ያለንበት ጊዜ በተገኘው አጀንዳ ላይ የሚነፈስበት ሳይሆን ብስለት የሚጠየቅበት ጊዜ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ስሜታውያን በርክተዋል::ተናግረው እፎይ ብለው የሚተኙ በርካቶች ሆነዋል::ልክ ልኩን ነገርጉት ብለው ሌላውን ደሞ ለማሸማቀቅ (የሚሸማቀቅ ካገኙ) አስበው በየምናምኑ የሚንጎዳጎዱ ጊዜው ይቁጠራቸው::በነፈሰበት የሚነፍሱ ሳያገናዝቡ የሚያራግቡ የፈጠራ እሳት የሚያርገበግቡ በተገኘበት ተደናብረው እና ደንብረው ደንግጠው ለማስደንገጥ የሚርበተበቱ እንዳሉ ሁሉ ሙድ ለመያዝ የሕዝብን ጭንቀት የሚጠቀሙበት ተደምረው ሆዳም በጥቅም የሚደለሉ በጠለዟቸው ሄደው የሚቾመሱ አጀንዳ እና አቋም አልባ ሮቦት ካድሬዎችም በርካቶች ሆነዋል::ይህ ሁላ የግንዛቤ እጥረት ነው::ያለንበትን ጊዜ እና የሚካሄዱ ትግሎችን አለመመዘን ለትግሉ አስታውጾ ለማድረግ ደፋ ቀና ከማለት ይልቅ ተደራሽነት ያሌላቸውን የክፋት ብእር አጀንዳዎችን ይዞ መክለፍለፍ ምም ውጤት የለውም::ለመድገም ያህል ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው::

ወያኔ ስራዋን ትሰራለች::ጓዳ ጎድጓዳ ገበናውን ስላወቀች በተላላኪዎቿ የሚሰጠውን የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች አሸክማ እሷ የውስጥ ጉዳይውን እያስተካከለች የለውጥ ሃይሎች እያሰረች እየሳደደች እየገደለች ስልጣኗን ታጠናክራለች::እና ከሚዘመሩ የሃሰት መዝሙሮች ተነስተን ወያኔ አብቅቶላታል በሚል የፕሮፓጋንዳ መደምደሚያ ላይ ትተን የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን::ራሳችን ማረም የምንጀምረው መች ይሆን ?አጀንዳ የማታጣው የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች ማዘጋጀት ስራዋ የሆነው ወያኔ የምታመጣው አጀንዳ እና የቤት ስራ አትኩሮት ባንሰእጠው ያላትን የፕሮፓጋንዳ ሂደት ማኮላሸት እንችላለን::በዚህ ሰሞን ብቻ የራያ ቢራ ባለኦክሲዮን የተባለው በአቡዳቢ የሕወሓት ንብረቶች የበላይ ጠባቂ አቶ ዳዊት ቃለ መጠይቅ – በቤንሻጉል የሰው ስጋ በሚጥሚጣ ተበላይ የሚል ወጣ ያለ ምስል – የኦሮሞ ጋላ ተብሎ መጠራት አለበት የሚል ፍትፈታ .. ኧረ በስንቱ ልበጥበጥ አለች? በሶ:: ይህንን የሚያራግቡ እና አገር ወዳዱን ርሁሩሁን ዲያስፖራ ሆዱን የሚያንቦጫብጩ አጀንዳዎች ላይ እንዲሽከረከር ማድረግ ምን ያህል የወያኔን አደገኝነት የሚያሳይ ነው::

አደባባይ ላይ አተካራ ገጥሞ የለውጥ ሃይሎን በ ነው/አይደለም አተካሮ ለማናከስ ክርክሮችን ፈጥሮ አለመግባባቶች ለማስፋት የሚደረጉ ያልተጣሩ መረጃዎች እና የፈጠራ ማዘናጊያ ጽሁፎች ምን ያህል የትግሉን ወንዝ እንደሚያሻግሩን አላውቅም:; መንገድ ዳር ሰጥሞ ለመቅረት ካልሆነ በስተቀር ሚዲያዎች ባልተናገሩት እና ምንጩ ባልታወቀ ወያኔያዊ የፈጠራ አጀንዳ እና መረጃ ላይ ፊት ለፊት እየነጠሩ መጠዛጠዝ የብስለት ስርቆት መካሄዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል::ወያኔን ለመጣል አንድ እና አንድ ነገር ያስፈልጋል ህዝብ ተስፋ የሚያስቆርጡ መረጃዎች የለውጥ ሃይሎች የእርስ በእርስ መናከስ በተገኘ አጀንዳ እንደተፈለገ ንፍስፍስ ማለት የመሳሰሉት ጉዳዮች ሊታሰብባቸው እና ሊወገዱ ይገባል::የሚመጡ መረጃዎች ሃላፊነት የሚወስድ ሰው አሊያም ሚዲያ እስካልተገኘ ድረስ አሊያም ወያኔን ወያኔ አዋረደ በሚል የዋህነት ፈሊጥ መነሳት እንዲሁም ባልበሰለ የዘረኝነት እና የመንደርተኝነት ጽሁፎች ከመቃጠል ራሳችን ማዳን እና ልብ መግዛት ይገባናል::ሁላችንም በጋራ በሚደረጉ ትግሎች ላይ ልንረባረብ ይገባል::ትግሎችን በማስፋፋት በማስተማር እና በመቀስቀስ በመርዳት ላይ ልንሰማራ ይገባል:ብስለት ማለት ለትግል የሚደረጉ አስታውጾዎችን በማበርከት እና በተረጋገጡ አጀንዳዎች ላይ ስራ መስራት ሲቻል ብቻ ነው::እና እኔም እላለሁ ያለንበት ጊዜ በተገኘው አጀንዳ ላይ የሚነፈስበት ሳይሆን ብስለት የሚጠየቅበት ጊዜ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

8 Comments on “ያለንበት ጊዜ በተገኘው አጀንዳ ላይ የሚነፈስበት ሳይሆን ብስለት የሚጠየቅበት ጊዜ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)”

  1. Good article.

    A lot of Ethiopians have been dumbed down by coward and/or sellout journalists.

    We should expect distraction from TPLF, also from its ferenji masters such as USA. We need to use our minds and warn people when necessary.

  2. በጣም በሣል ሠው ነህ ይህ ምክር በተለይ በዘር በሀይማኖት በፖለቲካ ነፃ ሀሣብ መረጃ እንዳይንሸራሸር የሚያደርጉ ሀይሎች ቢኖሩም ይህን በሠከነ ወኔ ተሣታፊ መሆን መልካም ነው መረጃ ደግሞ የለውጥ መንገድ ነው በዚሁ ቀጥል የህዝቡን ንቃተ ህሊና ከፍ የሚያረጉ መረጃዎች የሉንምና በርቱ።

  3. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    ከጣልያንና ከኢትዮጵያ የተወለደ ሰው ግማሽ ባንዳ ወይም ግማሽ አርበኛ ሊሆን ይችላል:በአሉታዊነት መጠመድ የነተንኮሉ ባህርይ መሆኑ ያሳዝናል:ምናልባት ተንኮሉና wind of change ግማሽ አርበኛ አሊያም ሙሉ ባንዳ ሊሆኑ ይችላሉ:

  4. እውነት እውነት ወዳጄ መቼም ባንዳ በመሀላችን ገብቶ ካላበጣበጠ በቀር እኔ
    ባንዳም ወያኔም አርበኛም ዘረኛም አይደለሁም የነውጥ ንፈሥ ብቅ ያረገኝ በመረጃ አቀራረባቸው የማለልኩኝ ተንኮሉ ያለንን ሀሣብ ግጭት ፈጣሪ ነው እኔ ዘረኞ አይደለሁም በአንድነት የማምን ንፁ ኢትዬጵያዊ ለውጥን ፈላጊ ድምፄ በኮሮጆ አሥማት የተሠለበበኝ ትንሽ ተንፍሼ ለመረጋጋት ብቅ አልኩ እንጂ ካጠፋሁ ይቅርታ ለአዘጋጆቹም ጭምር ጠይቃለሁ።

    ረጅም እድሜ ለ http://www.mereja.com እመኛለሁ

    wind of change

    እግዚያብሄር ኢትዬጵያን ይባርክ

  5. @ ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል ,

    The quote below tells who you are, yeAmerika Tebeqa ! You are loyal to USA according to quote below.

    ” ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says: August 18, 2015 at 5:59 am

    የአሜሪካ ጠላቶች ተንኮሉ,wind of change ኢራን …ናቸው:የክርስቶስ ጠላቶች ደግሞ ይሁዳ satan ወዘተ ናቸው:ቡጀሌ ሁላ: “

  6. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    @tencolu ጥሬጨው yes completly i am loyal to ethiopia and america too the world!this indicates as i am free from hatred-moron!

  7. “ንፈሥ ይነፍሣል እንጂ ከየት እንደነፈሠ ማንም አያውቅም”
    በሣል ሀኑ ጨው ካልጣፈጠ ድንጋይ ነው ብለውህ ……..

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*