“በምን ነፃ ልውጣ” አዲስ አልበም ነገ ማክሰኞ ይለቀቃል::

የድምፃዊት ቤሪ “በምን ነፃ ልውጣ” የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም፣የፊታችን ማክሰኞለገበያ እንደሚቀርብ ተገለጸ፡፡ 12ዘፈኖችን ያካተተው አ ል በ ሙ ፤ ሙ ሉበሙሉ በሙዚቃ ባለሙያው ኤልያስ መልካየተቀናበረ ሲሆን ፕላቲኒየም ሪከርድስእንደሚያከፋፍለው ለማወቅ ተችሏል፡፡

“በምን ነፃ ልውጣ” አዲስ አልበም ማክሰኞ ይለቀቃል

“መልኩስ ልቡ ነው”፣ “የፍቅር ዋጋ”፣ “ማዝመርእንዲህ፣ መዝፈን እንዲያ”፣ “ምህረት እና እውነት”እና ሌሎችም ዘፈኖች በተካተቱበት በዚህ የሙዚቃ አልበም፣ አብዛኞቹን ግጥሞችና ዜማዎች የደረሰውአቀናባሪው ኤልያስ መልካ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ድምፃዊቷ ቤሪም ጥቂት የዘፈን ግጥሞችንየደረሰች ሲሆን ዘፈኖቹ በፍቅር፣ በታማኝነት፣በይቅርታና ሌሎች ቁምነገር አዘል ጭብጦች የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡