<> ክፉ መሪ ክፉ ወንበዴዎች ክፉ ጎረቤቶች ጀግና ሐገር ኢትዮጵያ Tesfahun Alemneh
በታሪክ ማህደር ብዙ ክፉዎች በሃገራችን ተከስተዋል:: በጣም ክፉዎች እጅግ በጣም ክፉዎች ግን እንደ ወያኔ ገጥሞን አያዉቅም::

እነዚህ ክፉዎች 24 ዓመት የስቃይ እና የመከራ ቀንበር ጭነዉ በኢትዮጵያ ምድር የፈለጋቸዉን በደል እያፈራረቁ ፈጥመዋል:: ዳሩ ከሕዝብ ተደብቆ የሚቀር ባይኖርም ለጊዜዉ በርካታ
ወንጀሎችን ደብቀዉ ተቀምጠዋል:: ክፉ የታሪክ ግርዶሸ ክፉ የመጥፋት አደጋ ክፉ የአለመተማመን ዘመን ክፉ ኢትዮጵያዊነት ሽርሸራ ክፉ የዘር ማጥፋት ወንጀል እነዚህ ክፉዎች ፈጥመዋል::
ለዚህ ደግሞ ክፉ ጎረቤቶቻችን ተባብረዋቸዋል:: አሁንም ድረስ ትብብራቸው ዘልቋል:: ዛሬ በተገኘችዉ ጭላጭል እነሱ በመጡበት መንገድ ያነሱት ጠበንጃ ተነስተቶ የሰሩት የፓለቲካ አሻጥር ተትቶ ስለ ሐገር ስለ ኢትዮጵያ ሲባል መራራዉ ትግል ሲፋፋም ክፉዎች እጅ እና እግራቸዉን አጣጥፈዉ እንደማይቀመጡ ቀድሞ የታወቀ ነዉ :: ቀድሞ የታወቀ
ነገር ደግሞ እዳዉ ገብስ ነው ::
ሆኖም ግን ትግል በራሱ እሾሃማነቱ የጎላ ስለሆነ በተራመድሕ ቁጥር ይወጋሃል:: ቁም ነገሩ ወደ ድል መጓዝ ሕ ብቻ ነዉ:: የነፃነት እሾህን እየቀነስሕ እንደሆነ ከተገነዘብሕ ወግቶህም
ደምተህም ወድቀሕም የሚፈለገዉን ነፃነት መጎናፀፍ እንደሚቻል ከተረዳህ በቃ! ሐቅ ነዉ ማወቅ ይቀድማል ::ያወቀ ለተግባር ቅርብ ነዉ:: አወ ለምን እንሞታለን ?ለማን እንሞታለን?
ግልፅ መልስ አለን:: መስዋት የምንሆነው ለራሳችን አጀንዳ ብቻ እና ብቻ ነው::ነፃነት ስለ ምንፈልግ እያጠፉን ስለሚገኙ ለአለመጥፋት አራት ነጥብ:: ክፉዎች በክፋት ዘመናቸው የደም ባለፀጋነትን ስለ ተላበሱ የትግል መንገድ ላይ ተደራራቢ አጥር ለማስቀመጥ ይጠቀሙበታል::ክፉ ወዳጆችንም ይገዙበታል::ማጎብደድም ማጎንበስም አይገዳቸውም::ለአሜሪካ እንደሚያጎነብሱ ለቻይናም ይሰግዳሉ:: ክፉዎች የማይደራደሩበት ነገር የለም::ምክንያት ጎጥ እንጅ ሐገር አያውቁም::
ደግነቱ የክፉዎች ተፋላሚ ሕዝብ ነዉ:: ሕዝብ ደግሞ ለጊዜው ካለሆነ በታሪክ ተሸንፎ አያውቅም:: በተፋፋመዉ ትግል ተግባር እንጅ ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም::
ማወቅ ለትግሉ ከሚጠቅም ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ ነው ::ማወቅ አላስፈላጊ ከሆነ የጎንዮሽ ትግል መራቅ ነው:: እዉቀታችን ክፍዎችን ለማስወገድ እንጠቀምበት::