የአዲስአበባ ከንቲባ የስር አመራሮቻቸውን ወቀሱ
ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባል አቶ ድሪባ ኩማ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር በከተማዋ መቀነስ ያልቻለው መመሪያዎችን በቁርጠኝነት መፈጸም የማይችል አመራር በመኖሩ ነው ሲሉ በስራቸው የሚገኙ አመራሮችን ወቅሰዋል፡፡
ከንቲባው ይህን የተናገሩት በሰኔ ወር 2007 የተጠናቀቀውን የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸምና በቀጣይ ዓመት የሚጀምረው ሁለተኛውን ዕቅድ አስመልክቶ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ሰሞኑን በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ በከተማ አስተዳደሩ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመው «አዲስ ልሳን» ጋዜጣ በትላንት ዕትሙ እንደዘገበው ከንቲባው ባለፉት አምስት ዓመታት በአስተዳደሩ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር በታሰበው መልኩ አለመቀነሱን አረጋግጠዋል፡፡ ለዚህ ምክንያት ነው ያሉት ደግሞ በየደረጃው ያሉ አንዳንድ አመራሮች የሚወጡ መመሪያዎችን ማስፈጸም ባለመቻላቸው ነው፡፡
ከንቲባው በቁጥር ቀላል የማይባሉ አመራሮች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ፈጻሚዎች ከመመሪያ ውጪ ሲሰሩ በዝምታ በማለፍ፣ ራሳቸውም አልፎ አልፎ ተሳታፊ በመሆን ኪራይ ሰብሳቢነት በከተማዋ እንዲስፋፋ በር ከፍተዋል ከማለታቸውም በተጨማሪ፣ አንዳንድ የአስተዳደሩ መ/ቤቶችም የሚመሩት በአመራሮቹ ሳይሆን በደላሎች ፍላጎት ነው ብለዋል፡፡
ከንቲባው አንዳንድ ፈጻሚና አመራር ባልተገባ ጥቅም የተሳሰሩ በመሆናቸው አንዱ የህዝብ ንብረት ሲዘርፍ ሌላው በዝምታ የሚመለከትበት ሁኔታ መኖሩን ጠቁመውዋል፡፡
የተቋማት ውጤትም ሆነ ውድቀት በዋናነት የሚወሰነው በአመራሩ ጥንካሬና ድክመት ነው ያሉት ከንቲባው፣ አመራሩ ፈጻሚዎች የሚያከናውኑዋቸውን ተግባራት በትክክለኛው መንገድ መስራታቸውን መከታተል አለባቸው ብለዋል፡፡
24 አመት የከተማው ከንቲባዎች ምንም የሚሥብ ሥራዎችን ለሀገሪቱ አላበረከቱም እንዲያውሥ የክልል ከንቲባዎች ጥሩ ለውጦችን ሢያመጡ እያየን ነው የእውቀት ውሥን ሥህተቶች ቢኖሩባቸውም የኛዎቹ ግን መሬት ሊዝ ኪራይ ሠብሣቢነትን ብቻ ነው የሚያሣድዱት የህዝብ መፀዳጃ ፅዳት ፍሣሽ መንገድ ጉድጎድ መልካም አሥተዳደር ሙሥናን ሣይለወጡ ከነቁሻሻው ይዘውት 2ኛውን የልማት ወንዝ ተሻገሩ።
ለውጥን የሚያመጣ አቅም ያላቸው በቦታው ሢቀጥሉ አይታዩም በበጎ ፈቃድ ለውጥ ያሣዩ ለምሣሌ ጋሽ አበራ ሞላን የመሠለ በተለያዩ ማደናገሪያዎች ሥራውን አሥጣሏቸው ለምን? በጣም በርካታ ዜጎች እውቀቱ ያላቸውን ለምን እንዲሣተፉ አይደረግም? የወያኔ ችግር ለውጥን የሚያመጣ ባለሥልጣን ሣይሆን ፖለቲካውን እንደ አብዬት ጠባቂ የሚጠብቅ እንጂ ይህ ነው የሚባል ለውጦችን አላመጡም።
ባንድ እጅ መዶሻ በሌላኛው ኪሥ ፈሊጥ ሀገሪቷን የአደሀሪያን መፈልፈያ አድርጎታል!!!
ብዙ አይተናል የአዲስን ከንቲባ-ማን ይሻላል እንደድሪባ ኩማ-ባቡሩን ሲያሰራ መንገድ ሲያሰገነባ-ሙሰኛን ሲቃወም ውህኒ እያስገባ-ከቶ ማን ይሻላል ከድሪባ ኩማ