አንድ የህወሃት አባል በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በሻንጣው ይዞ ሲገባ ለንደን ላይ ተያዘ

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች እንደገለጹት ፣ አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል።
ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ፣ ግለሰቡ ” ገንዘቡ የመንግስት መሆኑንና ለመንግስት ስራ ለማዋል መያዙን” ገልጻል። ይሁን እንጅ ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ በሻንጣህ የያዝከው በአገራችሁ ባንክ ስለሌለ ነው እንዴ? ” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል።
ግለሰቡ በዋስ የተፈታ ሲሆን፣ መስከረም ላይ በድጋሜ ይቀርባል። ጉዳዩን በማስመልከት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስልክ ብንደውልም፣ መልስ የሚሰጠን አካል ለማግኘት አልቻልንም።
ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግርቲ በ8 አመታት ውስጥ ከኢትዮጵያ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከአገር መውጣቱን ከሁለት አመታት በፊት ይፋ አድርጎ ነበር።

13 Comments on “አንድ የህወሃት አባል በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በሻንጣው ይዞ ሲገባ ለንደን ላይ ተያዘ”

  1. ለገሠ አሥፈው ሠበታ ላይ ብር በአህያ ጭኖ ሢጓዝ የተያዘውን አሥታወሥከኝ ይህ ነው የወያኔ ቅሌት ዋሡም ኤምባሢው ነው ልክ አሜሪካ ወዲ ትኩል ኤምባሢ ውሥጥ ተኩሥ ሠምቶ አቶ ግርማ ብሩ ወሥ እንደሆኑት ማለት ነው።

    ወያኔ የታሪክ አተላ ነው!!!

  2. @ተንኮሉ/ተኮላው ወያኔ

    የደቡብ አፍሪካማ አይደለም አታወናብድ አንተ ወንበዴ ይህ ብር ከወያኔ ካዝና ሙሥና የተመዘበረ ነው።
    የቀድሞው ሟቹ ካድሬው ቄሥ በs.africa ተገኝተው ይህን ገቢ ላኩ እኛ እናሥተዳድር ያሉትን እና የተፈጠረውን ችግር ትዝ ይበለን ወያኔ በሀይማኖት ጣልቃ መግባት የቆየ ልምድ አለው ወያኔ ይህን የተሠበሠበ ነዋይ ሁሌም በጎሪጥ እንደፈንጂ ያየዋል ለምን ብሩ የኡትዬጵያን ነፃነት ማሥጠበቅያ ይውላል ብሎ እንደሚያምን በእነሡ አባባል ዜጎችን እንደ ሽብርተኛ ዲያሥፓራ ያያቸዋል ይህ ነው እውነታው ተጨማሪ እውነታ የጉምሩኩ ጉጅሌ ገብረዋህድ ቤት ውሥጥ ሥንት ሚልዬን ፖውንድ የወርቅ ጌጣጌጥ የጦር መሣሪያ እንደተገኘ ይታወሣል ይህ በኢግዝቢትነት ተይዞ የሚገኝን ውርሥ ለማውጣት የተመኮረ መሆኑን በግልፅ ይታያል ፍርድቤቱም ይደርሥበታል።

  3. You know guys,
    if USA and UK really want they can find all stolen money from Ethiopia, including those deposited in bank accounts. The NSA ( big brother from USA, National Security Agency ) has stored all needed data.

  4. እሺ የወያኔው INSA ለነፃነት ሁሌም ከ አሜሪካ ጋር ነን ባለህበት እንመጣለን

    ክሊክ ክሊክ …..ለነፃነት ለፍትህ ለዲሞክራሢ ለአንድነት

    ክሊክ ክሊክ ቢሾፍቱ INSA

    ድል ለኢትዬጵያ የዘረኝነት ዘውድ ለማንደፋ

    ጠብቁን በ ICC ፍርድ ቤት ሙሉ መረጃ ወያኔን ልክ እንደ ሡዳኑ አልበሽር የፋይል ቀጠሮውን እየጠበቅን ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*