አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከህወሃት የደህንነት አባላት ጋር መስማማት አልቻሉም።

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ኢህአዴግ ባደረገው ግምገማ ፣ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እርሳቸውንና ቤተመንግስቱን ከሚጠብቁ የደህንነት ሃይሎች ጋር ተስማማተው መስራት አልቻሉም የሚል ትችት ከቀረበባቸው በሁዋላ፣ ግንኙነቱ ወደ ባሰ ደረጃ መውረዱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ ሃይለማርያም “በቤተሰቦቼና እና በእኔ ላይ በሚደረገው አላግባብ ክትትል ተሰላችቻለሁ” የሚል ንግግር በሁለተኛው ዙር የኢህአዴግ ሂስ እና ግለ ሂስ የአቋም ግምገማ ላይ ተናግረዋል።
የጠቅላይ ሚንስትሩ የደህንነት ጉዳይ አማካሪ አቶ ፀጋየ በርሄ እና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ዶ/ር ደብረ ፅዩን ፣ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። አቶ ሃይለማርያም ” መለስ ገ/እግዚአብሄርን ጨምሮ ሌሎች 5 የደህንነት አባላትን በእኔ ጥበቃ ውስጥ አልፈልጋቸውም” ቢሉም ሰሚ አላገኙም።
የኢህአዴግ አመራር፣ ለመሪዎች ጥበቃ የሚመረጡ የደህንነት አባላት በተጠባቂዎች ምርጫ የሚካሄድ አለመሆኑን በመናገር አቶ ሃይለማርያም፣ ተግባብተው እንዲሰሩ መክረዋል።
ይሁን እንጅ በጠቅላይ ሚንስትሩ እና በ ጠ/ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳይ ዋና ሃላፊ በመለስ ገ/እግዚአብሄር መካከል የሚታየው አለመግባባት እየጨመረ እንጅ እየተሻሻለ አለመሄዱን ምንጮች ገልጸዋል።

4 Comments on “አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከህወሃት የደህንነት አባላት ጋር መስማማት አልቻሉም።”

  1. The TPLF puppet prime minister knows that the “dehninet sewoch” are there to watch him, to make sure that he doesn’t do things that threaten TPLF.

  2. they called him crossedeye ቦታውን ማን ይያዝ በሚል ጎጥ የፈጠሩት ባንዳዎች እሡም የደቡብ ነውጥ ሞተር መሆኑን ደርሠውበታል እናም ከአቶነት ወደ ዶ/c ማእረግ በገንዘብ የገዙ ወያኔዎች ሥለመጡ ምህዳሩ ” ናይተይ እዮ እያሉ ነው እዚህ ኩሉ ተንኾል መለሥ እዩ ዋእ” እየተባባሉ ነው ሞይቶም ምዝሀረፈ ሴጣን እዩ እናም ደንቃራ የሆነባቸውን ሠውዬ መረጃም አሣልፎ እንደሚሠጥ ደህንነቱ ደርሦበታል።

    ለምን ደህንነቱ ብዙ ሠው በማፈናቸው ሊግባቡ አልቻሉም

  3. ወያኔ የሥለላ ቁጥሮችን የደዋዮን ቁጥር በመለወጥ የዚህን ህዝብ ትርታ የምታደምጡ
    አባላት ይህ የሚያመለክተው ሣይንሣዊነት ሣይሆን ኢ ሠብአዊ ድርጊትም ነው
    በራሥ አለመተማመን አሻንጉሊት መንግሥት እንዳለ አመላካች ነው።

    ህዝቡ ይህን ያውቃል ደደቦች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*