ሳውና ባዝ እና የጤና ጠቀሜታው

በ19ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ አካባቢ በፊንላንዶች እንደተጀመረ የሚነገርለትና መጠሪያ ቃሉንም ከዛው ያገኘው ሳውና ባዝ፤ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሠራሽ መንገድ በጋለ አለት ላይ ውሃ በማፍሰስና እንፋሎት እንዲፈጠር በማድረግ በእንፋሎቱ ገላን የማጽዳት ተግባር ነው፡፡ አምስት የሳውና ባዝ አይነቶች በስፋት ይታወቃሉ፡፡ እነዚህም ድራይ፣ ስቲም፣ ኢንፍራሬድ ዌት እና ስሞክ ይባላሉ፡፡ እነዚህ የሣውና ባዝ አይነቶች እንደስማቸው ሁሉ የተለያዩ አገልግሎቶች አሏቸው፡፡ በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትሉትም ለውጥና የሚሰጡትም ጠቀሜታ እንደዚሁ የተለያየ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል በስፋት የሚታወቀውና አገልግሎት ላይ የዋለው ኢንፍራሬድ ሳውና ባዝ የተባለው ዓይነት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ሳውና ባዝ ከሰውነታችን ውስጥ መርዛም ነገሮችን በማስወገድ ጤናማና ንፁህ ቆዳ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት እንደቅንጦት ይታይ የነበረውና ለሠርግና ለአንዳንድ ፕሮግራሞች ብቻ ጥቂት ሰዎች ይጠቀሙበት የነበረው ሳውና ባዝ፤ ዛሬ የበርካታ የከተማችን ሴቶችና ወንዶች ራሳቸውን ለማስዋብና ቆዳቸውን ለመንከባከብ እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡ በእርግጥ ሳውና ባዝ (በእንፋሎት ገላን ማጽዳት) በአንዳንድ የአገሪቱ ክልሎች ለሚኖሩ ህዝቦች የተለመደና ለዓመታት ሲገለገሉ የኖሩበት የተፈጥሮ የህክምና ዘዴ ነው፡፡ ሆኖም ግን በከተማ ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ ከውበት መጠበቂያነት የዘለለ አገልግሎት እንዳለው እምብዛም ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡

ሳውና ባዝ በቆዳችን ላይ ያሉትን ቀዳዳዎች ክፍተት ስለሚጨምር፣ ከሰውነታችን በሚወጣው ላብ አማካኝነት መርዛማ ንጥረ ነገሮችንና ሌሎች ቆሻሻዎች ከደማችን ውስጥ እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡

በዚህ መንገድ አላስፈላጊ ነገሮች የተወገዱለት የሰውነታችን ቆዳ፣ ንፁህና ጤናማ በመሆን ለተመልካችም የሚያስደስት ገጽታን እንድንጐናፀፍ ያደርገናል፡፡ የቆዳ መድረቅና ማሳከክ፣ የቆዳ ቁጣ (አለርጂ) ለመሳሰሉ ችግሮችም ሳውና ባዝ ፍቱን መፍትሔ ነው፡፡ የሳውና ባዝ ሌላው ጠቀሜታ ደግሞ ጡንቻዎችን ዘና በማድረግ በመገጣጠሚያ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ማስወገድ ነው፡፡ የጡንቻ መሸማቀቅ፣ የመገጣጠሚያ ህመም፣ ሪህና የመሳሰሉ በሽታዎች ከእንፋሎት ውሃው በሚገኘው ሙቀት የህመም ስሜታቸውን ማስታገስና ህመምተኛው እፎይታን ሊያገኝ ይችላል፡፡

ሳውና ባዝ አካልና አዕምሮንም ዘና በማድረግ ውጥረትን የማርገብ ተግባርም አለው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ ከእንቅልፍ ማጣት ጋር የተያያዙ ችግሮች ያሉበት ሰው ሳውና ቢጠቀም ችግሩ ሊቃለልለት ይችላል፡፡

ለመታፈን ችግር፣ ለጉሮሮ ህመም፣ ለጉንፋንና ለብሮንካይትስ ሳውና ባዝ (የእንፋሎት መታጠቢያ) ውስጥ የገባ ሰው፣ የሙቀት መጠኑ በመጨመር 39 ድግሪ ሴንቲግሬድ ድረስ ከፍ ሊል እንደሚችል የሚጠቁመው መረጃ፤ ይህ የሰውነት ሙቀት መጨመር በቆዳ አካባቢ ከፍተኛ የደም ዝውውር እንዲኖር ማድረጉንና የላብ መጠንን በመጨመር አላስፈላጊ ነገሮችን ከሰውነታችን ውስጥ የማስወገድ ሥራው እንዲጨምር እንደሚያደርግ ይገልፃል፡፡ እነዚህን አላስፈላጊ ነገሮች ለማስወገድም ሰውነታችን ኃይል መጠቀም ይኖርበታል፡፡ ይህንን ኃይል ለማግኘት ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ የተከማቸው ስብ ይቀጣጠላል፡፡ በዚህም ከባድ ሥራን ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከማድረግ ጋር ተመጣጣኝነት ያለው ስብ ከሰውነታችን ውስጥ እንዲወገድ ያደርጋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የሰውነታችን ክብደት እየቀነሰ ይሄዳል ማለት ነው፡፡ ከ15-20 ደቂቃ ሳውና ባዝ መውሰድ ከአንድ እስከ ሁለት ሰዓት ጠንካራ እርምጃ ወይም የአንድ ሰዓት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል፡፡

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የሚነገርለትን ሳውና ባዝ ከጤና አኳያ መውሰድ የማይገባቸው ሰዎች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

እርጉዞች፣ የልብ ህሙማኖችና ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ሳውና ባዝ ችግር ሊያስከትልባቸው ይችላል፡፡ አብዛኛዎቻችን ለውበታችን የምንጠቀምበት ሣውና ባዝ (የእንፋሎት መታጠቢያ) እነዚህ ሁሉ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡

በከተማችን በቁጥር በርከት ያሉ የሣውና ባዝና የእስቲም አገልገሎት የሚሰጡ ቤቶች ያሉ ሲሆን የአገልግሎት ዋጋቸውም እንደ ቤቶቹ ጥራትና እንደ አካባቢያቸው ይለያያል፡፡ አብዛኛዎቹ የሳውና ባዝ ቤቶች በቦሌ፣ በሃያ ሁለት አካባቢ፣ ቴሌ መድሃኒያለም፣ ሲኤምሲ፣ መገናኛና ሣር ቤት አካባቢ ይገኛሉ፡፡ የፍልውሃዎች ድርጅትም በአዲስ አበባ ከተማ ብቸኛው ተፈጥሮአዊ የሳውና ባዝ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለአንደኛ ማዕረግ  47 ብር፣ ለሁለተኛ ማዕረግ 41 ብር እያስከፈለ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ የተለያዩ የግል ሳውና ባዞች ደግሞ ደንበኞቻቸው ለሁለት ሰዓታት በ75 ብር ክፍያ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋሉ፡፡ ዳጊ፣ አለም ፊትነስ፣ ዴይስፓ፣ ሮዝ፣ ዮሊ ወዘተ… የሣውና ባዝ አገልግሎት ከሚሰጡ የከተማችን የውበት ሣሎኖችና ጂምናዚየሞች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

5 Comments on “ሳውና ባዝ እና የጤና ጠቀሜታው”

  1. Sehafiw betam tru mkr new neger gn lemehonu ethiopiya wst yezemenu habtamoch enji dehama enkan sawena liyasb bitu eyeferese siwerewer alayehm sport bit sawena kefach negadi balefok …..yemesaselutn yekefetutm yemigebutm yezemenu bale habtoch weyaniwoch nachew edmi le ethiopiya yemotelsh kerto yegedelesh bela yemibalew teret betegbar be agerachn eyetaye new

  2. ደሃውማ ላቡ ተንጠፍጥፎ ስለሚያልቅ ምን ሳውና ባዝ ያስፈልገዋል። ያም እኮ ዕረፍት ሲያገኝ መሰለኝ ወደቦታው የሚሄደው።
    ይህኛው ምክር ለወዛሞቹ መሰለኝ ካልተሳሳትኩ። ጸሃፊውን ግን ማመስገን እፈልጋለሁ።

  3. Ato chalachew yemetenagerew yemetawek alemeselegnem. kemesafeh befet tenesh kom belehe asebebet. lelawe letazabi etewewalehugn.

  4. Sehafiw lenegeru asabu tkkl new tmhr sech new yemiyawkewn makafelu tegebinew betam trunew negeru gn yeagerachn chgr slemitawek beweyanina belilaw mekakel yalew lyunet beglS meneger yelebetm ethiopiya le ethiopiyanoch mehona kerto leweyani hwehatna agonbach ashkerochm weyanin yetewesene bota endiyadersu ketederegu behala eskemiwereweru litekemu ychlalu beterefe deham emibelaw ato menoriyam bagerulay ato gmashu siseded gmashu bitu eyeferese siwerewer yale hzb yemiyasbew lkusus sayhon yesew lj meseretawi flagoton new slezih mastawekiyahn lezemenu ethiopiyan yale gedeb ygl habtachew argew eyeteznanubat lalu ager shachochna investeroch new yemihonew

  5. ሳውና ባዝ እና ኢትዮጵያ?
    ውድ የሳውና ባዝ የጤና ተቀሜታ አቅራቢ መልካም ሃሳብ ነው ነገር ግን ይህ የሳውና ባዝ አጀማመር በማን? በምን? መቼ? እንተጀመረ በጥናት የተደገፈ ሁኖ ቢቀርብ የታሻለ ይሆን ነበር ለማንኛው በሃሳብህ እስማማለሁ እና
    ስለሳውና ባዝ ጉዳይ በሰሜኑ ሃገራችን ክፍል በወሎ በትግራይ ክፍለ ሃገር በጥንት ጊዜ አሁንም አልፎ አልፎ የሚጠቀሙበት እንዳለ እኔ እራሴ የአይን ምስክር ነኝ
    ይህን የሳውና ባዝ የሚጠቀሙበት ሴቶች ሲወልዱ፣ሙሽሮች በሙሽራ ቤታቸው በጫጉላ ቤታቸው ጉድጎድ ተዎፍሮ፣የከብት ቆዳ በልብስ የተሸፈነ ወይም በቅርጫት በጥንቃቄ የተሰራ ጪስ አንዳያስወጣ ተደርጎ የሚዘጋጅ የወለደችው ሴት፣ሙሽራዋ ገላዋን ታጥባ፣በእንፋሎቱ ውስጥ በቂ እስኪሆን ድረስ ሳውና ባዙን ለጤንነታቸው ፈዋሽ መሆኑን ቅድመ አያቶቻችን አሁንም ያልጠፋ የሳይንስ የጥበብ ውጤት መሆኑን አይቻለሁን ወሎ ውስጥ ሚዜ በነበረኩበት ወቅት ሙሽራዋ/የእኔ እናት ስትወልድ ሳውና ባዝ ትጠቀም ነበር፡፡
    ይህ የሳው ባዝ በወሎ ክፍለ ሃገር ውስጥ ከወይባ፣ ከስራስር፣ከጭሳጭስ፣ በመቀጠም በጋቢ ተሸፍነው ለጤንታቸው መድሃኒት መሆኑን የተመሰከረለት የጥንት ኢትዮጵያዊያን ጥበብ መሆኑን ለመግለጽ እወዳሁ፡፡
    ስለዚህ ሳውና ባዝ እና ለጤና ጠቀሜታው ያለው ጉዳይ ላይ በጥልቅ ጥናት ቢደረግ መልካም ነው? ሁላችንም እንተባበር! የእኛ የሆነውን የባዕዳን ነው ማለት ተገቢ አይደለም የእኛ የእኛ ነው እና ምሁራን ሆይ አትሳሳቱ ብዙ የተደበቁ፣የተሰረቁ፣የተዘረፉ፣የተቀበሩ የኢትዮጵያ የሆኑ ሃገር በቀል እውቀቶች ብዙ ናቸው እኛው እንፈልጋቸው ለእኛው እናውላቸው!
    ጠባብነት ጎጠኝነት የሰው ልጅ አስተሳሰብ አይደለም የሰይጣኖች እንጁ!
    ሳተናው አሊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*