ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ የፈረሰበት ወጣት ራሱን አጠፋ
ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ፣ ታምራት ታንቱ ባጫ የተባለ ወጣት፣ ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ በመንግስት አፍራሽ ግብረሃይሎች መፍረሱን ተከትሎ፣ ራሱን ያጠፋ ሲሆን፣ ባለቤቱም ራሱዋን ስታ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ውስጥ ጸሎት እየተደረገላት ነው። ወጣት ታምራት ትናንት ነሃሴ 26 የቀብሩ ስነስርአት ተፈጽሟል። ሚሚ ባቴ የተባለች የአንድ ሳምንት መጫትም በላዩዋ ላይ ቤቷ በመፍረሱ፣ ጎዳና ላይ ወድቃለች። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ወጣቶችም አሉ።
እስካሁን ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች መፍረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዚሁ ከተማ ትናንት ምሽት በንግድ ቤቶች ላይ በተነሳ ቃጠሎ ከ100 በላይ የንግድ ድርጅቶች ወድመዋል።
Let Christians, Muslims, Qallu believers, and others who share the same rivers: Abbay, Genalie, Wabi Shibelie, Awash, Gojeb, Baro, Omo, Jamma, Takezie, Gibie, etc. pray together; GOD will definitely hear and give us remedy. Because, GOD has provided us the same destiny whether we like it or not.