የኩናማዋ ፖለቲከኛ ታሰረች።

የኩናማ ብሄረሰብ ኣባል የሆነችውና በ2007 ዓ/ም ሃገራቀፍ ምርጫ ዓረና_መድረክ ወክላ ለፌደራል ምክር ቤት የተወዳደረችው ወይዘሪት ኣብረሀት ረዳ ዛሬ ሓሙስ 07 / 12 / 2007 ዓ/ም በሸራሮ ከተማ በህወሓት ካድሬዎችና ፖሊሶች ታስራለች።

ወይዘሪት ኣብረሀት ረዳ በካድሬዎችና በፖሊስ ልትታሰር የቻለችው በምርጫ ወቅት ከውድድርና ከዓረና_መድረክ ኣባልነት እንድትለቅ በቅርብ ዘመዶች፣ በኣገር ሽማግሌዎች ተለምና፣ የገንዘብና የስራ መደለያ ቀርቦባት፣ ከምርጫ በኋላ ልትታሰርም ልትገደልም እንደምትችል ዛቻና ማስፈራርያ በተደጋጋሚ ግዜ ደርሶባት በጀግንነት ተቋቁማ ያለፈች ጀግና ናት።

የኩናማዋ ጀግና በዓለማዋ የፀናች፣ ለህዝብ ያላት ጥልቅ ፍቅር ፣ ለዲሞክራሲ፣ ፍትህና መልካም ኣስተዳደር መስፈን ስትል ከፍተኛ ትግል በማካሄድ ላይ ትገኛለች።

የወይዘሪት ኣብረሀት ረዳ ቆራጥነትና ኣልበገር ባይነት እንደ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ የህወሓት መንግስ ፀረ ዲሞክራሲያዊ ባህሪ በማጋለጥ ተጨማሪ ኣስረጂ ከመሆኑ በተጨማሪ የሴቶች መብት ኣስከብርያለው ለሚለው መንግስት በጠራራ ፀሓይ የሚያጋልጥ ነው።

በምርጫ ወቅት “ከውድድር ራስሽ ካላገለልሽ ከምርጫ በኋላ በሂወት ኣትኖርያትም” ተብላ ሲዛትባት የነበረችው ኣብረሀት መታሰርዋ ‘መቶ ፐርሰንት ኣሸናፊ ነኝ’ ብሎ ላወጀው መንግስት ሊያሳፍረው ይገባል።

ህወሓት ወይዘሪት ኣብረሀት ረዳን በኣፋጣኝ ይፍታልን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

IT IS SO………!