የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ ዕጩ ተወዳዳሪ እድር ላይ ጥያቄ አነሳህ ተብለው ታሰሩ

በባሌ ዞን ሰልጣ ቀበሌ፣ ሲናና ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ወርቅነህ ጋድይ አያና የእድር ስብሰባ ላይ ጥያቄ ጠይቀሃል ተብለው መታሰራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባ አቶ ደመላሽ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ በተለይ ከምርጫው በኋላ ካድሬዎች አቶ ወርቅነህ እድርን ጨምሮ ከማህበራዊ ጉዳዮች እንዳይሳተፉ ጫና ሲያደርጉባቸው እንደነበረም ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም የአካባቢው ህዝብ ‹‹በፖለቲካ መሳተፍ ህገ መንግስታዊ መብቱ ነው፡፡ እድር ደግሞ ማህበራዊ መብቱ በመሆኑ መሳተፍ አለበት›› በማለቱ እስካሁንም የእድር አባል ሆነው ቢቀጥሉም በእድሩ አካሄድ ጥያቄ አለኝ በማለታቸው ‹‹ለምን ጥያቄ ትጠይቃለህ?›› ተብለው እንደታሰሩ አስባባሪው ገልፀዋል፡፡ አቶ ወርቅነህ ጋድይ በአሁኑ ወቅት በሲናና ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የአስተዳደር አካላት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ በሚፈፅሙት በደል ምክንያት ከትግል ውጭ ፍትህ እናገኛለን ብለው እንደማያምኑ አቶ ደመላሽ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

4 Comments on “የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ ዕጩ ተወዳዳሪ እድር ላይ ጥያቄ አነሳህ ተብለው ታሰሩ”

  1. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    the 2 commenter,tencolu and change of wind are terrorist who situated in hiden america they also danger for ethiopia

  2. @ተንኮሉ
    @ዘንድሮ….

    እባክህ ልብ ግዛ ከእውነት ጎን ቁም ሥሜተኛ አትሁን ህዝቡ ነፃ ፕሬሥን ይደግፍ ሀሣቡን በነፃነት ይግለፅ ሥልጣኔ አይመሥላችሁም የእውነት ችቦውን ያዙ እንለወጥ ዘውድን አናምልክ።

  3. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    @w/of/change እንክርዳድ እያሉ መሳደቡ ለቅቤ ጠባሽነትህ ማሳያ ነው:የስድብ ቅኔህ አለቃ ገብርሀናን ያስንቃል:ቅኔ ተዘርፋለህ ሰውም ትዘልፋለህ ስለ ስሜት ምኑን ታውቀዋለህ

  4. @ከዘንድሮ….

    የጋዜጠኛውን መንፈሥ የምታውኩ ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ ንግግራችሁ ወያኔ ምን አይነት ቦዘኔ እንደቀጠረ ያመላክታል አሥተሣሠባችሁን ለውጡ በህገ በአራዊት አትመሩ ህዝብ መሀል ነው ያላችሁት።

    ደጋግሞ እንደሚወቀር የድንጋይ ወፍጮ አትሁኑ/ን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*