.We all have to stand together and get rid of the Terrorist org.before they burn down our mother land and kill many million.I have no doubt that its TPLFs conspiracy to the Bomb explosion in Anwar Mosque.Now we all have to concentrate and support both the Armed and peaceful struggle.I am Andargachew and ESAT is mine.Death to TPLF and Hodams.God bless Ethiopia.Humanity before Ethnicity.
ke mililik eske derg yalew sreat yeamharawoch new blachu neber lemn ? amhara ethiopiyawi slehone amharan atftachu ageritun lemekefafel yalemachut hlm new weyani tgri eNa yalalefeln be amhara mknyat new sil oromow degmo amharaw oromon krstiyan eyale werona chefchfona slezih yerasachew yehone ager beamhara mknyat ethiopiyawi aydelenm eyalu lezerochachew nesanet amharan zer bematfat agerun bemekemat endemiyametu hwehat weyanim hone yeoromo tegentay betekawaminet komn silu yeneberu hulu hlmachewn behwehat lemasakat mannetachewn hwehat endametalechew amharan atfto oromonetachewn asawekeln bemalet beteleyayu guziat ethiopiya yemtbal ager ketefelegech amharaw yetntun sreat kaltemelese blo kalale eyalu eko ahun 25 amet keweyaniga amharan chefchfew yeamharan sreat atefan eyalum weyanin lemababel amharawn teteyaki lemadreg sikatachew yeneberu yeoromo yezer lhikanoch sltan lemeyaz ena neSanetachewnm keweyani lemekebel poletika yemiserut beamhara sm neber gobez beteley ye oromo yezer lhikanoch weyani bechakam hone sltan yzo bewananet yeseraw kenate ganew begara amharn ke ethiopiyawinetu lematfaT yasfelegachu yerasachn oromiya yemtbal ager kartachnn weyani sltan yzo asdkolnal bemalet neber enatem degmo hwehat bezih poletika amharawn endikotater be amhara sm tgin endiyaskemt werera endiyakahid endihum amharn lemewrer kenatega sisera lilawn gabilawn sumaliwn afarun….beamhara yderesebetn zer matfatna werera hwehat bchawn endikotater eredtachutal zari ke 25 amet behalam enaten oromiya yemtbal ager esetachuhalew lemegentel meserat yalebetn neger ensra amharan kalatefan selam yelenm bemil ena ethiopiyawinen yemilewn hulu beamhara sm bemayet yegeza zerochachun hulu staschefechfu neber slezih ahunm sle ethiopiya tarik beamharana beoromo mekakel man werari tewerari endehone ena ahunm bekel lemebekakel kehone endalachut beteley DR. meraram honu Dr. bekele gerba ethiopiya yemtbal ager ketefelegech weyani yametalachun yezer kll amharam hone ethiopiyawiyann mekebel alebachu kehone tesastewal mnm keweyaniga betekawaminet bnkomm be astesaseb ye oromo hzb tagayoch yemismamut ke hwehat gar new tesmamtew yenorutm kehwehat gar new slezih adis lewt lelilewn astesasebachew ethiopiya yemtbal ager ketefelegech eyalu masferarat new weys mn neber? ahunm wedefitm beamhara hzb lay be ethiopiya tark lay yeteseraw propagandana oromo kelal hzb adrgew endetewerere ena ezih endederese bemarageb gentayna asgertay hayloch yeserutn sira ena hzb yaschefechefutn ager yasatutn mknyat kegl tkmachew ena sltan lemeyaz blew ethiopiya yemtbal ager ketefelegech kemilu kerasachew jemrew eni ethiopiyawineN le ethiopiyawineti etagelalew kalalu ena ahunm leoromo hzb tewekay yasfelgewal bemalet endalut lemanm be ethiopiyawinetm hone bezerm neSanet aymetam mknyatum man ager kemto man tekemto ynoral yh astesaseb be ethiopiya tarik wst alseram mililikn bcha sayhon kezam befit beneberechew etiopiya tarik alseram ethiopiyan melilik lemejemeriya gzi alfeteratm ortodoks krstnam be ethiopiya bhir bhireseboch wst yetesfafaw le oromowm bihon bemililik zemen aydelem yemetalet tarikachnn hulachnm enawkalen
First we have to Identify what want. What is our problem ? What do we want ? In my humble opinion we the Oromos and the Amharas are the problem. We are our own worst enemy. We don’t know what we want. Amhara calls oromos are “Tegentawoch” and Oromos call Amhara are “Colonizers”. To be honest it is not the TPLF that devided Ethiopians. Ethiopia has a nation state formation problem since its Invention.
Know we face an existential threat from the fascist TPLF. Then what is the solution ? Again I believe we have (Amharas and Oromos) a common denominator that tie us together if we really want to defeat wuyane we have to come together with out any precondition. We the ordinary people have take the initiative and form a willing allians immediately without further delay. Let our political leaders negotiate the political part of it in the meantime.
No more short cut to power.Democracy, Democracy and Democracy.
awo and lay lememtat yeand ager ziga mehonachnn lemasayet bemejemeriya oromowoch beweyani zemen bandira keyrewal ethiopiyan ende agerachew abatochachew endaweresachew yemiyamnu kehone lezach ager zeri amharaneN oromoneN …eyetebale lemibalew mannet yetemotew be aregadi key bicha bandira new yh bandira yehulum bhir bhireseb ageru mannetu ethiopiyawi mehonun yasawkal beterefe yezer kll beweyani sereat amhara yemibal kll tefetral oromiya yemtbal kll tefetralech yh bewstu yalu zigoch yezih kll aydelehm kankachnn atnagerm bemalet endagerh endatnor endatsera kemadreg besteker yegara ager endalen masaya aydelem slezih oromona amhara and lay lemesrat beteley oromowoch yezer kll ayasfelgm sibal yamharan sreat yalefutn sreatoch lememeles eyalu propaganda mawrat makom alebachew ethiopiya malet yeamharana yeoromom bcha aydelechm 81 bhiroch slalu ende ager metaseb alebet lilaw wanaw beoromonet ena beamharanet mederajet sayhon be ethiopiyawinet mehon alebet mknyatum oromo bchawn oromon enji ethiopiyan ayweklm amharam endezaw slezih sle and ager ketasebe zer ayasfelgm awo yeoromon kanka bahl adabralew yemil ziga lilawnm mahbereseb mastemar ychlal enji bezer tekolfo ye oromo bahlna kanka yemiyadgew be oromo bchanew malet aychalm yeamharm endezaw lenegeru enkan behalu kankaw legebaw zeru yetedebelaleke hzbnew weyani yemiwedkew oromom amharam and nenn ethiopiyanoch nenn blo kaltenesa bemnm teamr yeweyani banda yefasisht sreat aywedkm slezih hzbun amharana oromo eyale yemikefaflh mannethn lilyatefanew blew yezer lhikanochm weyani sheweden kemilu weyani hasabun keyro simeta asabachewn mekeye mechal alebachew wed befitu lnameranew wede amhara sreat yemibalew teret teret biyabeka tru new weyani werera new yeyazew tgri liliawn bezer kolfo bezer lhikanoch amakaynet yale kll eko beamharam hone beoromo bedebub begabila negadiw fok seriw investeru yefilm akteru hulu sayker ensu nachew lemehonu kllu tadiya enesu bageritu tezewawrew endeagerachew kenoru lilaw lemn yezer kll asfelegew ? slezih oromona amhara begara lemesrat menesat alebet
ykrta ye ethiopiya bandira aregadi bicha key new yhnn mamen alebn
no bad nation in ethiopia.dirty poletical men made the conflict among nations.citizen… Inshort united people will win even evil dictators.
I don’t support the Oromos I would
rather prefer Woyane . the Oromos
have attacked the Amharas multiple
I don’t believe them at all .
that is absolutely right .
+t+++++ ባንዳና ጉጅሌ። +++++++
++++++++++++++++++++++
በ«በቃ!!»ተቋጭቷል፣መጨረሻው ቃሌ፤
በፍፁም አይኖሩም…፣ባንዳና ጉጅሌ።
በዘመን ልዩነት ፋሺሽት የሰራቸው፤
እርጉም እንደሆኑ ቆየሁ ካወቅኳቸው።
ለዓመታት አምርሬ፣
ቆሜአለሁ በግሌ፤
“ለምን ኖሩ?”ብዬ ባንዳና ጉጅሌ።
አርበኛን ሲገሉ፣ሲሰቅሉ የነበሩ፤
በእኛ ዘመን ደግሞ በካድሬ ቀየሩ።
ባንዳም ሆነ ፋሺሽት
መግደል ነው ግብራቸው፤
ሕዝብን ተመሳስለው
ሻጪም ገዢም ናቸው።
አርበኛን አጥምደው ሲሸጡ ለጠላት፤
እዩት ፍጻሜውን ዛሬም አለ ስቅላት።
ባንዳ ቅጥረኛ ነው የፋሺሽቶች ጀሌ፤
ጨካኝ ናቸው ሁለቱም፣ባንዳና ጉጅሌ።
በ«በቃ!» ተቋጭቷል መጨረሻው ቃሌ፤
በፍፁም አይኖሩም…ባንዳና ጉጅሌ።
አርበኞች ከታሪክ ሐቁን ስላወቁ፤
በባንዳዎች ተንኮል ያኔም ስለነቁ፤
መጀመሪ ባንዳን ገድለው እያነቁ፤
ፋሺሽቱን ሲደፉት ማታ እየጠበቁ፤
ይኸውና ዛሬ ትናንት ለድል በቅተው፤
እኛን አኑረዋል ብዙ ተሰውተው።
እናም…እያልን እኛ ኢትዮጵያን”አገሬ”፤
ለመኖር ሳናመር በባንዳ ላይ ዛሬ፤
ካጠገባችን ሆነው ሲያጋድሉን ሁሌ፤
አምርረን እንቁም ቆሜአለሁ በግሌ።
በ«በቃ!!»ተቋጭቷል መጨረሻው ቃሌ፤
በፍፁም አይኖሩም…
ባንዳና ጉጅሌ።
We don’t need a suport from an Aduwan woman. Uncalled for. Get lost.