(ሰማያዊ ፓርቲ ) … ፍርሀት እና ስጋት! (አርአያ ጌታቸው)

በሙሉ ልቤ የፈለኩትን እንዳልናገር እኔ ማን ሆኜ ነው? ትቼ የሄድኩትን ድርጅት የምተቸው፡፡ ዝም እንዳልል ጓዳዊ ስሜቴ ያዘኝና ነገሮች ከተበላሹ በኋላ ከማውራት ካሁኑ (ምንም እንካ አሁንም ቢረፍድም) ማለት ያለብኝን ብዬ የተቀረውን እንዳመጣጡ መቀበል ነው በሚል አጠር እድርጌ ልጀምር፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናቶች ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ ሊያደርግ እንደሆነ ሰምቻለሁ ስለዚህ ጉባኤ ዛሬ በነገረ ኢትዮጵያ ከወጣችው አጭር ወሬ በስተቀር በፓርቲው ገጾች ላይ አንዲትም ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልቻልንም፡፡ ሰማያዊን የሚክል ፓርቲ ለዛውም ከመስራች ጉባኤው ቀጥሎ የሚያደርገውን ትልቁን ጠቅላላ ጉባኤ የሚያደርግ ድርጅት እንዲህ ቀናት እስኪቀሩት ጉዳዩን ለምን በሚስጥር እንደያዘው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ፖለቲካ የህዝብ ነው ሆኖም አይደለም ህዝቡ ደጋፊዎች እና ለፓርቲው የቅርብ ሰዎች ነን የምንል ሰዎች እንኳ ምንም የምናውቀው ነገር የለም፡፡ ለምን? ከወያኔ ልምድ እየቀሰምን ይሆን?


ሌላው ጉባኤው ሊካሄድ 3 እና 4 ቀናት እየቀሩት ብቸኛው እጩ ይልቃል እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡ በእውነት ሰማያዊ ፓርቲ እንዲህ አይነት ድርጅት ነው? ዛሬም ከሀገራችን ባህላዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ አልተላቀቅንም? ይልቃል በጣም ጠንካራ ፖለቲከኛ እንደሆነ አውቃለሁ ድርጅቱንም ከነችግሮቹ መርቶ ዛሬ ድርጅቱ የደረሰበት ደረጃ ላይ አድርሶታል፡፡ ነገር ግን በውስጥ የፓርቲው ፖለቲካ እና በአለምአቀፍ ዲፕሎማሲ ግንኙነት በጣም ደካማ ሰው እንደሆነ በተደጋጋሚ ታዝበናል፡፡ በውስጥ ፖለቲካው ዙርያ ብዙም ዝርዝር ውስጥ ባልገባም በራሱ ፓርቲ ምክር ቤት እና ኦዲት እና ኢንስፔክሽን በተደጋጋሚ ክሶች ቀርበውበት እንደተቀጣም አደባባይ ወጥቶ አንብበናል፡፡ በዲፕሎማሲውም ረገድ ከመጋረጃ ጀርባ ከዲፕሎማቶች ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን በየጋዜጣው እና ሚዲያዎች ላይ እያወራ ብዙ ነገሮችን አበላሽቷል፡፡ ይሄ ማለት ይልቃልን ለመወንጀል ሳይሆን ይሄ እና መሰል ብዙ ድክመቶች ያሉበት መሪ እንዴት አንድ እንኳ እሚወዳደረው ሰው ይጠፋል? ነው ወይስ አሁንም የሀገራችና ባህል እየሆነ የመጣው የአንድ ሰው ፓርቲ እየሆነ ነው? ቢያጠፋም ቢያለማም እንዴ ከወጡ የማይወርዱበት ብቻ ሳይሆን የማይወዳደሩበት፡፡
እንደ እኔ ግምት የሰማያዊን ፓርቲ እንቅስቃሴ በቅርበት ለሚከታተል ሰው ይልቃል በድጋሚ ይመረጣል የሚል ፈጽሞ ግምት አልነበረኝም ጭራሽ ብቸኛ እጩ ሆነ (smile emoticon) የእኛም ትውልድ ባለበት እየረገጠ መሰለኝ፡፡


ወያኔ ከሚታወቅበት እንዱ ሚስጥራዊ መሆኑ እና ፖለቲካው ምንም ህዝብን የማያሳትፍ መሆኑ ነው፤ እናም የእነሱን አርዓያ እየተከትልንስ ይሆን እንዴ? ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ያሉት አመራሮች በተለይ ሲኒየሮቹ በ “ዝም አንልም” ውስጥ ይነሱ የነበሩ መርሆች የት ገቡ? ስንቶቻችሁ ታስታውሱታላችሁ “ፖለቲካ የህዝብ ነው”?
ለማንኛውም ያለ እጩ ተወዳዳሪ ቀርቦ 100% እንዳያሸንፍና ኤች ዲን እንዳይስተካከል
ያሳዝናል ::