ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የ14 አመት ልጁን አስገድዶ የደፈረው አባት በእስር ተቀጣ ::
የ14 አመቷን ታዳጊ ለተከታታይ ሶስት ዓመታት /2003- 2007/ ዓም ድረስ እግርሽ ላይ ለወጣው ጭርት መድሀኒት ነው በማለት ወሲባዊ ግንኙነት በማድረግ 2 ግዜ ስታረግዝ እንድታስወርድ ያደረገ እና ከዛ በሁዋላ እንዳታረግዝ የረዥም ጊዜ የወሊድ መከላከያ (ሉፕ ) በክንዷ ያስቀበረ ሰው በፍትህ አደባባይ ቆሟል ። ሌላ ሰው እንዳይመስላችሁ የገዛ ወላጅ አባቷ።ተሳስቼ አይደለም የፃፍኩት!! አሳዳጊዋ፣ የእንጀራ አባቷ ወይም አጎቷ ሳይሆን የገዛ አባቷ!!!!!!

ማን ይሄን ሊያምን ይችላል? ከአባት በላይ ማንን እንመን? አቅፎ ፀጉር እየደባበሰ ና እያሻሸ ፍቅር የሚሰጥ አባት ይህን ፈፀመ ሲባል እንዴት አይሰቀጥጥ!…እንዴትስ ለጆሮ አይከብድ? ለጥቃት ደራሽነቱ ለደቂቃ የማያጠራጥረን ፣ በኩራት በስሙ የምንጠራበት ወላጅ አባት በገዛ ልጁ ላይ ይህን እኩይ ተግባር አደረገ ሲባል ” እውነት ወላጅ አባቷ ነው?” ብለንስ እንዴትስ አንጠይቅ?
እንግዲህ የሆነው ይሄ ነው። ሌላ አገር፣ በሌላ ባእድ ምድር ላይ ሳይሆን እዚሁ … እዚሁ!!! በቅኔ በሚነገርባት ፣በመላእክት ቋንቋ በሚዘመርባት ፣መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ከምናምን ጊዜ በላይ እንደ ተጠቀሰች በሚነገርላት ኢትዮጲያ !!!!! አዲስ አበባ ላይ ነው።
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው ፍርድ ቤት በተከሳሹ ላይ የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል። ውሳኔው ‘አግባብ ነው! አይደለም !’ የሚለውን የምንነጋገርበት ይሆናል።
ሙሉ የወንጀሉን ዝርዝር ለጋዜጣው(ኢትዮ ቻናል )ስዘግብ ከህሊናዬ ጋር አየተጣላሁ እና የሚያስተምረውስ ምንድነው? ከሚል የህሊና ጥያቄ ጋር በመፋጠጥ ነበር።
ያመንኩት ግን መሸፋፈኑ እና መደባበቁ ከማስተማር ይልቅ ጥፋቱ ቢገንብኝ እያመመኝ ሰርቼዋለሁ።
ዝርዝር የወንጀሉን ድርጊት፣ የተከሳሽን ቃል እና የፍርዱን ውሳኔ በነገው እለት ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ይዛው ትቀርባለች።
በግሌ ምን እንደምል አላውቅም… ብቻ ግን የምንሰማው የምናየው ሁሉ ያማል!!!! በጣም ያማል!!! ኧረ ጎበዝ ፈጣሪንም አስቀይመን ከሆነ ሁላችንም እንደየእምነታችን ወደፈጠረን እንፀልይ?
አባት የገዛ ልጁን … !! (ሰለሞን ታደሰ /Solomon Tadesse/)