ህይወቷን በመኪና አደጋ ያጣችው የተዋናይት ሰብለ ተፈራ ባለቤት በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ክስ ተመሰረተበት

የፌደራል አቃቤ ህግ በ09/02/08 ፅፎ ያወጣበት የክስ ማመልከቻ እንደሚያሳየው አቶ ሞገስ ኮድ 2- አ.አ የሆነች መኪና ይዞ ከላንቻ ወደ ሳሪስ አቅጣጫ እያሽከረከረ ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ሲደርስ ፍጥነቱን ተቆጣጥሮ በሁለት እጁ መሪ ይዞ ፊትለፊቱን እያየ ማሽከርከር ሲገባው መሪውን በአንድ እጁ በመያዝ በአንድ እጁ ጎንበስ ብሎ ሬዲዮ እየጎረጎረ ከፊት ለፊቱ ከነበረው ኮድ 3- ኢት ታርጋ ያለው ተሳቢ ጋር በመጋጨቱ አብራው ተሳፍራ የነበረችውን ሰብለ ተፈራ ከፍተኛ የጭንቅላትና የአንጎል ጉዳት ደርሶባት ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ በፈፀመው በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ተከሷል፡፡


በተጨማሪም አቃቤ ህግ በተሳቢው ላይ የ100 ብር የንብረት ጉዳት በማድረሱም ሁለተኛ ክስ ፅፎበታል፡፡ አደጋው የደረሰው በሰብለ ስም በተመዘገበች ብርማ ቀለም ያላት የ2000 ቪትስ ሞዴል መኪና ሲሆን መኪናዋ 997 የሞተር ሲሲ/ችሎታ/ እና 45 የፈረስ ጉልበት አላት፡፡ አቶ ሞገስ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

5 Comments on “ህይወቷን በመኪና አደጋ ያጣችው የተዋናይት ሰብለ ተፈራ ባለቤት በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ክስ ተመሰረተበት”

  1. ይህ የሚያሣየው ፍርደ ገምድል የሆነ ህግ ይዘን የአንድ አርቲሥት ህልፈት ላይ ማብጠልጠል ያሥገምታል የዚህ አይነት የሞት ሠለባ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጎማ በልቷቸው ቀርተዋል ይህ ሠው እውነቱን በመናገሩና ማንኛውም ሠው የሚሠራውን ሥህተት ማጋነን ተገቢ አይደለም ወይሥ ቴፕ ሣሥተካክል ማለቱን ትቶ መሪው አሥቸገረኝ ማለት ነው ያለበት? ህሊና የለሌው የመንግሥት ፍትህ አካላት ሀይላችሁን ለማሣየት አትሞክሩ ብዙ አይተናል ቴዲ አፍሮ ውሻ ገጭቶ ሠው ነው አላችሁ የ9ኝ ጦማሪያንን…..አረሥንቱን የሀሠት ፍርድ የጦጣ ፍርድ አሣለፍን አሁንም ይህን ሠው እንደለመዳችሁት ምሥክር አቁሙና እንያችሁ።

    ከሌባ መንግሥት እንዴት ፍትህን እንጠብቃለን

  2. “ጥምብ በወደቀበት አሞራ ይዞራል”እርካሽ/ ቁስላም ወያኔ ገንዘብ አይትዋል ማለት ነው።የአርቲስትዋን account ለመዝገን ነው።ofcourse ታዲያ ወያኔ ለሰው ሕይወት።።።።

  3. Wind of change this is not about weyane.all weyane weyane woyane weyane woyane.from like you diaspora is nothing but wishet. Zeregnet .RIP artist tirfe

  4. ወያኔ የፍትህ መንግስት ባይሆንም ፍርዱ ትክክል ነዉ መጠየቅ አለበት!

  5. ህግ እኮ የለስሙላ እየሆነ ነዉ,ስንት ሌባ እያለ ,ምን በደለ ሰውየው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*