አንድ ነው ደማችን ( ሄኖክ የሺጥላ )
በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ብዙ ሰብከናል ፣ ኢትዮጵያዊነት የምናምንበት የጋራ ቤታችን ነው ። ከምንም ነገር በላይ ዛሬም ዋጋ የምሰጠው ስለ ኢትዮጵያዊነቴ ነው ። ግን ግን ዋጋ ለመስጠትም ሆነ ዋጋ ለመቀበል በመጀመሪያ እኔ መኖር አለብኝ ፣ የመፈጠሬ ምክንያት የሆኑት ሰዎች ሳይኖሩ ፣ ማንነት የምለው ኢትዮጵያዊነት ሊኖር አይችልም ። ለሌሎች ሊኖር ይችላል ። እኔን ላጠፉት ፣ በዘር ፖለቲካ ፣ በለጠፉብኝ የጨቋኝነት ታርጋ ፣ ማንነቴን ላወደሙ ፣ ለነሱ ፣ ኢትዮጵያዊነት ከኔ ወዲያ ሊኖርላቸው ይችላል ። ለምሳሌ ዛሬ ኢትዮጵያ የማን ነች ? እኔ አለሁ ወይ ? የሌለሁት ኢትዮጵያዊነቴን ስለምጠላ እና ስለምጠየፍ ነውን ? እኔ ከነሱ ያነሰ ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ ነውን ? አይደለም ። እኔ የሌለሁት አማራ ስለሆንኩ ነው ። እኔ ሳልኖር ስለምትኖር ኢትዮጵያ ፣ ልጆቼ ሳይኖሩ ፣ ዘመዶቼ ሳይኖሩ ፣ ወገኖቼ ሳይኖሩባት ስለምትኖር ኢትዮጵያ ማሰብ የሚችል አእምሮ የለኝም ። የጋራ ቤታችን ነው ስንል ፣ በጋራ እስከኖርንበት ብቻ ነው ። ኢትዮጵያ የሁላችንም ሀገር ስንል ፣ በአርፍተ ነገር ላይ ብቻ ሕልውናው የተመሰረተ ሀገር በምናብ መገንባትም አይደለም ። የኔ ስል ፣ እኔም የዛ አካል መሆኔን የሚያሳይ ፣ ከዛች ሀገር ላይ የሚገኘው ማንኛውም ጥቅምም ሆነ ፣ የዛች ሀገር ማንኛውም መከራ ተካፍይ መሆን መቻል ነው ።
ለመሆኑ አማራ ነኝ የሚለው ነገር እንዲህ የሚያስፈራን ለምንድን ነው ? ኮምፒውተር እንኳ ሲሰራ ( ኢንተል ኢንሳይድ ) ይላል ። ይህ አባባል ቁሱን ወይም ነገሩን ኮምፒውተር ከመሆን አያግደውም ። አማራ መሆኔ ኢትዮጵያዊ እናዳልሆን ያረገኛል እንዴ ? እንግዲህ በደንብ እወቁት አማራ ነኝ ። በእስክስታ ያደኩኝ ፣ ጎራው ና የሚለውን እየዘመርኩ ከልጅነት ወደ ወጣትነት የገሰገስኩኝ ። አዎ አማራ ነኝ ፣ የምኮራበት ታሪክ እና ባህል ያለኝ ፣ የጀግና አባቶች ልጅ ። አማራ ነኝ ፣ በጣልያን ቀንበር ስር ሲማቅቁ የነበሩ ባንዳዎችን ሳይቀር የታደኩኝ ፣ በመቅደላ ላይ በአልበገርም ባይነት ፣ ላገሬ በክብር የሞትኩኝ ፣ አርሼ የምበላ ፣ ፈትዬ ሸማ የምሰራ ፣ የቅኔ ቤቱ ባላባት ፣ የዜማ የድጏ መሰረት ፣ የነ ዘራያቆብ ፣ የነ ዳዊት ፣ የነ ሱስንዮስ ፣ የነ ፋሲል ፣ የነ ላሊበላ መፈጠሪያ ለኔም መፈጠሪያ የሆነ ፣ አማራ ነኝ ፣ እኔም መቅኒ መበጠስ ፣ መሃል አገዳ መለየት አሳምሬ የማውቅ ።
አማራ መሆን ያሳፍርም ፣ አማራ ነኝ ማለትም አያሳፍርም ። ይልቅስ እጅግ የሚያሳፍረው ፣ አማራን ከሚያጠፉት ጋ ተሰልፎ ስለ ኢትዮጵያዊነት ማውራት ፣ ይልቅስ እጅግ የሚያሳፍረው ፣ ላለመጥብ እና ላለማነስ በሚል ሰበብ ፣ ወገን ሲገደል ፣ ወገን ሲበደል ፣ ወገን ሲራብ ፣ << ተው አማራ አትበሉ >> እያሉ መኖር ። እሱ ያሳፍራል ፣ ያናዳል ፣ ጥርስ ያስነክሳል ።
ለምሳሌ ፣ በህወሓት ዘመን ብዙ የአማራ ብሔር ተወላጆች ፣ እየታሰሩ ፣ እየተፈናቀሉ ፣ እየተሰደዱ ያሉት ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ነውን ? እነማን ናቸው ሃጋሪቷን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ በአሁኑ ሰዓት ተቆጣጥረዋት ያሉት ? እነ ማን ናቸው ዛሬ በማዕከላዊ እየተሰቃዩ ያሉት ? የነማን ልጆች ናቸው በየመን ጦርነት ጊዜ ፣ በፍጥነት ከየመን እንዲወጡ የተደረጉት ?
አማራ ነኝ ማለት አያሳፍረኝም ፣ ምክንያቱም አማራ የሚያሳፍር ታሪክ ስለሌለው ፣ አማራ ነኝ ማለት ግራና ቀኝ እንዳስብ አይደርገኝም ፣ ምክንያቱም የሆንኩትን ነገር ነውና ። አሁን እየገባኝ የመጣው ፣ አማራ ነኝ ስል ፣ የደም ግፊታቸው የሚነሳ እንደበዙ ነው ። አማራ መሆኔ እኮ ኢትዮጵያዊ መሆኔን እንደ ሌሎቹ አያስክደኝም ። ወይስ አማራ እየጠፋ ፣ እየተሰደደ ፣ እየተገደለ ፣ ለማይገባቸው ሰዎች ስለ አንድነት ልስበክ ? በወገኖቼ ስቃይ ላይ ፣ አዳራሽ ሕዝብ ሰብስቤ ልጨማለቅ ? ይበቃል ! አማራነቴን ሳትቀበሉ ፣ ኢትዮጵያውነቴን እንድትቀበሉሉኝ አልፈልግም ።
እንዲህ በዘር እና በጎሳ በሽታ የጦዘች ሀገር ፣ እንዲህ በጥላቻ መርዝ የተለከፈች እና የተበከለች ሀገር ፣ ስለ አንድነት መስበክ መጫወቻ መሆን የገባኝ ቆይቶ ነው ። መጀምሪያ ስለ እኔ መኖር ፣ እርግጠኛ መሆን እፈልጋለሁ ። ስለ ኢትዮጵያዊነት ስናገር ደስ ይላቸው የነበሩ ፣ ስለ አማራ ሳወራ የሚቀፋቸው እና የሚከፋቸው ፣ በኢትዮጵያዊነቴ እና በአማራነቴ መሃከል የአስተሳሰብ እና የሀገር ፍቅር ልዩነት ስላዩ ሳይሆን ፣ እነሱ ማጥፋት ለሚያስቡት አማራ ፣ ይሄኛው አካሄደ ህልማቸው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ስለሚደፋበት እንጂ !
ለምሳሌ የትግራይ ነጻ አውጪ የሚባል ቡድን አለ ፣ አንደኛው አዲስ አበባ ፣ ሌላኛው ደሞ ኤርትራ ። ሁለቱም አላማቸው ትግራይን ነጻ ማውጣት ነው ። በዚህ ላይ ምንም ቀወሜታ የለኝም ። የራሳቸው ጉዳይ ነው ! ግን የነሱ ነጻነት የሚመጣው አማራን በማጥፋት ፣ አማራን በመጨቆን እንዳይሆን ፣ ስለ አማራው እቆማለሁ ፣ እሞታለሁ ፣ ማንኛውንም አይነት መስዋት እከፍላለሁ ። እንደውም አንዳንድ መጻጉ አማራ ነኝ ባይ ሙሁራን ችግር የሚመስለኝ ( የወለደውን ልጅ ሳያሳድግ ፣ ህጻናት ማሳደጊያ ከፍቶ ልጆች ማሳደግ እንደሚፈልግ አይነት ሰው ስለሚመስ ለኝ ነው )። ስለ አማራነቱ እርግጠኛ ሳይሆን ፣ ስለ ኢትዮጵያዊነቱ ማውራት የሚወድ ሕዝብ አማራ ነው ። ያ ሕዝብ መንቃት አለበት ። በይበልጥ << የአማራው ጠላቱ ራሱ አማራው ነው >> የሚለው አባባል ምክንያታዊነት እጅግ ግልጽ ብሎ በሚታይበት ዛሬ !
ስለዚህ አማራ ነኝ ። እነ ጃዋር ሜንጫ ሲስሉ ፣ በአንድነት ስም መታረጃ ሞረዴን የማቀብል አማራ አይደለሁም ፣ ይልቅ እኔን ለማጥፋት ከሆነ ፣ የራሱን ሜንጫ እራሱ አንገት ላይ መሰካት የምችል አማራ እንጂ ! አማራነት በደሜ ውስጥ አለ ። ማንነቴን አክብረው ፣ ለሚኖሩ ከማንም የማላንስ ኢትዮጵያዊ ነኝ ። ማንነቴን ማክበር ላቃታቸው ፣ እኔን ለማጥፋት ቀን ከሌት ሳይተኙ ለሚያድሩት ግን እኔም የማልተኛ አማራ ነኝ ።
ፍርሃት አያውቀኝም ። ልምምጥ አልችልበትም ። ይሉኝታ ፣ የኔ ባህል መሆን ማቆብ እንዳለበት ገብቶኛል ። ለመኖር የምችለው ፣ በሁለት እግሮቼ እኔ ለራሴ መቆም ስችል ነው ። በደካማ እና ተገን አልባ አማሮች የተገነባች ኢትዮጵያን ማየት አልሻም ! ይህ ማንነቴ ነው ። እንዳልናገር የምትፈልጉትን ሁሉ ስለኔ ማንነት ከሆነ ፣ እናገራለሁ ። ኢትዮጵያዊ ነኝ ፣ በዛ ላይ ደሞ የአማራ ልጅ ነኝ ። አንድ ነው ደማችን ለዘፈን እና ዜማ ፈላጊዎች ብቻ እንዳይሆን ፣ መጀመሪያ እኔነቴን ተቀበሉ !
Tag ; – Minilik Salsawi , Henok Yeshitla , Ethiopia
I have never seen an Amhara being shy or ashamed of saying “I am Amhara”. But I know many proud Amharas who do not believe in tribalism and consider Amhara different from other Ethiopians! Many Amharas say Ethiopia first! And nothing wrong with that. Thinking of Ethiopianism first, does not at all minimize anybody’s identity as Amhara, oromo, tigre….etc. Just the reverse is true. When you think of your tribe first, you lose your sense of human being-ness and you end-up being nothing but subhuman!
ሄግኖኬ
አትሞኝ በድንበር ሥለምትዋሠን መሬትህ ናፍቋቸው እንጂ ሌላ ምን… ይህ የጫካ ሴራ ነው ሻብያና ወያኔ ያቦኩት የኢትዬጵያ ፈንጂ ዘረኝነት ነው አንድ ነች ሀገራችን ዘረኛው ወያኔም ይወገዳል
ሀገራችን አትቆራረሥም
ሞት ለወያኔ!!