ኤርትራ የተጣለባት ፍትሐዊ ያልሆነ ማዕቀብ እንዲነሳላት ተማፀነች ::

የፀጥታው ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 2009 በኤርትራ መንግሥት ላይ ከጣለው የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ማለትም የፖለቲካ መሪዎችና ወታደራዊ አመራሮች ሀብት እንዳይንቀሳቀስ፣ እንዲሁም በእነዚህ አመራሮች ላይ ከጉዞ ማዕቀብ ውጪ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን በዲሴምበር 2011 ላይ ጥሏል፡፡ ይህ የኢኮኖሚ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ግፊት በኢጋድ በኩል የቀረበ ሲሆን፣ በተለይ አገሪቱ ከማዕድን ዘርፍ የምታገኘው ገቢ የምሥራቅ አፍሪካን ቀጣና ሰላም ለማወክ እየተጠቀመችበት በመሆኑ ማዕቀብ እንዲያርፍበት ተጠይቆ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በውጭ የሚኖሩ ኤርትራውያን ከሚያገኙት ገቢ ሁለት በመቶ በመቀነስ ወደ አገር ቤት የሚልኩት እንዳይተላለፍ የሚያደርግ ነው፡፡

ማዕቀቡ ከተጣለ ከአራት ዓመታት በኋላ ኤርትራ በኢኮኖሚ ማዕቀቡ የተዳከመች ትመስላለች፡፡ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት በጠራው መደበኛ ያልሆነ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት፣ በተመድ የኤርትራ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ግርማ አስመሮም ያረጋገጡትም ይህንኑ ነው፡፡ በውጭ ከሚኖሩ ኤርትራውያን ዓመታዊ ገቢ ሁለት በመቶ ተሰብስቦ የሚውለው በጦርነት ለተሰው ዜጎች ቤተሰቦችና የጦር ጉዳተኞችን ለመደገፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አምባሳደር ግርማ በውጭ የሚኖሩ ኤርትራውያን በዓመት የሚልኩት 11 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ አጠቃላይ የኤርትራ መንግሥት የሚያወጣው ግን ከ27 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተለይ የፀጥታው ምክር ቤት ሊገነዘበው የሚገባው ኤርትራ ከማዕድን የምታገኘውን ገቢ በፍፁም ከተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ውጪ (ማለትም ለእኩይ ዓላማ) አውላ እንደማታውቅ፣ አምባሳደር ግርማ ለምክር ቤቱ የማዕቀብ ኮሚቴ አሳውቀዋል፡፡ የኤርትራ መንግሥት ዓመታዊ በጀት ውስጥ 40 በመቶ የሚሆነውን የሚያገኘው ከማዕድን ዘርፍ መሆኑን በመጥቀስ፣ የማዕቀቡ መነሳት በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረውን አወንታዊ ተፅዕኖ ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ‹‹ማንኛውም የዓለማችን አገርና ሕዝብ ወደኋላ ሊተው አይገባም›› የሚለውን ተመድ በቅርቡ ያፀደቀውን ድኅረ 2015 የልማት ግቦች ያስታወሱት አምባሳደር ግርማ፣ በኤርትራ ላይ በተጣለው ፍትሐዊ ያልሆነ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ምክንያት የኤርትራ መንግሥትና ሕዝብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ በኤርትራ ላይ የተጣለው የኢኮኖሚ ማዕቀብ በተመድ ከተያዘው የድህነት ቅነሳ አጀንዳ ውጪ በመሆኑ፣ ይህንን ፍትሐዊ ያልሆነ ማዕቀብ የፀጥታው ምክር ቤት እንዲያነሳ ጠይቀዋል፡፡ አምባሳደር ግርማ በኤርትራ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ምክንያት የሆኑት ኤርትራ በሶማሊያ የሚገኘውን አልሸባብ የሽብር ቡድን ትረዳ ነበር መባሉ፣ እንደሁም በኤርትራና በጂቡቲ መካከል በተነሳው የድንበር ግጭት ሰበቦች መሆናቸውን ያስታውሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ ኤርትራ አልሸባብን እንደምትረዳ ቀደም ባለው የፀጥታው ምክር ቤት የሶማሊያና የኤርትራ አጣሪ ቡድን ሪፖርት ማረጋገጥ አለመቻሉን ቡድኑ ራሱ መጥቀሱን እንዲሁም በቅርቡ ባደረገው ምርመራም ምንም ዓይነት ማስረጃ አለማግኘቱን ራሱ መግለጹን ለፀጥታው ምክር ቤት የማዕቀብ ኮሚቴ አስረድተዋል፡፡ ሌላኛው የማዕቀቡ ምክንያት በኤርትራና በጂቡቲ መካከል የተነሳው የድንበር ውዝግብ በጭራሽ ከአካባቢውም ሆነ ከዓለም ፀጥታ መደፍረስ ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

ለዚህ የሰጡት ምክንያትም የግጭቱ መጠን ይህንን ያህል የሚያሳስብ ባለመሆኑ፣ ሁለተኛ ደግሞ ራሱ የፀጥታው ምክር ቤት ባፀደቀው መሠረት የኳታሩ ኤሚር የማግባባት ሥራውን እያከናወኑ መሆናቸውን፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የኳታር 200 ወታደሮች በአካባቢው መሰማራታቸውን በማውሳት፣ የማዕቀቡ ምክንያቶች በአሁኑ ወቅት ትርጉም የሌላቸው መሆናቸውን ተከራክረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፀጥታው ምክር ቤት ያቋቋመው የሶማሊያና የኤርትራ አጣሪ ቡድን ገለልተኝነትን ተችተዋል፡፡ የሶማሊያና የኤርትራ አጣሪ ቡድን ሐሰተኛ የፈጠራ መረጃዎችን በመጠቀም ሪፖርቱን እንደሚያጠናክር፣ ለዚህም እንደማሳያነት መረጃዎችን ከኢትዮጵያና ከጂቡቲ እንደሚቀበል አምባሳደር ግርማ ተናግረዋል፡፡ ‹‹አንድ ሰው ከእነዚህ ከኤርትራ ጋር ግጭት ካላቸው ኢትዮጵያና ጂቡቲ እንዴት እውነተኛ መረጃ ይጠብቃል?›› ሲሉ ተችተዋል፡፡

አጣሪ ቡድኑ ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስመልክቶ በተደጋጋሚ ለፀጥታው ምክር ቤት ኤርትራ ይግባኝ ብትልም፣ ችግሩ ሊቀረፍ አለመቻሉን አምባሳደሩ ለኮሚቴው አስረድተዋል፡፡ ለምሳሌ ኤርትራ በየመን ካለው የፀጥታ ሁኔታ ጋር ያላትን ግንኙነት መገምገም እንደሚፈልግ፣ ከዚህ በማለፍ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ስላልተፈታው የድንበር ውዝግብና በኤርትራ አጠቃላይ ውስጣዊ ፖለቲካ ውስጥ ያለ ሥልጣኑ እየገባ ነው ሲሉ አምባሳደሩ ይከሳሉ፡፡ የኤርትራና የኢትዮጵያ ጉዳይ የተወራሪና የወራሪ ጉዳይ ነው ያሉት አምባሳደሩ፣ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰንዘር እንደምትገደድ እየገለጸች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በማስረጃነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም እ.ኤ.አ. ጁላይ 7  ቀን 2015 ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹ኢትዮጵያ ወታደራዊ ዕርምጃ በኤርትራ ላይ ልትወስድ ትችላለች›› ማለታቸውን በማስታወስ፣ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ይህንን የኢትዮጵያን ዛቻ በቸልታ ማለፍ ሳይሆን ሊያወግዘው ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ የሰጡት ምክንያትም በአንድ አገር ላይ ወታደራዊ ኃይል የመጠቀም ወይም ለመጠቀም መዛት የተመድ ቻርተርን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጥስ እንደሆነ ነው፡፡

 

 

ኤርትራ የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት ተማፀነች

14 Comments on “ኤርትራ የተጣለባት ፍትሐዊ ያልሆነ ማዕቀብ እንዲነሳላት ተማፀነች ::”

  1. Assa Gorguwari Zendo Yawetal….Alarf Yalech Tat……Yekotun Awerd Bila Yebibituwan Talech……Yihe Hulu Le Ertra yemismama Teret neuw…. Aye Singapore….H ahahahaahhhhh

  2. Oh ! ! You wretched of the earth you deserve it.you installed woyane on Ethiopia.Now you sing a pooooor ! ! Not singapor or Taiwan.ስራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው።በ ኢትዮጵያ ላይ ወያኔን የመሰለ እሾህ ተከላችሁ! ! You bit the hand that fed you generiously.

  3. Gud fela! Wey Eritrea! ye 100 amet yebet sera yesetut astemari melsun rasachew sayawukut teshewedu neber leka! Enedegena memar alebachew lezih degmo alawakinetahewun bezuriya temtem sayehon beketeta amenew mekreb alebachew.Yane afeteto lemetabachwu yehezb besot meftehe yaggnalu.

  4. ምንም ቢባል ምንም ሃቅና ጭስ መውጫ ኣያጣም እነዚህ ሰዎች የውሸት ነገሮችን እየደረደሩ ሃቅን በውሸት ለመቀየር እየሞከሩ ነው በኢትዮጵያና በኣከባቢው የድሃውን ረሃብና እሮሮ ወደኋላ ትተው የራሳቸውን ጥቅም ለመጠበቅ የኤርትራ መንግስትና ህዝብን ቢከሱም ሃቅ ሃቅ ነው ኤርትራ የራሷን ፖለቲካዊ ይሁን ኤኮኖሚካዊ ጥቅም ኣክብራ የማንም ሃገር ጥገኛና ሳትሆን እንደምትቀጥል የሚጠራጠር ኤርትራዊ የለም ምክንያቱም በልመና ከመኖር ራስን መርተህ ወደፊት እየሰራህ መኖርን ይመረጣል

  5. Sing a pooooooooooor ! ! Not singapore or taiwan.I remember when i transited in london hitrow airport, i saw a shavia taxi drive and on his t-shirt was a pictur of a coffee tree የተንዠረገገ ይቡና ዛፍ ነው።እስሩ ልይ” የኤርትራ ቡና” ይላል! ! I said what ! ! ! Coffee is from southern Ethiopia.Well that was when woyane and shavia were in their honey moon and shavia had unlimited access to Ethiopia’s resource left and right.Now የተከበረው አምባሳደር is telling us he has no access to his petsonal account ? Wel እስቲ እንቆይ የቆየ ሰው ብዙ ሊያይ ይችላል! ! ! ላሁኑ ጉድ ብለን እንዝጋ።ያማርኛውን ጉድ ማለቴ ነው።በእንግሊዘኛው ጉድ እንዳታስተውሉት

  6. እኛ ስለ ኤርትራ ምን አገባን?ከኢትዮጵያ አስገንጣዩና ተገንጣዊ ስለ ኤርትራ ይጨነቁበት:ኢትዮጵያዊያን ኤርትራ ብታድግ ብትፈርስ አ አይመለከተንም:ብቻ ለእግዜሩ ሰላም ይሁኑ ከዚህ ውጭ አያገባንም

  7. ጥያቄው ተገቢ ነዉ።በአኑ ጊዜ ለራሱ ህዝብ እና ለአካባቢው ከኤርትራ ይልቅ በአደገኛ ሁኔታ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን ማን ለተመድ አጣሪ ቡድን በነገረው።መቸም አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይነቃም እንደሚባለው ።

  8. ኤርትራ ያሉ የግንቦት ሰባት አመራሮች የመከፋፈል እድላቸው የሰፋ ነው:አመራሮቹ ኤርትራን ሊያጠፉ ነውና,ኤርትራውያን ግንቦት ሰባትን ከመሬታችሁ አስወጡ:መቼም ብርሀኑ ነጋ ሊዋጋ ድፍረት አይኖረውም ስለዚህ ኤርትራ ያለህ ጥቂት የግንቦት ሰባት አባል አንተን ሊማግዱህ ነውና ጥለሀቸው ወደ ሀገርህ ግባ:የግንባሩ መሪወች እንካን ጥይት,የውሻ ጩሀት የሚፈሩ ናቸው::

  9. አንተ ወዲ ተረዋኢ ቁስላም ወያኔ አገር በሻቪያ ፊታውራሪነት በወያኔ የሻቪያ condomነት ጠፋች። which country you talking about.ኢትዮጵያንማ የሚዜ ቂጣ አደረጋት እኮ ወያኔ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*