የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር በኣውሮፓ ሕብረት በረሃቡ አና ድርቁ ዙሪያ ንግግር አንዲያደርጉ በኣና ጎሜዝ ተጋበዙ።
የፊታችን ማክሰኞ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በብራስልስ ቤልጄም በሚገኘው የኣውሮፓ ሕብረት ፓርላማ ላይ በረሃቡ አና ድርቁ ዙሪያ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፥ለትጥቅ ትግል ኣስመራ የገቡት ፕሮሬሰሩ በኣውሮፓ ፓርላማ አባል በሆኑት በወይዘሮ ኣና ጎሜዝ ጋባዥነት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በረሃቡ አና ድርቁ ዙሪያ እና ድርጅታቸው በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፕሮግራሙ ለሕዝብ ክፍትና ነፃ ነው።
