“እንደ ሰው ካሰብክ ትፈለጋለህ ” ጥላዬ ታረቀኝ

የፀረ ሽብር ግብረሀይል ነኝ ብሎ የሚጠራው ቡድን አንድ ሰሞን የብሄር እና የፖርቲ ተዎፆ ያማከለ በሚመስል መልኩ ጠንካሪ የተባሉ የፖርቲ አመራርና ንፁሀን ሀሳብ ያላቸውን ግለሰቦች ከየአሉበት ሀገር ሆነ አዲስ አበባ ጨምሮ በገፍ ያስራል ህውሀት ። ይሄን የተመለከተ የአንድ ፖርቲ ብሄራዊ ም/ቤት ስብሰባ ይጠራል ለመመካከር እስሩን በተመለከተ አባላቱም በገፍ በመገኘት ጉዳዩ ጉዳያችን ነው በማለት በአትኩሮት ይከታተላሉ አፈ ጉባኤና የፖርቲ ከፍተኛ አመራር ባለበት ቀጠለ ሀሳብ መሰጠት ስለእስርና ሰላማዊ ትግል ~~~~~~~

1st እኛ በዚህ ከቀጠለ ፖርቲውን ሊዘጉብን ነው ስለዚህ ምን ማረግ እንዳለብን መመካከርና ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ አለብን አለ ቀጠል አድርጎ 2nd በዚህ ከቀጠለ እኮ እኛም አይቀርልንም የሚል ሀሳብ አመጣ ብቻ በጣም ብዙ በርከት ያለ ሀሳብ እኛም እኔም መታሰሬ አይቀርም የሚል አጀንዳ ሆነ ስብሰባው ሁሉም ባይባልም በብዛት ስለራሱ ማውራት ጀመረ በቃ በጣም ተካረረ ነገሩ በዛ መሀል የታሰሩትን ተረስቶ በራስ ዛቢያ መሽከርከር ተጀመረ ግን የሚገርመው ሀሳቡን የሚያነሱት ወሽካቶቹ መሆናቸው ነው በዚህ መሀል አንድ የምክር ቤት አባል እጁን ብቅ ያረጋል በስተመጨረሻ አፉ ጉባኤው ቀጥል የተከበሩ እከሌ ይላል የተከበሩ የምክር ቤት አባል አከሌም ብድግ ብለው ወደ ሆላ የተከበሩ አባላቶችን ከተመመለከቱ በሆላ በግርምት የአክብሮት ሰላምታ ካቀረቡ በሆላ ንግግራቸውን ቀጠሉ የገረመኝ አብዛኛዋቻችሁ አጀንዳውን አስቀይራችሁ ብንታሰርስ ብላችሁ ስታወሩ የሰማሆችሁ መሰለኝ ግን ጥያቄ አለኝ አሉ *ቆይ ህውሀት እንዴት ያስረናል ለምን ያስራናል ለዚህ ጥያቄ መልስ ያለው አለ ብለው ቢጠይቁ ዝም መልስ የለም ማብራራታቸው ቀጥለው እሳቸው እኛ እኮ ስራ ላይ የለንም አንድ እርምጃ ተራምደዋል በአሳተሳሰብ በቅንነት ተለውጠዋል በሀሳብ ይፈትኑታል አዳዲስ ሀሳብ ያመጣሉ የታሰሩት ሰዋች ቅኖች ናቸው ለአላማ ታማኝ ናቸው ነገ ለውጥ ያመጣሉ ይሄን ስለሚያውቅ ህውሀት አሰራቸው እኛን እንዴት ያስረናል ጎበዝ ይቺን መልስ የሚሰጠኝ ይኖራል እኛ እኮ ለኢህአዲግ ተመችተነዋል ለሚሰሩት ቦታ አልሰጠን ወይ አልሰራን ቦታውን ይዘን ስራ እየሰራን ያለነው እኛ ነን ለትግል እንቅፋት ሆነናል እንደውም ሊያስረን ቀርቶ ለሽልማት እንዳያጨን ነው የምሰጋው በማለት ዝምታውን አሰፈነው ሁሉም እራሱን ፈተሸ የተከበሩት ውስጥ ከሚያስራቸው የሚሸልማቸው ወይ ከፍተኛ የህውሀትን ስራ የሚሰሩ ሆነው ራሳቸውን ያገኙ ሰዋች መኖራቸውን እራሳቸውን ታዘቡ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የሚሰራ እንጂ የማይሰራ አያስርም አዘል ነገር መልክት ያለው ትልቅ ትምህርት ሰጣቸው ቢያንስ ስናውራ ባቅማችን እናውራ ሰውም ይታዘበናል በማለት እራሱ ገዤው ፖርቲ የሴራው ባለቤት ቢሆንም የሚረዳው ነገር ይኖራል በመሆኑም የት ነን ምን ላይ ነን እንዴት ነን ራሳችንን እንፈትሽ የዝሆኖንና የአይጥ ታሪክ አይነት ማለት ነው ዜና እያዬ ዝሆን ከሆላ ሆኖ አይጥ ከፊት ሆና ሰበር ዜና ሲከታተሉ ዝሆን ከሆላዋ ቁጭ ብሎል ዞር ብላ ጋረድኩህ አይደል ዝሆን እንዳለችው አይጥ አንዶለም አራጌ አብርሃ ደስታ ሀብታሙ አያሌው ብዙሀኑን እናስብ ። ይቺን መነሻ አድርጌ ባለሁበት የታዘብኩትን ላስቀምጥ ብዙ ታዝቢያለሁ ብዙ አይቻለሁ ቢያንስ ሰው አላማውን ባይረሳ መልካም ነው ስሙን ብቻ ይዞ ነገ ዛሬ በስጋት መኖር ጭራሽ መኖሩ የማይታወቅ አስታዋፅ የማያበርክት እታሰር ይሁን ብሎ እራሱን እስረኛ ያረገ በሌለበት እያለ ስጋት በኩንታል የተጫነበት የወንድ ወኔ የሌለው ሙያውን የማያከብር አሉባልታ ቦልት ስራ ያረገ እንዴት አርጎ ህውሀት ያስረዋል በጣም እንዳይሸልመው እሰጋለሁ ህውሀት ከጫት ላይና ከጫት ቤት ሰው ሲወስድ አይቼ ሰምቼ አላውቅም ከስራ ላይ እንጂ ሳስበው የሚሸልማችሁም ይመስለኛል በአርቲ ቡርቲ በተንኮል አንድ እርምጃ ሳትራመድ መግባባት ሳትችል ስብዕናህን መጠበቅ ሳትችል በምን ሀሳብ ነው በየትኛው ስራችን ከዚህ የሚወስደን ብሎ በስጋት ብዙ ባለሙያዋች ቅኖች መስራት የምትችሉ ብትኖርም አላሰራ ያሉ ሲርመጠመጡ የሚውሉ አሉ ስለዚህ ስንሰራ ወይም አንድ እርምጃ ሳንራመድ ማንም አይነካም ሰፉ ብላችሁ ኑሩ ስራ ስትሰሩ የተለየ ሀሳብ ወይም አንድ እርምጃ ስትራመዱ ግን ያኔ ፍሩ ካልሆነ ግን ለምን ያስረናል ለምን ይፈልገናል ለምን ያስጨንቀናል ተመችተነዋል በቃ አውቀነውም ይሁን ሳናውቀው ስለዚህ ልክ #እንደተከበሩት ለሌሎች አርአያ ለመሆን የት ነን ምን እያረግን ነው ለሌላ ተምሳሌት ነን ወይ ምን እየሰራን ነው ለሙያው ታማኝ ነን ወይ ብለን ራሳችንን እንፈትሽ በብዙ መልኩ ሁሉም ነገር መስዋትነት ተከፍሎበታል አክባሬ የለም ማለት አልችልም ይቺም የዝሆንና የአይጥ ታሪክ ታስታውሰኛለች ዝሆንና አይጥ የእንሰሳ ፍሽን ሲያሳዩ ዝሆን ጆሮ ላይ አይጥ ቁጭ ብላ በመድረክ ላይ ሲያልፍ ዝሆን ጆሮ ላይ ቁጭ ያለችው አይጥ ለዝሆኑ ቀወጥነው አይደል ያለችው ቢጤ አንሁን እነ እስክንድር ነጋ zOne 9 ተመስገንን ደስአለኝ እናስብ እዳ አለብን ። ፍቅር ሰላም ጤና አንድነት ከኛ ጋ ይሁን ።