ገነነ መኩሪያ(ሊብሮ) በደርግ ዘመነ መንግስት በከፍተኛ 1 ሊቀ መንበርና የቀይ ሽብር መሪ ተዋናይ ተከሰሰ ::

በደርግ ዘመነ መንግስት በከፍተኛ 1 ሊቀ መንበርና የቀይ ሽብር መሪ ተዋናይ በመሆን የንፁህ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ነፍስ ሲቀጥፍና አካላቸውን ሲያጎድል የነበረው እርገጤ መድበው ታዋቂውን የታሪክ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ(ሊብሮ)ን በስም ማጥፋት ከሰሰ::
እርገጤ መድበው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያን የከሰሰው ኢ.ሀ.አ.ፓና ስፖርት በተሰኘው በቁጥር 1 መፅሃፉ ሲሆን::
በዚህ ክስ ሀሙስ ሐምሌ 16ቀን 07ዓ.ም አራዳ ጊዮርጊስ ፍርድ ቤት የቀረበው ገነነ መኩሪያ የዋስትና መብቱ ተጠብቆለት ለሐምሌ 30ቀን 07ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጦታል::
እርገጤ ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በቀይ ሽብር የግድያና የግርፍያ ወንጀል ላይ መሳተፉ በማስረጃ በመረጋገጡ 18ዓመት ታስሮ በምህረት መለቀቁ ይታወቃል::
* ኢ.ሀ.አ.ፓና ስፖርት ቁጥር 2 መፅሐፍ በዚህ ሣምንት በገበያ ላይ ውሏል::