ጥቂት ትዝታ ዶ/ር ነጋሶ ቤት ከነበረኝ ቆይታ (ዳንኤል ተፈራ)
ጥቂት ትዝታ ዶ/ር ነጋሶ ቤት ከነበረኝ ቆይታ
………………….. ዳንኤል ተፈራ
ትናንት አንድ ቀጠሮ ይዘን ነበር….. አዎ!… ይሄው በቀጠሯችን መሰረት ከች፤ የመብራቱ መኖርና ‹‹የኢንተርኔት ኮኔክሽን›› መከሰት ታክሎበት በትናንትናው ዕለት ከዶ/ር ነጋሶ ጋር ስለነበረኝ ቆይታና ትዝታ ጥቂት ለማለት በቃሁ፡፡

ዶ/ር ነጋሶ የሚኖሩት ብስራተ ገብርኤል አካባቢ በመንግስት ቤት ነው፡፡ ያውም ፖለቲካው ላይ ሲያከሩ ቂመኛው ህወሃት/ኢህአዴግ ‹‹ልቀቁ!›› እያለ እያንገራገራቸው ነዋ! ለአዛውንቱ ፕሬዘዳንት ግርማ በየወሩ 400 ሺ ብር ሆጭ እያደረገ የሚያቀማጥለው ገዥ ፓርቲ ለዶ/ር ነጋሶ ዞሮ መግቢያ ጎጆ ሊከለክላቸው ይፈልጋል፡፡ የመለስ/ኃይለማሪያም አገዛዝ በስልጣን ዘመናቸው የነበራቸውን መኪና ነጥቆ በእግራቸው ከህዝብ ጋር እየተጋፉ ሲሄዱ እየተመለከተ መሳቅ ያምረዋል – ጥርስ የለውም እንጅ፡፡ ነገርግን ዶ/ር ነጋሶ ከህዝብ ጋር በመሆናቸው ከበሩ እንጅ እንደጠበቁት አልተዋረዱም፡፡
ቁሳዊውን ዓለም ያሸነፉት ዶ/ር ነጋሶ አሁን ብዙ ግዜያቸውን የሚያሳልፉት ከግርጌ ካለው ፎቶ በስተጀርባ በምትመለከቷት ቢሮ ውስጥ ነው፡፡ እንደነገሩኝ ከሆነ እዚችው ቢሮ ሲያነቡና ሲፅፉ ይውላሉ፡፡ እዚች ቢሮ ገብቼ አውቃለሁ፡፡ ፓ! መረጃ አያያዝ፤ ኢህአፓ የበተነቻት የመጀመሪያዋ ወረቀት ሳትቀር አለች፡፡ ያ እሳት የላሰ ትውልድ ከመሳሪያ በተጨማሪ ሲራኮትባቸው የነበሩት ታገል፣ ታጠቅና ሌሎች መፅሔቶችም በክብር ተቀምጠዋል፡፡ በአጠቃላይ ቤታቸው የተደራጀ የታሪክ ላይበራሪ በሉት፡፡
የነጋሶ መንገድ የተቀዳው እዚህ ፀጥታ በረበበት ቤት ነው፡፡ ለቃለ መጠይቅ ብቻ ለሦስት ወር ከትሜ ነበር፡፡ የማስታወስ ችሎታቸው ድንቅ ነው፤ በልጅነታቸው ደምቢዶሎ ከቤታቸው ፊት ለፊት የነበረችውን ዛፍ ቁመትና ስፋት ሳይቀር ያስታውሳሉ፡፡ ከኦህዴድ/ኢህአዴግ ጋር ከተፋቱ በኋላ ቂም ተይዞባቸው ለረጅም ዓመት ጣሪያው በሚያፈስ ቤት ኖረዋል፡፡
በ2003 ዓ.ም በልግ ወቅት አንድ ቀን የቤታቸው ሳሎን ቁጭ ብለን ለማነሳላቸው ጥያቄ መልስ እየሰጡኝ እያለ ሰማዩ አጉረምርሞ እንባውን አረገፈው፡፡ ተንደርድረው በስተግራ በኩል ወዳለው ሰፊ ክፍል ሮጡ፤ አብሬያቸው ተንደረደርኩ፤ እንደወንፊት የተቦዳደሰው ጣሪያ ዝናቡን መመከት አቅቶት ያንዠቀዥቀው ይዟል፡፡ የሚበላሹ ዕቃዎችን ለማሸሽ ሞከርን፤ ወዲያው ፊታቸው ላይ አንጀት የሚያኮማትር ሀዘን ረበበ፤ ዓይኖቻቸው እንባ አቀረሩ፤ ፕሬዘዳንቱ ሲያለቅሱ ላለማየት ሰበብ ፈልጌ ወደ ውጭ ወጣሁ፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ መሃረባቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ዓይኖቻቸውን እያበሱ ወደ ሌላ በስተቀኝ በኩል ወደሚገኝ ክፍል ይዘውኝ ገቡ፡፡ ትላልቅ የብረት ቁምሳጥኖች ተገጥግጠዋል፡፡ ‹‹አየህ!…›› አሉ ሀዘን እንደ ሜትሪዮሎጅ አውሮፕላን በዙሪያቸው እየተሸከረከረ ‹‹አየህ…. እነዚህ ሁሉ የብረት ሳንዱቆች ታሪካዊ ሰነዶችንና ዶክመንቶችን የያዙ ናቸው፡፡ ዝናብ እንዳያበላሽብኝ ቆልፌባቸው ነው – ያሳዝኙኛል ግን ምንም ማድረግ አልችልም…..›› ያሉኝ ትዝ ይለኛል፡፡
ትናንት ስሄድ ግን ለቤቱ መጠነኛ እድሳት ስለተደረገለት ቢያንስ አያፈስም፡፡ ዶክተሩ ከማንኛውም የፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸውን ስላገለሉ መረጋጋት ይታይባቸዋል፡፡ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ሲሰሩ እንደሚውሉ ቢሯዋቸው ጠረፔዛ ላይ የተዝረከረኩ ሰነድና መፅሐፍቶች ያሳብቃሉ፡፡ ነብይ በሀገሩ ባይከበርም ምናልባት እንድ ቀን እንጠቀምበት ይሆናል፡፡
ከዶ/ር ነጋሶ ጋር በደንብ የተግባባነው አንድነት ፓርቲን ከተቀላቀሉ በኋላ ነው፡፡ በ2002 ምርጫ ወቅት ወደ አርባ ምንጭና ደቡብ ኦሞ ለቅስቀሳ ሲሄዱ አብሬያቸው ሄጄ ነበር፡፡ መንገዱ ረጅምና አሰልቺ ቢሆንም ዶ/ር ነጋሶ የሚነግሩን የህወሃትና ኦነግ ታሪክ ድካማችንን አሽቀንጥሮት ነበር፡፡ አስታውሳለሁ የዶ/ር ነጋሶን ታሪክ የመፃፍ ውጥን ያሳደርኩት በዚህች ቀን ነበር፡፡ ከኃይለማሪያም ሀገር ወላይታ ሶዶ እስከ አርባ ምንጭ ባለው የምሽት ጉዟችን ሁለት ጥያቄ አነሳሁላቸው፡፡
አንደኛው ስለ አወዛጋቢው ጋዜጠኛ ወ ፖለቲከኛ ተስፋየ ገብረአብ ነበር፡፡ ‹‹ተስፋየ ገብረአብ በኦሮሞ ጉዳይ ላይ የሚያነሳቸውን ሀሳቦች እንዴት ይመለከቷቸዋል…..›› የሚል ያልተደራጀ ጥያቄ ሰነዘርኩላቸው፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሶለን እንደዚህ ብለው ጀመሩ፡- ‹‹ተስፋየ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ልሁን ይላል፡፡ ተስፋየ ብቻ ሳይሆን አንድ ጀርመናዊም ነበረ (እኔ ነኝ ስሙን የረሳሁት እንጅ ነግረውን ነበር) ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ልሁን የሚል፡፡ የእኔ አውቅልሃለሁ ስሜት የተጠናወታቸው……..፤ አየህ ተስፋየ ገብረአብ……›› እያሉ ቀጠሉ፡፡ በጥቅሉ አሁን ተስፋየ ገብረአብ ያለበትን አቋም ያኔ ተረኩልን፡፡ ባለ ውብ ብዕሩና ‹ተንኮለኛው ደራሲ› ተስፋየ ገብረአብም የነጋሶን ‹‹በማይመለከትህ ጥልቅ አትበል!›› አስተያየት ሰምቶ በስደተኛው ማስታወሻው ይመስለኛል መልስ ለመስጠት ሞክሯል፡፡
ሁለተኛው ጥያቄየ፡- ‹‹መለስ ዜናዊን ሲያውቁት ምን አይነት ሰው ነው…›› የሚል ነበር፡፡ ‹‹መለስ ጎበዝም ሴረኛም ነው፡፡ ጠላት ብሎ ያሰበውን ሳያስወግድ እንቅልፍ የማይተኛ፡፡…… በስብሰባ እረፍት ጊዜ በተከታታይ እያጨሰ ስብሰባው ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለበት አሰላስሎ የሚገባ፤ ግን ደግሞ ጎበዝ አንባቢ…….›› እያሉ ቀጠሉ፡፡ በአጠቃላይ ሁለቱን ጥያቄዎች እያብራሩ አርባ ምንጭ ገባን፡፡ በዚህ ሁናቴም ዳንዲ- የነጋሶ መንገድ ተጸንሶ ተወለደ፡፡
ዶ/ር ነጋሶ አንድነት በጋሜ በመቅረቱ አዝነዋል፡፡ ብዙ የደከሙበት ድርጅት ነበር፡፡ በተለይ በወጣቶች የተቀነቀነው የለውጥ ፈላጊነት እንቅስቃሴ ጥርስ ውስጥ እንደከተተው ነግረውኛል፡፡ በሳምንት ሁለት ቀን ጋዜጣ ማተም፤ የማተሚያ ማሽን መግዛት፤ ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ ማድረግ…. ለኢህአዴግ ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ቢሆንም አንድ ድርጅት የታለመለትን ዓላማ የማያሳካ ከሆነ መኖሩ ካለመኖር እኩል ነው፡፡ የነጋሶ ስንብት የአንድነት የመውደቂያው መጀመሪያ ይላል ሀገር የተቀማው ትውልድ…….. ‹‹እንግዲህ ወገኖቼ›› የምትለውን ቃል ልዋስና ልሰናበት፡፡ ቀጣዩን ቴሌና መብራት ሃይል ፈቅደው ለፌስቡክ አይነስጋ ከበቃን እንቀጥለዋለን፡፡
ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ለተከበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሶለን በመመኘት
ትውልዱ ታሪክን ያሥታውሣል ከአባቶቹም ልምድ ይማራል የተቀማውንም ሀገር ያሥመልሣል ይለወጣል።
Je suis ኢትዬጵያዊ!!!
” ያ እሳት የላሰ ትውልድ “,
well, that tiwlid was fooled by Eritreans who were possessed by Italian demons and used as a tool to advance ferenji, arab and shabia agendas. That tiwlid should now admit to have been fooled and instrumentalized. Even Derg could have been instrumentalized by France, USA and the West for agendas like keeping Djibouti, taking revenge on Haile Selassie etc.
” ‹‹ተስፋየ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ልሁን ይላል፡፡ ተስፋየ ብቻ ሳይሆን አንድ ጀርመናዊም ነበረ (እኔ ነኝ ስሙን የረሳሁት እንጅ ነግረውን ነበር) ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ልሁን የሚል፡፡ የእኔ አውቅልሃለሁ ስሜት የተጠናወታቸው……..፤ ”
That behaviour is easily explained, those people wanted to instrumentalize Oromos to advance Eritrean and ferenji agendas.
” The Nazis of Austro Hungary had already in the 1930s targeted Ethiopia as a threat against white supremacy, and white colonialism in Africa. The book by the Austrian Nazi, Baron Roman Prochazka, “Abyssinia the Powder Barrel” (Vienna 1935), translated in all the major Western languages before the Italian invasion in 1936. Baron Roman Prochazka was posted for two years as Austrian Consul in Addis Ababa until his expulsion in February 1934, for activities not compatible with his job of a diplomat.The Italian translation of Prochazka’s book entitled ABISSINIA PERICOLO NERO meaning “Abyssinia the Black Threat or Danger” was published in 1935, which is a year before the Fascist invasion.
Starting from the first page, Prochazka alerts his white public by stating that since four years that Emperor Haile Selassie’s Ethiopia, in “close co-operation with Japan,” was engaged “on a life and death struggle with the white race, the consequences of which are incalculable. The targets are the colonial powers in Africa without exception. It is hardly possible to imagine a more unhappy situation of a white man than to have to live under the oppression of an Abyssinian grandee. The prevalence of this contemptuous invective is characteristic of the mentality and attitude of the natives who imagine themselves to be infinitely superior to the white race.”
The solution proposed by Prochazka is the tribalisation of Ethiopian politics for the purpose of divide and destroy. Prochazka was the first ever to have spoken of “self determination” as the most handy instrument for the dismantlement of the Ethiopian State. Here in brief are the highlights of Prochazka’s strategy:
“The numerous peoples and tribes who inhabit the territory of the Ethiopian state, and which differ in race, language, culture and religion from the ruling minority of the Abyssinians proper, would long ago have thrown off the Abyssinian yoke if they had been given the right of self-determination. Instead, they are being forcibly kept cut off from European influences and from the advantages that progressive colonization could confer upon the country.
The final aim of (Abyssinian) policy of antagonism to the white race, in co-operation with Japan, is nothing less than to act as the champions of all
the colored peoples of Africa… It is incumbent on the legations of the civilized nations in Abyssinia to warn their governments to take a definite stand before the Abyssinians attack and destroy western culture and civilization in its entirety. There is no such thing as a united Abyssinian people. The greater part of the non-Christian tribes in Abyssinia has no more burning desire than to be freed from the tyranny of the Amharas.
If they would vote freely they would certainly prefer a European protectorate to universally hated extortionists and slave drivers. This country is cracking at all its joints and has only been kept together up to the present by methods of ruthless coercion.”
With all the talk of the “right of self determination” in the 1930’s the CIA’s Ethiopia policy of the right of self-determination and nations and nationalities could has been copied word for word from the Nazi Baron Roman Prochazka,for the tribal dismemberment of Ethiopia. ”