አዲስ አበባ በግሬቪቲ የተቃውሞ ፅሁፎችና ወረቀቶች ተጥለቅልቃ አደረች።

ፍትህ ለታሰሩት !!!! ….. አዲስ አበባ በግድግዳ ላይ ጽሁፎች እና ግራፊክስ አሸብርቃ አደረች:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Graphics‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

አዲስ አበባ በግሬቪቲ የተቃውሞ ፅሁፎችና ወረቀቶች ተጥለቅልቃ አደረች። በህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎች ላይ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ከ7 እስከ 22 መፈረዱን ተከትሎ የቁጣ መልእክት ያዘሉ መልእክቶች በአዲስ አበባ በስፋት ተፅፈው ማደራቸውን የቢቢኤን ምንጮች ገልፀዋል።


በቀይ ቀለም እንዲሁም በቀይ በቢጫ፣ ነጭ ወረቀቶች ከተፃፉት መልእክቶች መካከል
ይብቃ!!! አንባገነን ስርአት ከትከሻችን
ይውረድ!
ዋ!ዋ! ዋ!
አንባገነናዊ ፍርድ አንቀበልም!!!
ህገ–ህውሃት ይብቃ!!ህገ—መንግስት ይከበር!! ፣
ትግላችን ይቀጥላል!!
we need freedom ፣የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች ፣
ሀምሌ 27 የሀገሪቱ ሰላም ላይ የተፈረደበት ቀን
በችሎት ስም የተላለፈው ፖለቲካዊ ቀልድ ነው! ፣
ፍርድ ቤቶች ነፃ ይውጡ!!
1 ትግላችን እስከ ድላችን!
የተዘነበለው ፍትህ እስኪቀና ትግላችን ይቀጥላል!!! ፣
ፍትህ ለሙስሊሙ፣ ፍትህ ለኢትዮጵያውያን!!!
…የተጨቆነ ህዝብ የአብዮት ነዳጅ ነው!!! ፣ የሚሉና ሌሎችም እንደሚገኙበት ከአይን እማኞችና በፎቶ ግራፍ ለቢቢኤን ከደረሱት መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል። ቢቢኤን ተጨማሪ የፎቶ ና የቪዲዮ ማስረጃዎች እንደደረሱት ለህዝብ የሚያደርስ ይሆናል