የኢትዮጵያ ሰራተኞች የውጭ አገር ኩባንያዎች ባሪያዎች ሆነዋል ተባለ

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ሬዲዮ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክቶ በሰራው ዘገባ ፣ የአገሪቱ ሰራተኞች በአለም ላይ እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ክፍያ ከሚያገኙ አገሮች ቀዳሚ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ የውጭ አገር ኩባንያዎች ሰራተኞቹን እንደ ባሪያ እንደያዙዋቸው ገልጿል።
ከ11 ሚሊዮን በላይ ስራ አጥ ባለበት የሰራተኛውን የመጨረሻ የክፍያ ወለል ማስተካከል ፈታኝ መሆኑን የገለጸው ቢቢሲ፣ ወጣቱ በ50 ዶላር ወርሃዊ አማካኝ ክፍያ ህይወቱን ለመለወጥ ባለመቻሉ ስደትን አማራጭ አድርጎታል ብሎአል። የቢቢሲው ኢድ በትለር ዱከም ላይ ያናገራቸው በርካታ ስራ አጥ ወጣቶች ስደትን ብቸኛ አማራጭ አድርገው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።
ግንባታዎች እና የኢኮኖሚ እድገት ቢታይም፣ ኢትዮጵያ ከካምፖዲያና ባንግላዲሽ ባነሰ መጠን በአለም ላይ የመጨረሻውን ዝቅተኛ ክፍያ የመትከፍል አገር በመሆኗ፣ ሰራተኛው በየጊዜው እየናረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም አላስቻለውም። በኢትዮጵያ እርካሽ ጉልበት መኖሩን ያወቁት የውጭ አገር ኩባንያዎች ፣ ወደ አገሪቱ ገብተው በገፍ ምርት እያመረቱ ቢሆንም፣ የሰራተኛውን ህይወት ግን ሊለውጡለት አልቻለም ሲል ነቅፏል።
በዚህ ክፍያ ህይወትን ማቆየት እጅግ ከባድ ነው የሚለው ጋዜጠኛ በትለር፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታውን አቶ አህመድ ሸዲን፣ “ለመሆኑ አገሪቱን አማካኝ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ እናሰልፋታለን ስትሉ፣ የሰውን ገቢ ስንት ብላችሁ አስባችሁ ነው?” በማለት ጠይቆታል። ሚኒስትር ዲኤታው ጥያቄውን በማድፈንፈን ሳይመልሱት ቀርተዋል።
የአለም አቀፍ የሰራተኞች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ጋይ ራይደር ፣ ኢትዮጵያውያንን ክብርን ከሚያዋርድ ድህነት መታገድ ይገባል ብለዋል።
የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ እና የምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በአዲስ አበባ አብዛኛው ሰራተኛ በ900 ብር ገቢ የቤት ኪራይ ከፍሎና የምግብ ወጪውን ሸፍኖ ለመኖር እንዳልቻለ ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዲኤታው አህመድ ሸዲ አገሪቱ እያደገች ስትሄድ ክፍያው እንደሚሻሻል ቢገልጹም፣ ጋዜጠኛው ለውጡ አሁን አስፈላጊ መሆኑን ወጣቶችን በማናገር ገልጿል።
ቢቢሲ ኢትዮጵያዊው ወጣት ህይወቱን ለማቆየት ሲል አገሩን ጥሎ እንደሚሰደድ በዘገባው ቢያሳይም፣ በደሃውና እና በሃብታሙ መካከል እየናረ ስለመጣው የኑሮ ልዩነት ያነሳው ነገር የለም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ 100 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን የጫነ መኪና ኬንያ ውስጥ ተይዟል። ኢትዮጵያውያኑ በሞያሌ በኩል አድረገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ በመጓዝ ላይ ነበሩ። በመንገድ ላይ እየተሹለኮለኩ ለ3 ቀናት ያክል መቆየታቸውን የገለጸው ፖሊስ፣ ከፍተኛ ድካም እንደሚታይባቸውም ገልጿል። ኢትዮጵያውያኑ ወደ እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

6 Comments on “የኢትዮጵያ ሰራተኞች የውጭ አገር ኩባንያዎች ባሪያዎች ሆነዋል ተባለ”

  1. De facto USA / UK mouthpiece ESAT,
    dont you know that BBC is a mouthpiece of the UK government, and that TPLF is in power because of UK and USA ?

    Why dont ESAT remind UK’s and by extension BBC’s responsibility for the problems reported by the BBC ?

    Or are you guys dumbing down Ethiopians ?

    The evil ferenjis are responsible for most problems they report about Ethiopia. At least the ESAT guys must be smart enough to see that.

  2. These ESAT guys appear to lack basic understanding of logic.

    1. UK, and by extension BBC as it is financed by the UK government, impose TPLF on Ethiopians against their will.

    2. BBC, and by extension the UK government, complains how bad things are in UK-imposed-TPLF governed Ethiopia.

    If UK finds things bad why does it create them ?

  3. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    @tencolu አወክ አወክ ሲሉህ መፅሀፉን አጠብከው

  4. @ ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል,

    you are a strange person and yeferenjina yeAmerika aqaTari, Tebeqa.
    Your loyalty is not to Ethiopia.

  5. ESAT has the tendency of being shallow.

    I read the article.

    I found few things written by the wicked ferenjis quite offensive:

    1. የአገሪቱ ሰራተኞች በአለም ላይ እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ክፍያ ከሚያገኙ አገሮች ቀዳሚ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ የውጭ አገር ኩባንያዎች ሰራተኞቹን እንደ ባሪያ እንደያዙዋቸው ገልጿል።

    Is that true or not ?

    2. ኢትዮጵያ ከካምፖዲያና ባንግላዲሽ ባነሰ መጠን በአለም ላይ የመጨረሻውን ዝቅተኛ ክፍያ የመትከፍል አገር በመሆኗ፣ ሰራተኛው በየጊዜው እየናረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም አላስቻለውም።

    Is that true ?

    3. የአለም አቀፍ የሰራተኞች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ጋይ ራይደር ፣ ኢትዮጵያውያንን ክብርን ከሚያዋርድ ድህነት መታገድ ይገባል ብለዋል።

    That is offensive. The term “ኢትዮጵያውያንን ክብርን ከሚያዋርድ ድህነት መታገድ ይገባል ብለዋል።” is offensive and dumb ESAT should not have quoted the comment without counterattacking the formerly cannibal brits who are also partly responsible for this condition as they help to keep TPLF in power. ESAT has been often heard quoting offensive things said by ferenjis without counterattacking them. ESAT behaves that way also because it is infiltrated by Eritreans. ESAT should better change that behaviour.

    4. ቢቢሲ ኢትዮጵያዊው ወጣት ህይወቱን ለማቆየት ሲል አገሩን ጥሎ እንደሚሰደድ በዘገባው ቢያሳይም፣

    That is de facto declaring: Ethiopian refugees are economic immigrants, and not political asylum seekers. ESAT should not have simply quoted that without counterattacking the claim.

    Is ESAT a friend or an enemy of Ethiopians ?

    Are ESAT people that stupid who dont know what they are doing ?

    Another point to consider is that the ferenjis have ulterior motives when they report about working conditions in Africa in companies and factories owned by non-ferenjis, particularly Chinese. So one of the ulterior motives of the ferenjis was anti-China propaganda. And ESAT didn’t remind readers of such hidden agenda of the ferenjis and simply quoted them.

    All in all a bad job.

  6. FYI

    Wicked BBC never reported how bad working conditions for black laborers were in ferenji-owned farms in Zimbabwe.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*